Breaking News
Home / Amharic / ጦርነት ተጀመረ !

ጦርነት ተጀመረ !

ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በመሰንዘሩ ሀገር እና ህዝብ ለማዳን ሲባል መከላከያ ሠራዊቱ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ መታዘዙን ገለጹ። 

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእኩለ ሌሊት በኋላ እንዳስታወቁት ህወሓት ትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን እና የሰሜን እዝን ለመዝረፍ መሞከሩን አስታውቀዋል። 

ህወሓት በአማራ ክልል በዳንሻ በኩልም ጥቃት መክፈቱን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህ ሙከራ በአማራ ክልል በነበረው ኃይል እንደተመከተ ገልጸዋል። 

“ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል ፤ ሀገር እና ህዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል እና በየአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ትንኮሳዎችን በንቃት በመቃኘት ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅረበዋል።ጦርነት ተጀመረ

Check Also

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !!

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !! ********************************************** #ሼር እናድርግ #እናዛምት ከቅዳሜ ግንቦት 5/2015 …

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። መሳይ መኮነን

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። እነአብይ አሁን ብቻቸውን አይደሉም። ከእነጌታቸው ረዳ ጋር ተጣምረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.