Breaking News
Home / Amharic / ጣና ሀይቅ እየደረቀ አብይ እስካሁን ዝም ብሎአል። ጉድ ተመልከቱ።

ጣና ሀይቅ እየደረቀ አብይ እስካሁን ዝም ብሎአል። ጉድ ተመልከቱ።

ጥያቄ ነው።ሳትሳቀቁ #SHARE አድርጉ።ፖስት አድርጉት።በየግሩፑ አጋሩት‼️በዛሬው የአረንጓዴ ቀን እየደረቀ ስላለው ጣና እንጮሃለን!

ዶ/ር አብይ በቴሌኮም ሳይቀር “የችግኝ ተከላ” መልእክት አስተላልፈዋል።5 ቢልየን ችግኝ እንተክላለን እያሉም ናቸው።

5 ቢልየን ችግኝ መተከሉ የሚያስከፋው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም።ነገርግን ፦

-የአባይ ግድብ ሕልውና የሆነው፣ ከመከራው ውኃ የተረፈ፣ ከኤዶም ገነት የተጨለፈ፣ የቃል ኪዳኗን መርከብ ያንሳፈፈ፣ ፍጥረቱንም ሁሉ ያተረፈ ጣና ሐይቅ ወደ እርሻነት ሲቀየር ምነው ግድ አልሰጥዎት አለ?

ይኼ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣
የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኒስኮ የተመዘገበ ሐይቅ ፣በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች እና 27 ገዳማትን አቅፎ
የያዘ፣ የ7509 ዓመት የዕድሜ ባለጠጋ የሆነው ጣና ከ900 በላይ ሄክታር ወደሜዳነት ሲቀየር ምነው ያልሰሙ መስለው ዝምታን መረጡ?

በውኑ ሰው ሰራሽ ሐይቅ እገነባለሁ፣የቆሸሹ ወንዞችን እና የአዲስ አበባን ጎዳናን አፀዳለሁ በፀጌረዳ አበባም አስውባለሁ፣የኢትዮጵያን መሬትም አረንጓዴ አለበሳለሁ ከሚል መሪ ይሄ ይጠበቃልን?

አልሰሙም፤አላዩም እንዳንል ቦታው ድረስ ሄደው “የእምቦጭን አረም ለማጥፋት የፌድራል መንግሥት እየሰራበት ነው።ጠላቶቻችን በዚህች ቅድስት ሀገር ላይ ጦርነት ቢያውጁም አሸንፈው አያውቁም፡፡እምቦጭንም እናሸንፈዋለን” የሚል ዲስኩር አሰምተው እንደነበረ መቼም የሚዘነጉት አይመስለኝም።

ይኼን ቃል ከተናገሩ ግን ይኼው ሁለት አመት ሊሞላው ነው ክብር ጠ/ሚ አብይ አሕመድ።

ሐይቁስ ለምን ለአማራ ክልል ብቻ ይተዋል?

የመላው ኢትዮጵያ አይደለምን?

አባይን ገድበን 6 ሺህ ሜጋ ዋት እናመነጫለን፣የኢትዮጵያን ጨለማ እንገፈዋለን የምንለው እኮ ከዚሁ ክልል ከሚመነጨው ጣና ሐይቅ ላይ ነው።ነገርግን ይብዛ ይነስም እየታገለ ያለው ክልሉ ብቻ እንጂ ሌላው ግድ ያለው አይመስልም።#SHARE!

Tadele tibebu – ታደለ ጥበቡ

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

One comment

  1. The nearby construction developments had been dumping so many tons of debris into Lake Tana regularly for decades which caused this problem, the Bahir Dar city knew the illegal dumping of debris into Lake Tana but failed to stop the practice due to corruption which brought this problem we face now.

    Investigation should be launched about illegal dumpings that went on for decades and the responsible parties including the ADP officials who let these dumping of debris practices continue need to be held accountable . Soon the crucifix will get robbed due to these weed problem on Tana which will be the final nail on Orthodox Ethiopia’s coffin.

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.