Breaking News
Home / Amharic / ፋኖና የአማራ ሀይል ከጠላት የማረከዉን መሳሪያ የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት እየነጠቀዉ ነዉ::

ፋኖና የአማራ ሀይል ከጠላት የማረከዉን መሳሪያ የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት እየነጠቀዉ ነዉ::

ቶማስ ጃጃዉ ከጦር ግንባር
————-
በአማራ ሀይልና በፋኖ ላይ በኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት  ከጀርባዉ የሚደረግበት የተቀናበረ ሴራ ሊቆም ይገባል ሲል አስጠነቀቀ !
————————
 
ፋኖና የአማራ ሀይል ከጠላት የማረከዉን መሳሪያ የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት እያስፈታዉ እና እየነጠቀዉ. ነዉ ሲል ቶማስ ጃጃዉ ለህብር ሬዲዮ ገለጸ። 
 
ከፋኖና የአማራ ሀይል ጀርባ ተንኮል እየተጎነጎነ መሆኑ ግልጽ ሆኗል. ሲል ቶማስ ጃጃዉ ከጦር ግንባር ሆኖ ለሚመለከተዉ ሁሉ ብዙዎች በሹክሹክታ የሚያወሩትን እና አንዳንዶችም ከኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት ጋር መሰለፍ በአንድ ጨረቃ ሰባቴ ምሎ ሰባት ጊዜ መከዳትን የሚያስከትል የእዳ ዉል ነዉ ሲሉ ገና ከመነሻዉ የተነበዩትን ነገር በመረጃ ፍርጥ አድርጎታል።
 
ቶማስ እንደገለጸዉ ለፋኖና የአማራ ሀይል እንኳን መሳሪያ ጥይት አልቀረበላቸዉም። ሌላዉ ቀርቶ በራሳቸዉ ተጋድሎ  የማረኩትን መሳሪያ የመግፈፍ እና ትጥቅ የማስፈታት ወንጀለኛ እንቅስቃሴ በአቢይ ሀይል ተጠናክሮ ቀጥሏል። 
 
በተለይም ደግሞ በጠለምት ግንባር አንድም የኦህዴድ/ኦነግ መከላከያ አልተሰለፈም። ይሄ ግንባር ህዉሃት ለአመታት የገነባዉ የጦር ግንባር የተሰለፈበት መሆኑ እየታወቀ የአማራ ሀይልን እና ፋኖን  ብቻዉን በዚህ ግንባር በማሰለፍ ሆን ብሎ ኦህዴድ/ኦነግ መራሹ መከላከያ.   የተቀነባበረ ሴራ እየሰራ ነዉ ሲል ቶማስ ጃጃዉ ለህብር ሬዲዮ መግለጹ ተዘግቧል።
 
 ቶማስ ጃጃዉ እንደገለጸዉ ከሁሉም አሳዛኙ በዚህ ህዉሃት እስካፍንጫዉ በታጠቀበት እና እጅግ ብዙ ሰራዊት ባሰለፈበት ግንባር
 
የአማራ ሀይልና ፋኖ መሳሪያም ሆነ ጥይት አይቀርብለትም. ሲል አብራርቷ ።
 
በዚህም ግንባር እራሱ ይዞት በገባዉ የተወሰነ ትጥቅ ከጠላት ላይ መሳሪያ ሲማርክም በአቢይ ትዕዛዝ በኦህዴድ/ ኦነግ ሰራዊት ይነጠቃል ሲል ገልጿል። 
 
ቶማስ ጃጃዉ ለጊዜዉ ከመግለጽ የተቆጠበዉ መረጃም እንዳለዉ ከገለጽ ብሗላ ይሄ በአማራ ሀይልና በፋኖ ላይ ከኋላ በኩል የሚደረግበት የተቀናበረ የማጥቃት ሴራም እንዲቆም ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ቶማስ ጃጃዉ ለህብር ሬዲዮ የገለጸዉን መረጃ ህብር በዜና እወጃዉ በሚከተለዉ ሊንክ አቅርቦታል። ሙሉ ዝርዝሩን ያድምጡት !
————
Watch “Hiber Radio Daily Ethiopia News Nov 23,2020| ሕብር ሬዲዮ ዕለታዊ ዜና | Ethiopia” on YouTube

Check Also

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በአማራ ላይ የለየለት ጥላቻ!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በአማራ ላይ የለየለት ጥላቻ ባይኖረው ኖሮ በተለያዩ አካባቢዎች ዓመቱን ሁሉ የደከምንበት ሰብል …

የደብረ ብርሃን ከንቲባ ፖለቲካ !

  የቅርብ ጊዜ ትዝታዎችን እናስታውስ እስቲ ጊዜውን ባልጠበቀ ሁኔታ ተፈራ ወንድማገኝ ከዞኑ አስተዳዳሪነት እንዲነሳ ሲደረግ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.