Breaking News
Home / News / የአጤ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች::

የአጤ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች::

አጤ ቴዎድሮስ በመሳፍንቶች አስተዳደር ተበጣጥቃ የነበረችውን ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ መሰረቱን በመጣላቸውና ከእንግሊዝ ጋር ባደረጉት ጦርነት እጃቸውን አልሰጥም ብለው ሽጉጣቸውን በመጠጣታቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ደጋግሞ ይነሳል፡፡ ስለ እኚህ መሪ ልጆችና የልጅ ልጆች ግን ምንም ሰምተን አናውቅም። ጎንደር ሄደን፣ የተወሰኑትን አግኝተናል።https://bbc.in/2ZgVTn4

Posted by BBC News Amharic on Thursday, April 18, 2019

አጤ ቴዎድሮስ “መይሳው ካሳ” እያሉ ይፎክሩ ነበር አሉ። ጠላታቸውን ጥለው ሲሸልሉ “መይሳው ካሳ፣ አንድ ለናቱ ሺ ለጠላቱ” ብለው ይፎክሩ እንደነበር ይነገራል።

ዘመናዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ጥረት ያደረጉት አጤ ቴዎድሮስ፣ ያለሙትን ለውጥ ለማምጣት ሳይሳካላቸው ከሀገር ውስጥና ውጪ በተቀሰቀሰባቸው ተቃውሞ ምክንያት የእንግሊዝ ጦርን ተፋልመው በሚያዚያ ወር 1860 መቅደላ አምባ ላይ እራሳቸውን ሰዉ።

በመቅደላ ጦርነት ወቅት ለእንግሊዞች እጅ አልሰጥም ብለው ራሳቸውን ያጠፉት የአፄ ቴዎድሮስን ቁንዳላም ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው በቅርቡ ነው።

አጤ ቴዎድሮስ በጀግንነት እና በሀገር አንድነት ያልተነሱበት የኢትዮጵያ ጫፍ ያለ አይመስልም። ቴዎድሮስ “አጤ” ከመባላቸው በፊት ስማቸው ካሣ ኃይሉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ አጤ ቴዎድሮስ የተባሉት የሰሜኑን ገዥ ደጃዝማች ውቤን፤ ደረስጌ ላይ ድል አድርገው ዘውድ ከጫኑ በኋላ ነው።

• የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ሊመለስ ነው

• ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?

አጤ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሥነ ጽሑፉ ዓለም ውስጥም ስማቸው ገናና ነው። በልቦለድ ሥራዎች ውስጥ እንፈልጋቸው ብንል የብርሃኑ ዘሪሁን የቴዎድሮስ እንባ፣ የአቤ ጉበኛ አንድ ለናቱን እናገኛለን፣ በተውኔት ደግሞ የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን አጤ ቴዎድሮስና የጌትነት እንየው የቴዎድሮስ ራዕይን መጥቀስ እንችላለን።

ስማቸው በዘፈን ያልተነሳበት፣ ያልተወሳበትም ዘመን የለም። ኢትዮጵያን ያነሳ፣ ጎንደርን የጠቀሰ ስለ አጤው ያዜማል።

ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር፤

ለአንት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የሚለው የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የቅርብ ጊዜ ዜማን ማስታወስ በቂ ነው።

አጤ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ከእንግሊዝ አገር ከመጡ 32 ሺህ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቷ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እንደተፈፀመ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ።

የእንግሊዝ ወታደሮች የዘረፉት መጻሕፍትን፣ የተለያዩ ከወርቅ የተሠሩ ቅርሶችን፣ መንፈሳዊ ሥዕሎችን፣ ታቦታትን፣ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶችን ብቻ ሳይሆን ልጃቸው አለማየሁ ቴዎድሮስንም ጭምር ነው።

አለማየሁ በሰው ሀገር በብቸኝነት፣ በለጋ እድሜው መሞቱና እዚያው መቀበሩ ይታወቃል። ሌሎች የአጤው ዘመዶችስ? የት ናቸው?

Check Also

Look at Abiy Administration’s Dictatorship !

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ከእስርቤት ከተፈቱ ስድስት ወር ሊሞላቸው ነው መንግስት ግን እስካሁኗ ደቂቃ የባንክ አካውንታቸውን …

አዲስ አበባ ተቦርቡረሽ አልቀሻል!

  በተሻሻለው የወንጀል ስነ-ስርዓት ህግ አንቀፅ 25 መሰረት ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የመወሰን ስልጣን …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.