Breaking News
Home / Amharic / ዶ/ር አብይ ከላይ በተገለፀው አጣብቂኝ ውስጥ

ዶ/ር አብይ ከላይ በተገለፀው አጣብቂኝ ውስጥ

ዶ/ር አብይ ከላይ በተገለፀው አጣብቂኝ ውስጥ ቢገባ በመግቢያዩ ላይ እንደገለፅኩት “ቀዩ” መንግስቱ ኃይለማሪያም እንደሚሆን አትጠራጠሩ። ስለዚህ ዋናው ጥያቄ “የዶ/ር አብይ አመራር በጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ወይ?” የሚለው ነው። እንደሚታወቀው የዶ/ር አብይ አመራር ከውስጥም ሆነ ከውጪ በጥርጣሬና ተቃውሞ የተሞላ ነው። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን የመጣ ሰሞን ዲያስፖራዎች “የህወሓት ቅጥረኛ/ተላላኪ” ሲሉት ነበር። ህወሓቶች ደግሞ “ደርግ ነው፣ የአሜሪካ ቅጥረኛ ነው፣ የግብፅ ወዳጅ፣ የኢሳያስ ተወካይ፣ የአረቦች አገልጋይ፣…” ይሉታል። የአማራ ተቃዋሚዎች ደግሞ “ዶ/ር አብይ ኦነግ ነው፣ ጃዋር አማካሪው ነው፣ ተተኪነት ነው” ሲሉ ደቡቦች ደግሞ “ጨፍላቂ ነው፣ አምባገነን ነው፣ ኦሮማራ ነው” ይላሉ። የተቀረው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ “ዶ/ር አብይ ልፍስፍስ ነው፣ አቅመ ቢስ ነው፣ ፓስተር ነው! አፈ-ቅቤ ነው” ይላል። አሁን ደግሞ ኦቦ ለማ መገርሳ የዶ/ር አብይ ተቃዋሚ ሆነው መጥተዋል።

የዶ/ር አብይ አመራር የኃይል እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፉ በጣም ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች ተከስተዋል። ከእነዚህ ውስጥ፤ የሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት፣ የአብዲ ኢሌ የመጨረሻ ሳምንታት፣ በአዲስ አበባ በሚኖሩ የጋሞና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት፣ ቤተ መንግስት የገቡት ወታደሮች፣ የኦነግ-ሽኔ ትጥቅ አለመፍታትና በወለጋ የነበረው ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ በጉጂ ዞን የሚኖሩ የጌዶኦ ተወላጆች መፈናቀል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በኦሮሞና አማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመው ጥቃት፣ በሀረር ከተማ የሚታየው ውጥረትና ግጭት፣ በቴፒ ዞን በተደጋጋሚ የሚታየው ግጭትና አለመረጋጋት፣ በቦረና እና ጌሪ ጎሳዎች መካከል የነበረው ግጭትና ብጥብጥ፣ ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን በቅማንት ማህብረሰብ የተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ፣ በከሚሴና አጣዬ አከባቢዎች የተፈጠረው ብጥብጥ፣ በአዊ ዞን ጃዊ አከባቢ የተፈጠረው ግጭት፣ በአማራ ክልል አመራሮች እና በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ላይ የተፈፀመው ግድያ፣ በጃዋርና ህወሓት ጥምረት የተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች የተፈጠረው ሁከትና ግድያ፣ በአፋርና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ በተደጋጋሚ የሚታየው ሁከትና ብጥብጥ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚታየው ግጭትና አለመረጋጋት እና የመሳሰሉትን እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል።

ከላይ በተገለፀው መሰረት የዶ/ር አብይ አመራር በጭፍን ተቃውሚዎች፣ አክራሪ ብሔርተኞች እና ህወሓቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በፈጠሩት ጥምረት አማካኝነት በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በሚያስነሷቸው ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ምክንያት የመንግስት መዋቅር፣ ሃብትና ተቋማዊ አቅምን ተጠቅሞ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ አጣብቂኝ ውስጥ ከትተውታል። በሌላ በኩል አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል የዶ/ር አብይ መንግስት የኃይል እርምጃ በመውሰድ ነገሮችን ፀጥ-ለጥ እንዲያደርግ ግፊትና ጫና ከማድረግ አልፎ የፀጥታ መዋቅሩ አቅመ-ቢስ እንደሆነና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማስከበር እንደተሳነው እስከመግለፅ ተደርሷል።

“መንግስት አቅመ-ቢስ ነው” ብለው የሚንቁት ሆኑ “መንግስት ከመጠን ያለፈ ኃይል ተጠቅሟል” ብለው የሚወቅሱት ኃይሎች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ዶ/ር አብይ “ቀዩ” መንግስቱ ኃይለማሪያም እንዲሆን የሚማፀኑ መሆናቸው ነው። ነገሩ ከተራ የቃላት ጨዋታ አልፎ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት የዜጎች ህይወትን ከመቅጠፍ ወደ ቤተ መንግስት ወደታደር እስከማዝመት ደርሷል። በአንፃሩ የዶ/ር አብይ አመራር እነዚህ ኃይሎች በሚፈልጉት ደረጃ የኃይል እርምጃ ላለመውሰድ፣ በዚህም የመንግስቱ ኃይለማሪያምን ታሪክ ላለመድገም ሲታገል ቆይቷል። ዶ/ር አብይ እንደ ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም የቀይ ሽብር ዘመቻን ለማወጅ የሚያስገድድ ሁኔታ የተፈጠረው ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ላይ ነው። የሰኔ 16/2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ለዚህ በቂ አልነበረም የሚል ካለ በአመቱ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በባህር ዳር እና አዲስ አበባ የተፈጠረው ችግር ከበቂ በላይ መሆኑን አይክድም። ይሁን እንጂ የዶ/ር አብይ አመራር የደርግን ስህተት ላለመድገም ተጠንቅቆ በመጓዝ ዛሬ ላይ ደርሷል። ወደፊትም ቢሆን በጭፍኖች ወጥመድ ውስጥ ይወድቃል ብዬ አላስብም።
****

ስዩም ተሾመ

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.