Breaking News
Home / Amharic / የአዳነች አቤቤ መልእክት!

የአዳነች አቤቤ መልእክት!

እነ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ሊያጭበረብሩን ፈልገው ወይስ ሒሳብ የማይችሉ ሆነው???

ወ/ሮ አዳነች ትናንትና በከተማው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከቤተክርስቲያን ይዞታ ውዝግብ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ከመሬት ጋር ተያይዞ ለሚነሣው ጥያቄ ሁሉም የእምነት ተቋማት በጋራ የፈረሙበት ባለፉት ሦስት ዓመታት 2014ን ሳይጨምር በመሥተዳድሩ የተሰጡ ቦታዎችን በተመለከተ፡-
• ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ 89 ቦታዎች እና በአራት ኪሎ የሚገኘውን ባለመንትያ ሕንፃ ማስመለስን ጨምሮ ሰጥተናል፡፡ ይህም በካሬ ሜትር ከአንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ነው፡፡
• ለእስልምና እምነት ተከታዮች 85 ቦታዎች 260ሺህ 968 ካሬሜትር፡፡
• ለወንጌላውያን አማኞች በጠቅላላ 47 ቦታዎች 98ሺህ 290 ካሬ ሜትር፡፡
• ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ሦስት ቦታዎች 700 ካሬ ሜትር
• ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ሦስት ቦታዎች 6ሺህ 812 ካሬ ሜትር፡፡
በጠቅላላ በተቋም ደረጃ ሁሉም የእምነት ተወካዮች ሁለት ወር ሙሉ ተወያይተው ባጸደቁበት መልኩ ማስተላለፍ ችለናል፡፡
ይህንን ማድረግ የቻለ ከዚህ በፊት አልነበረም!” በማለት “የሚበቃውን ያህል የመሬት ጥያቄ ስላስተናገድን ሌላ ተጨማሪ የቦታ ወይም የይዞታ ጥያቄ አናስተናግድም እንወርሰዋለን እንጅ!” የሚል እንድምታ ያለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አንዳንድ ፀረ ቤተክርስቲያን ግለሰቦችና ቡድኖችም “ወ/ሮ አዳነች የተናገሩት ትክክል ነው ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጣም ብዙ መሬት ነው የተሰጣቸው!” እያሉ ይገኛሉ!!!

እኔ የምለው እነ ወ/ሮ አዳነችም ሆኑ ፀረ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግለሰቦችና ቡድኖች projectionኑን እንዴት አድርገው ሠርተውት ነው በዚህ ባስቀመጡት ዳታ ኦርቶዶክስ የበለጠ ተጠቃሚ የሆነችና ሌላ የመሬት ይገባኛል ወይም የይዞታየ ይጽደቅልኝ ጥያቄያችንን ተገቢ ያልሆነ አስመስለው ሊነግሩን የፈለጉት???

projectionኑን ተሰጣቸው ተብሎ ከተገለጸው ሜትር ካሬ አኳያ ካሰላነው ደግሞ ለእስልምና 260ሽህ 968 ሜትር ካሬ ከተሰጠና ኦርቶዶክስም አስተዋጽኦዋ ወይም አበርክቶዋ ውለታዋ ምኗ ሁሉ ነገሯ ግምት ውስጥ ሳይገባ “ከእስልምና ጋር በንጽጽር ዕኩል ቦታ ብቻ ይሰጣት!” ከተባለ ኦርቶዶክስ ሊሰጣት የሚገባው ቦታ 1,206 ሽህ 977 ሜትር ካሬ ነው፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክስ ከእስልምና ለመድረስ ገና 206 ሽህ 977 ሜትር ካሬ ቦታ ይቀራታል ማለት ነው!!!

ያቀረቡት ዳታ 74.7% በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ ኦርቶዶክስ በሆነባት ከተማ የኦርቶዶክስ ይዞታ እጅግ አነስተኛ መሆኑንና ከሌሎቹ በእጅጉ ያነሰ መሆኑን ቢያውቁ ሰዎቹ ምን ይሉ ይሆን??? የቤተክርስቲያን አሥተዳዳሪዎች የቤተክርስቲያንን ውለታ እና ፍጹም የማይተካ አበርክቶዋን የረሱ ደርግ እና ወያኔ የተባሉ ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዞች ይመጣሉ ብለው ስላልሠጉና ቤተክርስቲያን እንዲህ ዓይነት ፈተና ይገጥማታል ብለው ስላላሰቡ ነው እንጅ ይሄ ቢታወቅማ ኖሮ በቀደመው ዘመን ለየ አብያተክርስቲያናቱ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እያወጡ ይይዙ አልነበረም ወይ???

ለነገሩ ይሄ ክፉ ቀን እንደሚመጣ የተረዱ ብልህ የሆኑ የአንዳንድ አብያተክርስቲያናት አሥተዳዳሪዎች በቀደመው ጊዜ ያወጡትን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የዘመናችን ባለሥልጣናት እያመከኑ “መክኗል!” እያሉ አይደለም እንዴ ይዞታዎቻችንን እየነጠቁን ያሉት??? ሕግ በሌለበትና ወንበዴ ሥልጣን በያዘበት ሀገር ፍትሕ የት አለና!!!

እንኳንና የጠቀሱት ዳታ ይዞታችን አነስተኛ መሆኑን እያረጋገጠ ይቅርና አንድ አካል ስንት ደክሞ ያገኘውንና ለብዙ መቶ ዓመታት ያለማውን ይዞታ “እንነጥቅሃለን!” በማለት በግፍ መንጠቅ እንዴት ነው ፍትሐዊ አሠራር የሚሆነው??? መቸም አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ዋጋው የሚከፈለው በሠራው ሥራ፣ ባበረከተው አበርክቶ ነውና እንዲህ እንተሳሰብ ከተባለማ እንግዲያውስ የእምነት ተቋማቱ ለሀገር ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሥልጣኔ ወዘተረፈ. ባበረከቱት ልክ እየተመዘኑ ይከፈላቸዋ እንግዳው???

እራሳቸውን ለቅኝ ገዥ ምዕራባውያንና ለወራሪ ዓረቦች ቀጥረው ሀገር ሲያጠፉና ሲያወድሙ፣ ሉዓላዊነታችንን ሲያስደፍሩ፣ በጠላት ሲያስወርሩ ወዘተረፈ. ሲያደርጉ ከኖሩ የእምነት ተቋማት ጋር ዕድሜ ዘመኗን ለዚህች ሀገር ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሥልጣኔ ወዘተረፈ. ስትማስን ከኖረች ቤተክርስቲያን ጋር ማፎካከር በእጅጉ ሚዛን ከመሳትም በላይ የጠላት ቅጥረኝነት አይደለም ወይ??? ዕኩልነት ማለት የሠራን ካጠፋ ጋር ዕኩል መክፈል ማለት የሚሆነው በየትኛው ሕግ በየትኛው አመክንዮ ነው???

ከዚህ ቀደም አንድ ዳታ ሠርቸ አሳይቸ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ሕዝብ፦

* 74.7% የሚሆነው ሕዝብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ነው፡፡

* 16.2% የእስልምና ተከታይ ነው፡፡

* 7.7% የፕሮቴስታንት ተከታይ ነው፡፡

* 0.4% የካቶሊክ ተካታይ ነው፡፡

እግዚአብሔር ያሳያቹህ ለ74.7% ለሆነ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ያለው የአብያተክርስቲያናት ብዛት ጥቂት ማለትም 16.2% ከሆነው የእስልምና ተከታዮች ካላቸው የመስጊዶች ብዛት በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ 171 መስጊዶች ሲኖሩ 131 አብያተክርስቲያናት አሉ፡፡ በየደጁ ያለውን የፕቴስታንት አዳራሾችን ቁጥር ብዛትማ ስታዩ “በዚህች ሀገር ምን እየተኪያሔደ ነው ያለው???” ብላቹህ እራሳቹህን በአንክሮ ሳትጠይቁ አትቀሩም!!!

አሁን ባለው የአምልኮ ስፍራ ይዞታን አማካይ ስንመለከት ለአራት ሽህ እስላሞች አንድ መስጊድ ሲኖራቸው ለኦርቶዶክስ ግን አንድ ቤተክርስቲያን ለ27 ሺህ ምእመናን ነው ያለን። የልዩነት እርቀቱን ልብ በሉ 4ሽህ ለ27ሽህ ነው!!!

የኦርቶዶክስ ምእመናን ከእስልምና ተከታዮች ለመድረስ አገዛዙ አዲስ አበባ ላሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ከ470 አብያተክርስቲያናት በላይ የመሥሪያ ቦታ የማቅረብ ግዴታ አለበት ማለት ነው፡፡ እነሱ ግን ይሄም ሳይበቃቸው የመስቀል አደባባይንና ጃን ሜዳ ጥምቀተ ባሕርን ጨምሮ አሁንም ድረስ የእኛን ይዞታዎች እየነጠቁ ለመውሰድ ያምራቸዋል!!! አገዛዙ ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ሰይጣናዊ የቅጥረኝነት ተልእኮና ዓላማ ስላለው ነው እንጅ እውነቱ ጠፍቶት አይደለም!!! መረጃው ያለው በእጃቸው ነውና!!!

ሞኝ ምእመናንና ቤተክርስቲያንን የሚያስበሉ ምንደኛ “እረኞች ነን!” ባዮች ሲያገኙ እነሱ ምን ያድርጉ ብላቹህ ነው በእነሱ ይፈረዳል ብላቹህ ነው???

ፀሐፊው :- ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

Check Also

ኤርትራ ከአማራ ህዝብ ጋር መቆሟን አስታወቀች !

Related Posts:የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ የነበረው ችግር እንደተፈታ አስታወቀች::ኤርትራ ለአማራ ልዩ ኃይል እና …

ጥቁር ጣልያን በአዲስ አበባ። ለታሪክ አስቀምጡት። ሼር

Related Posts:የመሬት ዝርፊያ በአዲስ አበባ !የኦሮሞ ባንዲራ በአዲስ አበባ !በአዲስ አበባ የሚሰራዉን ተንኮል ተመልከቱና ፍረዱ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.