Breaking News
Home / News / ፋኖና መንግስት ዛሬ ተስማሙ! ፋኖ ትጥቅ አይፈታም!

ፋኖና መንግስት ዛሬ ተስማሙ! ፋኖ ትጥቅ አይፈታም!

ከፋኖ የተሰጠ ጥብቅ መግለጫ
15/8/2012
ሁሉም አማራ(ኢትዮጵያዊ) ይሄን መግለጫ ያንብበው ለሌላውም ያጋራው

በአርበኛ መሳፍንት የሚመራው የፋኖ ሀይል እንዲሁም በሌሎች ጀግና የፋኖ አመራሮች የሚመራው አይበገሬው የፋኖ ሀይል በታላቁ የአማራ ህዝባችን ላይ ጭቆናና በደልን ሲያደርሱ በነበሩ አሁንም እጃቸውን ካልሰበሰቡ ሆድ አደር ካድሬዎች ጋር እየተጋፈጥን ህይወታችንን እየገበርን መቆየታችን ይታወቃል የመጨረሻ ግባችንም የነበረው የፋኖን አደረጃጀት በማጠናከርና ፋኖን በማስታጠቅ ሙሉ አማራን ተቆጣጥሮ የአማራ ህዝብ እራሱ በመረጠው ለአማራ ህዝብ ከልቡ የሚቆረቆር አመራርን ማስቀመጥ ነው አማራ ምድር ላይ የጎጠኝነትን መርዝ በመርጨት አማራ አንድ እንዳይሆን እንዲዳከም አቅም እንዲያጣ የተበጣጠሰና መርህ አልባ ጉዞን እንዲያደርግ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲገጥም አጥብቀው የሚሹ የእናት ጡት ነካሾች ባንዳዎችን ፍርድ እንዲያገኙ ማድረግ ነው እኒህ ሆድ አደር ባንዳዎች የአማራ ህዝብ እናት ሀገር ኢትዮጵያን ወዳድ ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ሞጋች አመራሮች እንዳይኖሩት ሲያሴሩ መኖራቸው ግልጥ ነው ለዚህም ማሳያ እነ አሳምነው ፅጌ, አምባቸው መኮንን እና ሌሎችም ጀግና መሪዎቻችን ላይ በተሰራ ድራማ ገለዋቸው ሲያበቁ እርስ በእርሳቸው ተገዳደሉ የሚል ቀልድ ነግረውናል እንዴት ለአንድ አላማ በአንድ ላይ የተሰለፋ ጀግኖች ተገዳደሉ ሲሉን እንድናምናቸው ይጠብቃሉ?

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አለማችን ላይ በተከሰተው የcovid 19 corona virus ምክንያት የሆዳችንን ቁርሾ ለጊዜው ወደኋላ ብለን ለታላቁ ህዝባችን ጤና ቅድሚያ በመስጠት ከመንግስት ጋር ድርድር እያደረግን መቆየታችን ይታወሳል በዚህም ዛሬ ባደረግነው ድርድር በብዙ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ ደርሰናል ከስምምነቶቹ መካከል አሁን በስልጣን ላይ ያሉና ለሆዳቸው በመገዛት የአማራን ህዝብ ትጥቅ ለማስፈታትና ለማስጠቃት መከላከል እንዳይችል ለማድረግ የጣሩ, የአማራን ህዝብ አቅሙን ለማሳጣት በጎጥ ለመከፋፈል የጣሩ በማንኛውም ምክንያት አሳበው የአማራን ህዝብ የበደሉ, የገደሉ ያሸማቀቁ አመራሮችን ከስልጣን ማውረድ እንዲሁም ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ ማድረግ የሚለው ይገኝበታል ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምናወጣ ሲሆን በድርድሩ ስምምነት ላይ መድረሳችንን ግን ለመግለፅ እንወዳለን

የአማራ ህዝብ ሆይ እኛ ለእናንተ ስንል ህይወታችንን እንሰጣለን እናንተ ለኛ ስትሉ አንድ ሁኑ!!!

የፋኖ የጎበዝ አለቃ ጀግናው ሻለቃ መሳፍንት እና በመንግስት ተወካዮች አማካኝነት እረዘም ላለ ግዜ ሲደረግ የሰነባበተው ድርድር/ሽምግልና በዛሬው እለት በስኬት ተጠናቋል። ለዚህ ዋና ሃላፊነት ወስደው ከላይ ታች በማለት ከፍተኛውን ድርሻ የተጫወቱት የሃገር ሽማግሌዎች ናቸው።

ይህ አላስፈላጊ ፍጥጫ በሰላም ውይይት እንዲቋጭ ሁላችንም ስንወተውት ሰነባብተናል። በዚህ ወቅት በሃገር የጋራ ጠላት ጉዳይ ብቻ ላይ ነው ጦርነትም የግድ የሚሆን። ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ ባለመስጠቱ ስንወቅሰው የነበረው የመንግስት አካል አሁን ለተደረሰው ስምምነት በመድረሱ በዚሁ ቀጥሉ ልንል እንወዳለን።
ዳባት እንኳን እፎይ አልሽ!
ጎንደር ይህ የሰላምሽ መስፈን መሰረት ይሁንልሽ!
ሃሳብ ገብቶት የነበረው መላው አማራ ደስ ይበልህ!
ኢትዮጵያ በልጆሽች መሃል ደም አይፍሰስ ጠላቶችሽ ይከፉ!ይፋኖ ደጋፊዎች እንኴን ደስ አላችሁ።

ሙሉነህ ዮሃንስ

ፋኖን ደግፉ

Check Also

የአማራ ሀይልና መከላከያ ከወልቃይት እንዲወጡ በአቢይ አህመድ ትእዛዝ ተሰጠ።

——————–#ወልቃይትን__እናድን—-———– የኦህዴዱ አብይ አህመድ ክህደት በወልቃይት ላይ #ግርማካሳ በርካታ ሜዲያዎች እየዘገቡት ነው፡፡ የአማራ ክልልና የአማራ …

ለአማራ ሕዝብ የቀረበ ጥሪ – Please share

Related Posts:አስቸኳይ ስብሰባ ለአማራ ሕዝብ ! Please shareመልዕክት ለአማራ ሕዝብ - አማራ የሆናችሁ ምንድነው የምትጠብቁት …

One comment

  1. I really wish this news comes from real Amhara but Muluneh Yohans is ginbot 7 cadre well known in Seattle, I believe he’s now Ezima trying to meddle in fanos… Since he’s from Gonder he might trap Fanos. This is Amarawi mkir! Please be careful!!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.