Breaking News
Home / Amharic / የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን ዛሬ አስመርቀ ! ለዉጡ ይሄ ነው እንዴ?

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን ዛሬ አስመርቀ ! ለዉጡ ይሄ ነው እንዴ?

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ ማሰልጠኛ ማእከል ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን ዛሬ ከፍተኛ የመንግስት
ባለስልጣናት በተገኙበት እንደሚያስመርቅ የክልሉን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Biniam Shemelis ሌሎችም ክልሎች ከዚህ ልምድ በመውሰድ አቅማቸውን በማጠናከር የህዝባቸውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ይገባል ።
ለኢትዮጵያ ግን የሚጠቅመው አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ ነበር።ነገር ግን የአንድን አካባቢ ልዩ ሀይል እያጠናከሩ የሌላውን ልዩ ሀይል ማዳከም ነውር ነው።የእራስን ልዩ ሀይል እያጠናከሩ የሌሎችንም ልዩ ሀይሎች እንዲጠናከሩ ማድረግ እኩልነት ነው። ለማንኛችንም ግን አንድ ወጥ የሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ብቻ ነው የሚጠቅመን።
አለበለዚያ ወረቀት ላይ ባይሰፍርም ተለያይተናል ማለት ነው።

Agegn Bizuneh AB በለው በለው!!!
ይህ ሁሉ ፖሊስ የሚሰለጥነው አገርን ከወራሪ ሀይል ለመከላከል ሳይሆን መከረኛውን አማራ በቄሮ ስም ለማሰቃየትና ይችን መከረኛ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለማወክ ነው።

Teshome Nigussie  የአማራን ልዩ ሃይል ለማጥፋት ቀን ከለሊት እየሰሩ ይገኛሉ ። የወቅቱ ባለተራ የኦሮሚያ መንግሥት ለ30 ጊዜ ልዩ ሃይል @# በኢትዮጵያውያን ህዝብ ሃብት በማን አለብኝነት እያሰለጠነ ይገኛል ። #አማራ ግን አንድ ጊዜ ሲያሰለጥን #አብይ ደሴ ላይ የተናገረውን ማስታወስ በቂነው። @#ለውጥ የለም ተረችነት ነው ያለው የሚባለው ለዚህ ነው ነገሩ ግን ከተረኝነትም ያለ የእብሪት አካሄደ ነው። በእርግጥኛነት እንኳን ለ30 ጊዜ #ለ300 ጊዜም ቢያሰለጥን #በአማራም ሆነ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ አይኖርም ።

Tafarii Bantii Haile ይህ ሁሉ ፖሊስ እየሰለጠነ ያለው የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ሳይሆን የብልጥግናን ወንበር ለመጠበቅ ነው፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ የህዝቡ የሰላም ዋስትና መሆኑ ቀርቶ በህዝቡ ዘንድ ስጋት እየሆነ መጥቷል፡፡ ከፓርቲ አልፎ የግለሰቦች የግል ቂም መወጣጫ እየሆነም ነው፡፡ ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ግለሰቦች በግል የተጣሉትን ሰው ያስደበድባሉ ያሳስራሉ፡፡ ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበታቸው እስረኞች በእነዚህ ሰዎች ትዕዛር ፖሊስ አደራ ተሰጥቶናል በሚል በእስር ያቆያል፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ዕቃ ብቻ ሳይሆን ሰውም በአደራ እስር ቤት ውስጥ ይቀመጣል፡፡ ይህ ሁሉ ወታደር እየሰለጠነ ኦሮሚያ ውስጥ ህግ የለም ሰላም የለም፡፡ ህጉ እየተጣሰ ያለው ደግሞ በህዝቡ ሳይሆን ህግን አስከብራለሁ በሚል አካል ነው፡፡

Mary Hailu #ሌላው ክልል ሲያስመርቅ አላየንም 😕😕
ነው ወይስ #ማሰልጠንም_ማስመረቅም የሚችለው #ባለጊዜው ብቻ ነው??

Des-A’legn Alemu አማራ ክልል ለ2ኛ ጊዜ አስመረቀ ተብሎ ወሎ ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ በጀታችሁን ለሚሊሻ ማሰልጠኛ ነው የምታዉሉት ብሎ እነ ብ/ጄኔራል አሳምነውን መድረክ ላይ አሸማቀቀ፡፡ ኦሮሚያ ክልል ለ30ኛ ጊዜ አሰልጥኖ ሲያስመርቅ ምንም አልተባለም ግልፅ ተረኝነት እንዳለ ማሳያ ነው፡፡!

Thomas Jejaw Molla
ኦሮሚያ ራሷን ችላ እንደ ሉዓላዊ ሀገር ለመቆም እየገሰገሰች ነው ። ለ 30ኛ ጊዜ ያሰለጠኑትን ልዩ ሃይል አስመርቀዋል ። አማራ አይደለም ያደረገውና ጆሮ የሰጠው የለም ። ብአዴን በተቃራኒው ፋኖን ካላጠፋሁ ሞቼ እገኛለሁ እያለ ነው ።

 

Check Also

ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል (FANO) የተሰጠ መግለጫ!!

ቢዘገይም ፍላጎታችንና መሆን ያለበት እየሆነ ነው እናመሰግናለን ጀግኖቻችን ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል የተሰጠ መግለጫ!! ××××××××××××××××××××××××××× የአማራ …

የአማራ ፋኖ (የአማራ ህዝባዊ ኃይል ) በአዲስ መንፈስ ተቋቋመ!

Related Posts:የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ውይይቶች በ4 የአውሮፖ ከተሞችበአዲስ አበባ ጉዳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን(አብን) አቋም …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.