Breaking News
Home / Amharic / የአብይ አህመድ አማካሪው ቄስ ዳንኤል ክብረት የሚያሳዝን ንግግር

የአብይ አህመድ አማካሪው ቄስ ዳንኤል ክብረት የሚያሳዝን ንግግር

የዲያቆኑ ሰይጣናዊ የጥላቻ ንግግር የሚወገዝና የሚኮነን ነው #ግርማካሳ
አንዳንድ ወገኖች ስለ ዳንኤል ክብረት ምነው ዝም አልክ ብለው ጠይቀዉኛል፡፡ እስክሰማው ነበር፡፡ አንዲት እህት ክሊፑን ላከችልኝና ሰማሁት፡፡ የሰማሁት ነገር በጣም የሚገርም፣ የሚያሳዝን የሚያሳፍርም ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ ለማመን የሚከብድ፡፡
ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንደሚባለው ዲያቆኑ ካቲካላ ለግቶ ይሆን የተናገረው ብዬ አስብኩ፡፡ ይህ ንግግሩ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚያስጠየቀው፣ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ንግግር ነው፡፡
1ኛ የዲያቆኑ ንግግር፣ የርሱን አባባል ልጥቀስና የ”ጭራቅ” ንግግር ነው:: ከዲያቆን፣ ቤተ ክርስቲያንን አገለግላለሁ ከሚል ሰው የሚጠበቅ አይደለም:፡፡ ዲያቆን ፣ ፍቅርን የሚሰብክ፣ የሚያስታርቅ የሚፀልይ እንጂ እርግማንን እንደ አጋንንት ጠሪ ጠንቋይ የሚረጭ አይደለም::
2ኛ ንግግሩ እፍራሽ፣ ጥላቻን ያዘለ ንግግር ነው፡፡ ህወሃትን የሚጠቅም ለህወሃት ደጋፊዎች ለፕሮፖጋዳቸው ፍጆታ የሚጠቅም ነው:፡፡ ህወሃትን ለማሸነፍ የትግራይን ህዝብ መያዝና ከጎናችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የዲይቆኑ ንግግር ግን የትግራይን ህዝብ የሚያስቀይም፣ ልዩነትንን መካረሩን የበለጠ የሚያሰፋ ነው፣ ጥላቻና ቂም በቀልን የሚያበረታታ ንግግር ነው፡፡
3ኛ ይህ ሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣን ነው:: አንድ የመንግስት ሃላፊ የነገውን ትውልድ ማሰብ አለበት:: የዲያቆኑ ንግግር ግን የነገውን ትውልድ ያሰበ ንግግር አይደለም::
በኔ እይታ አንደኛ ዲያቆኑ ለትግራይ ሕዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡ ሁለተኛ ከያዘው የመንግስት ሃላፊነት፣ ተመርጬበታለሁ ካለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መልቀቅ አለበት፡፡ አለቅም ካለም መንግስት ሊያባረረው ይገባል፡፡ እርሱ የመንግስት ሃላፊነት ይዞ መቀጠሉ በመንግስት ላይ ተጨማሪ ጣጣ የሚያመጣ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያንን ለተወሰነ ጊዜ አገልግሎት እንዳይሰጥ መታገድ አለበት፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሄዶ፣ ንስሃ ገብቶ፣ ራሱን በመመርመር ሱባኤ ይግባ፡፡
(ዲያቆኑ የተናገረው ጸያፍ በመሆኑ እዚህ ላጋራው አልፈለግም)

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.