Breaking News
Home / Amharic / ከምሁራን ለመንግስት የቀረበ አስቸኳይ ግልጽ ጥሪ!!

ከምሁራን ለመንግስት የቀረበ አስቸኳይ ግልጽ ጥሪ!!



የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ ባልታወቁ ሰዎች መገደልን ተከትሎ፣ በተቀሰቀሰው አመጽ ብሄርንመሰረት ያደረገ ጭፍጨፋና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል። የዜጎችን ሕይወትና ደህንነትየመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ መዋቅር ቸልተኝነት ለጉዳቱ አስከፊነት
አስተዋጽዖ ማድረጉም ተሠምቷል። የፌዴራሉ መንግስት ስላም እና መረጋጋትን በማስከበር፣የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሃላፊነቱን፣ በተገቢው መንገድ መወጣትም ያልቻለበት ሁኔታምተከስቷል። ሃገሪቱን ማለቂያ ወደ ሌለው ደም መፋሰስ ለመውሰድ፣ ባለ በሌለ ሃይላቸውእየሰሩ የሚገኙ የጥፋት ሃይሎች፣ በይፋ በሰጡት የአመራር ስምሪት፣ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑንጹሃን ዜጎች የማይተካ ህይወት እና በብዙ ጥረት ያፈሩት ንብረት በአንድ ጀንበር እንዲወድምተደርጓል።
ከዚህ ሌላ፣ መንግስት አጋጣሚውን በመጠቀም፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግ ንኙነትየሌላቸውን፣የህጋዊ ሰላማዊ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን፣ ማሰሩን ተዘግቧል። በተለይም፣በሃገር ሕልውናና ለብዙ ሰዎች ሕይወት መጥፉት ቀጥተኛ ተጠያቂ ከሆኑ ጽንፈኛ ብሄረተኞች
ጋር አጣምሮ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋንና ፣የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞያሰረበት ሁኔታም መኖሩን፣ለማወቅ ችለናል።በጽጥታ ሃይሎች ቁጥጥር የሚገኙት አቶ
እስክንድር ነጋ፣ አካላዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ለማረጋገጥ ችለናል። በአቶ እስክንድር ላይድብደባ መፈጸሙም ተረጋግጧል። ይህ ድርጊት የሕግ ልዕልናን ዋጋ የሚያሳጣ፣ የፍትህ ሂደቱንጥርጣሬ ላይ የሚጥል እና ሃገራችን የተቀበለቻቸውን አለም አቀፍ የሰብዐዊ መብት
ድንጋጌዎች የሚጥስ፣የሚወገዝ ተግባር ነው። ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድናመንግስታቸው ደጋግመው የገቡትን ቃልኪዳን የጣሰ አሳፉሪ ድርጊት እንደሆነ በአጽንኦትለማስገንዘብ እንወዳለን።
በመሆኑም፤ እኛ ከታች ስማችን የተዘረዘረው፣ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎየተከሰቱ አሰቃቂ ማንነት ተኮር የጅምላ ጭፍጨፋዎችን፣ በተጨማሪም የሚመለከታቸውየመንግስት አካላት የአደጋውን ጉዳት ለመቀነስ ያሳዩትን ቸልተኝነት በመገምገም፣ የከዚህ
ቀደሞቹን ተመሳሳይ እልቂቶችንም ታሳቢ በማድረግ፣ ጉዳዩ እጅግ ያሳሰበን መሆኑን በፅኑበማመን የሚከተሉትን ጥሪዎች እናስተላልፋለን፡፡

1. የተፈጠረውን የጅምላ ጭፍጨፋ ተከትሎ፣ በመላዉ የኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባእየታየ ያለውን የማንነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃት፣ በመከላከል የዜጎችን በህይወት
የመኖር፣ ንብረት የማፍራት እና በፈለጉት ቦታ የመንቀሳቀስ መብት የፌደራሉመንግስት እንዲያስክብር በአንክሮ እንጥይቃለን።
2. የድምጻዊውን ግድያ እና እሱን ተከትሎ፣ በዜጎች ላይ የተከሰተውን ሞት እና ንብረትየማውደም ድርጊት ፈጻሚዎችን፣ አጣርቶ ለፍርድ የማቀረብ እርምጃ ሳይውል ሳያድርእንዲካሄድ በጥብቅ እናሳስባለን። እንዲህ አይነቱን፣ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈፀሙወንጀሎችን በመምራት እና በማሰተባበር የተጠረጠሩ ወንጀለኞችን፣ ለፈጸሙት
ወንጀል የሚመጥን ሕጋዊ እርምጃ፣ ከአድሎና ከፖለቲካ ውሳኔ በጸዳ መልኩ፣ ግልጽየሆነ የፍርድ ሂደት ባለበት፣ እንዲወሰድባቸዉ እናስገነዝባለን:: በቀጣይም የሃገርን
ሕልውናና የዜጎችን ደህንነት ለአደጋ በሚያጋልጡ፣የበሄር እና ሃይማኖት ጽንፈኛየመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ፣ ሕግና ስርዐትን የጠበቀ የማያዳግም እርምጃእንዲወሰድ መንግስትን አጥብቀን እንጠይቃለን።
3. ባልደራስና አመራሩን አስመልክቶ በመንግስት እየቀረበ ያለው የክስ ሰነድ በአጽዕኖትገምግመናል:: መንግስት የጽንፈኛና ሽብርተኛ ብሄረተኞችን ተቃውሞ ለማስተንፈስ
የባልደራስ ፓርቲ አመራርን በመናጆነት ለማሰሩ ከግምት በላይ በጽኑ እናምናለን::”አንድ ንጹህ ከሚታሰር ሺ ወንጀለኞች ቢፈቱ ይሻላል” እንደሚባለው፣ ያለ በደልና
ተሳትፏቸው የታሰሩት የባልደራስ መሪና አመራሮች ላይ የቀረበው ክስ የማያሳምንናመሰረት የለሽ ውንጀላ መወገዝ ያለበት መሆኑን በፅኑ እናምናለን።
4. የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በሰላምና ሕጋዊ መስመር የሚያምን፣ መሪውአቶ እስክንድር ፣ በሰላማዊ ትግል እና በሕግና በስርዐት የሚያምኑ፣ አለም የመሰከረላቸው የሰብዐዊ መብት ታጋይ ናቸው:: እኚህን፣ ታላቅ የሰላም ታጋይ፣መሰረት በሌለው፣ የወንጀል ጥርጣሬ ማሰር ዜጎች በሰላም ለመታገል ያላቸውንተነሳሽነት የሚጎዳ ወደ አመጽና ሽብር የሚውስድ ውሳኔ ነው:: በመሆኑም፣ ይህንየቀውስ አጋጣሚ በመጠቀም፣ ባልሰሩት ወንጀል ተጠርጥረው፣ በእስር የሚገኙት፣የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር : አቶ እክንድር ነጋ፣ የድርጅት ጉዳይ
ሃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወሮ ቀለብ (አስቴር) ስዮም እና ሌሎች የፓርቲውአባላት አለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ እንጠይቃለን።
5. የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር፣ አቶ እስክንድር ነጋ፣ በጸጥታ ሃይሎችቁጥጥር በነበሩበት ወቅት፣ አካላዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው መዘገቡ ይታወቃል።የህን ድርጊት በጽኑ እናወግዛለን። ሕግና ስርዐትን ተላልፈው በአቶ እስክንድርናበተከታዮቹ ላይ ድብደባ የፈጸሙ፣ የጸጥታ አካላት ላይ፣ ተገቢ የሆነ አስተዳደራዊእርምጃ እንዲወሰድም፣ አጥብቀን እንጠይቃለን።
6. ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና መንግስታቸው፣ የድምጻዊውን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙጥቃቶች፣ ህይወታቸውን እና ንብረታቸውን ላጡ፣ ወገኖች አስፈላጊውን መልሶ
የማቋቋም ድጋፍ እንዲደረግ፣ በግንባር ቀደምትነት የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ፣እንጠይቃለን። በዚህ አሳዛኝ አደጋ ለሞቱ እና ለተጎዱ ወገኖች ብሄራዊ የሃዘን ቀን
እንዲታወጅ፣ ጥሪ እናቀርባለን።
7. በሃገር ውስጥና በተለያዩ የአለም ማዕዘናት ሆነው፣ በማህበራዊ ሚድያ፣ በቴሌቪዥንናበዪቱብ፣ የዘር ማጥፉት ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት እንዲፈጸም፣ በቀሰቀሱ አካላትላይ ክትትል ተደርጎ፣ ለሕግ የሚቀርቡበት እንቅስቃሴ እንዲጀመር፣ እናሳስባለን።
በመጨረሻም፣ መንግስት ዛሬ በሃገራችን ለሚታየው ልቅ ጽንፈኝነትና ሃገራዊ ቀውስ፣በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከተጠያቂነት እይድንም።

እንደ ሃገር ከገባንበት ፖለቲካዊ ቅርቃርለመውጣትና ሁሉንም ዜጋ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ፣ መንግስት፣ ከአድሏዊነት የጸዳ፣ከተረኝነት ስሜትና ጠባብ አመለካከት የራቀ፣ ሀገርና ሕዝብን ያስቀደመ፣ እንዲሁም ሀገራዊአንድነታችንን መሰረት ያደረገ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ አቅጣጫ፣ ጸንቶ እንዲይዝም፣ከመምከር ባለፈ፣ በአንክሮ አናሳስባለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ዩኤስ አሜሪካ
ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር ገብርዪ ወልደሩፋኤል ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር ሞገስ ወልደሚካኤል ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር አክሎግ ቢራራ ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ኔዘረላንድስ
ዶክተር ወንድሙ መኮንን ብሪታኒያ
ዶክተር ግርማ ብርሃኑ ስዊድን
ዶክተር ተድላ ወልደዮሃንስ ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር ሰማህኝ ጋሹ ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር ፍጹም አቻምየለህ ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር አብርሃም ጥበቡ ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር ልዑልሰገድ አያሌው ካናዳ
አቶ ሙሉጌታ አያሌው ዩኤስ አሜሪካ
አቶ ሃይለገብኤል አያሌው ዩኤስ አሜሪካ
አቶ ጌታነህ ካሳሁን ዩኤስ አሜሪካ
ዶክተር አምሳሉ አስናቀ ዩኤስ አሜሪካ
አቶ ሙሴ እንግዳሸት ዩኤስ አሜሪካ
አቶ መስፍን አማን ኔዘርላንድስ
አቶ ማስተዋል ደሳለው ዩኤስ አሜሪካ

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.