Breaking News
Home / Amharic / ሰበር ዜና – ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ህብረት !

ሰበር ዜና – ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ህብረት !

ሃገር በሴራ እና በውሸት አትመራም!!!

 
የሸዋ ፋኖ በምንጃር እና ሸንኮራ ልዩ ስሙ አውራ ጎዳና በተባለ ቦታ የኦሮሚያ መንግስት ታጣቂዎች ያደረጉትን ጥቃት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ።
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ #መዋቅራዊ በሆነ ጥቃት ብዙ መሰዋዕትነት መክፈል ከጀመረ ከሰላሳ(30 ) አመታት በላይ አስቆጥሯል።
ዛሬም እንደ ትላንቱ በመንግስት ስልጣን እና መዋቅር በመታዘዝ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና የሚባል ቀበሌ ላይ የመንግስት ታጣቂዎች ማለትም የኦሮሚያ ልዩ ሃይል፣ የኦሮሚያ ሚሊሻ እና የኦሮሚያ ሰላምና ደህንነት ሃላፊ በጥምረት በከፈቱት ጥቃት የአንድ ወንድማችን ሕይወት ሲሰዋ 6 የሚሆንኑ ወንድሞች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የኦሮሚያ ሚሊሻ ልብስ የለበሱ እና መታወቅያ የያዙ በባለ ሶስት ኮከብ ማዕረግ ወታደር እየተመሩ መነሻቸውን መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ዜጎች ላይ የቡድን መሳርያ ተኩስ በመክፈት እና አካባቢው ላይ ያሉ የፌደራል ፖሊሶችን #በመግደል ወደ ሌላ ጥቃት ሊሸጋገሩ ሲሉ በጀግናው የምንጃር ህዝብ እና በሸዋ ፋኖ ትብብር ብዙ ጉዳት ሳያደርሱ ቀርተዋል።
ሰላም ወዳዱ የአማራ ህዝብ የማንም ሰው ህይወት ሳይጠፋ እነዚህን ታጣቂ አካላቶች በሰላም እጅ እንዲሰጡ እና በሰላም ችግሩ እንዲፈታ ቢጠይቁም አሻፈረኝ በማለታቸው እና ተኩስ አቁሙ በሰላም እጃችሁን ስጡ ሲል የነበረን ወንድማችን ላይ በመተኮስ በመግደላቸው ብሎም ሌሎች ሰዎች በማቁሰላቸው ራስን ለመከላከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ህወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
ከላይ እንደተባለው የኦሮሚያ መንግስት የጸጥታ አካል እንደሆኑ ብዙ መረጃወች እጃችን ላይ የሚገኝ ሲሆን ራሱ ገዢው መንግስት ባወጣው ህግ የማንኛውም ክልል ሚሊሻ እና ልዩ ሃይል ወደ ሌላ ክልል ያለምንም ስምምነት ወይም ፍቃድ ወደ ሌላ ክልል መግባት የማይቻል መሆኑ እየታወቀ ድንበር #ጥሰው ገብተው #ጥቃት ለማድረሳቸው በቂ መረጃ እያለ መንግስት ግን ግጭቱ የተፈጠረው ድንበር ጥሰው በመጡ ታጣቂዎች አማራ ክልል ላይ ጥቃቱን መፈጸማቸውን በመካድ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደተፈጸመ #አርጎ ያወጣው መግለጫ የአማራ ህዝብን #የካደ እና በሞቱት ወገኖቻችን ደም #መቀለድ መሆኑ ታውቆ እንዲስተካከል ስንል እናሳስባለን።
በመሆኑም የሸዋ ፋኖ የሚከተሉትን ባለ 4-ነጥብ መግለጫ አውጥቷል
1) የዚህ ጥቃት ዋና አቀነባባሪ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በህግ እንዲጠየቁ ስንል እናሳስባልን፣
2) በኦሮሚያ ክልል እንደተፈጸመ ተደርጎ በየሚዲያው የሚሰጠው መግለጫ ፍጹም ውሸት መሆኑ ታውቆ የአማራ ህዝብን ይቅርታ እንዲጠየቅ ስንል እናሳስባለን፣
3) ኦሮሚያ ክልል ወደ አማራ ክልል የሚደረገውን ህገወጥ #ወረራ እንዲያቆም፣ ግጭቱ የተፈጠረው አማራ ክልል ሆኖ ሳለ ኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ቆርኬ ቀበሌ የተባለው ባስቸኳይ ማብራርያ እንዲሰጥበት እናሳስባለን፣
4) መላው የአማራ ህዝብ የብልጽግና መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረገ ያለውን #መዋቅራዊ #ጥቃት እውቅና እንዲኖረው ስንል ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለቀጣይ መንግስት ሃገር በውሸት እና በሴራ እንደማይመራ አውቆ ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳሰቢያዎች ባስቸኳይ መፍተሄ እንዲሰጥ ስንል እያሳሰብን ባስቸኳይ መፍተሄ የማይሰጠን ከሆነ ህዝባችንን ይዘን ወደ ሌላ የትግል ምዕራፍ እንደምንሸጋገር እናሳስባለን።
አማራ በልጆቹ ክንድ የተቃጣበትን የህልውና አደጋ ይቀለብሳል!!!
 

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.