Breaking News
Home / Amharic / የአብይ መንግስት የፖለቲካ አሻጥር!

የአብይ መንግስት የፖለቲካ አሻጥር!

የነአብይ መንግስት የፖለቲካ አሻጥር!

By Eshete Assefa

——

የዶክተር አብይን መንግስት ከጂምሩ ከሁሉም የበለጠ አስፈርቶት የነበረው የአማራው ብሔርተኝነት ነበር። ነገር ግን ይህን ብሔርተኝነት የአማራ መሪወችን በፖለቲካ ሴራ እንዲወገዱ ከተደረገ በኋላ ለትንሽ ግዜም ለማለዘብ ተችሎ ነበር። ከመሪወች ሞት በኋላ የአማራ አደራረጀቶች በተፈለገው መንገድ እንዲሄድ አልተቻለም። የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚኒሻ እና ፍኖ ላይ ሆን ተብለው አሉባልታዎች ተነዙ፣ ልዩ ሀይሉም እስከመፍረስ ደርሶ ነበር። ይህ የሆነው አማራው ጠንክሮ እንዳይወጣ ስለተፈለገ ነበር።
ነገር ግን የአብይ አህመድ መንግስት በትህነግ ምክኒያት የህልውና አደጋ ውስጥ ሲገባ የአማራ ህዝብ በህወሓት ላይ የነበረውን ጥላቻ ተጠቅሞ አማራውን በህወሓት ላይ እንዲዘመት አደረገ፤ ትንሽ ሳይቆይ የአብይ መንግስት ከህወሃት ሊደርስበት የነበረውን አደጋ በአጭር ግዜ አስወገደ፤ እፎይታም አገኘ። ነገር ግን አብይ አህመድ መንግስት ከሚያራምዱት የተረኝነት ፖለቲካ አንፃር አሁንም የአማራው ህዝብ በለቲካውም፣ በኢኮኖሚ ጠንክሮ መውጣት ከህወሓት የበለጠ ያሳስበዋል።
ስለዚህ የአብይ መንግስህ ህወሃት ሙሉ ለሙሉ እንዲጠፍ አልፈለግም ምክኒያቱም ለአማራው ብሔርተኝነት ማስተፈሻ ይሆናል ብለው ስለሚያስቡ።
መከላከያ ትግራይ ውስጥ 8 ወር ሙሉ ሲቀመጥ ህወሃትን ሙሉ ለሙሉ ሽባ አድርጎ መውጣት ይችል ነበር። ነገር ግን ሲደረግ የነበረው በተቃራኒው ነው፣ ህወሓት ሙሉ ትጥቁን እንደያዘ፣ እስከሙሉ ወኔው ጥለውት ወጡ።
አሁን በአብይ በመንግስት እቅድ እና ሴራ ምክኒያት ጦርነቱ አማራ ክልል እንዲደረግ ተፈለገ፣ ከአማራ ክልልም ለአብይ መንግስት ህልውና ስጋት የማይሆንበት ቦታ። ራያ አላማጣ፣ ቆቦ፣ ላሊበላ፣ ወለዲያ የፈለገ አማራ ቢፈናቀል፣ ቢሞት ለምንግስት ህልውና አደጋ እስካልሆነ ድረስ አላማው አማራውን በጦርነት እስካዳከሙለት ድረስ አሁንም ይህ የሴራ ፖለቲካ ይቀጥላል።
ህወሃት ከእነዚህ የአማራ ግዛቶች አልፎ ለፌዴራሉ መንግስት አደጋ እንደማይሆን የአብይ መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል። እንዲውም ከሰሜን ወሎ ወደ ደቡብ ወሎ ደሴ፣ ኮምቦልቻ የጂቡቲ መስመር እስካልተዘጋ ድረስ በምእራብም በኩልም አደርቃይ፣ ዳባርቅ፣ ዳባት፣ ጎንደር በወልቃይት መተማ ህወሃት ከሱዳን ወይም ግብፅ ጋር ተገናይቶ እስካልተጠናከረ ድረስ የህወሓት ሀይል ገብቶ አማራን እስካዳከመለት ድረስ የአብይ መንግስት ደስስታውን አይችለውም፤ እቅዳቸውም ነው።
ነገር ግን ህወሃት ሀይል አግቶ የአብይን መንግስት ፈተና ውስጥ ይጥላሉ ተብለው የታሰቡት የአፋር (የጂቡቲ መስመር) እና የወልቃይት ሰዳን ኮሪደር መከላከያ በሙሉ አቅሙ ሲዋጋ አይተናል። ህወሃትንም ሲደመስስ አይተናል፣ ሰምተናል። ነገር ግን ከላይ በተጠቀሱት የአማራ ግዛቶች መከላከያ እንኳን በሙሉ አቅሙ ሊዋጋ ቀርቶ ትላልቅ እና ከባድ መሳሪያዎች ለህወሓት ሀይል አስረክቦ ስወጣ አሁንም አይተናል፣ ሰምተናል። ይህ ያደረጉበት ምከንያት ደግሞ አንድም ህወሃት ባካባቢው ጠንክሮ እንዲወጣ ሁለትም የአማራ ልዩ ሀይል አቅመቢስ ለማድረግ ታስቦ ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ አማራ ህዝብ በእራሱ ሀይል እራሱን እንዳይከላከል እየተደረገ ነው። የአማራ ልዩ ሀይል ከህወሀት ሀይሎች አንሶ አይደለም። ነገር ግን በሙሉ አቅሙ እንዳይዋጋ እያደረጉት ነው። የአማራ ልዩ ሀይል ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ስር ተቀፍድዶ ተይዟል። የአማራ ልዩ ሀይል እንደ ህወሃትቶች እንደፈለጉት መከላከልም ሆነ ማጥቃት አይችልም። ብዙ ልዩ ሀይሎች እንደሚሉት ህወሃት ሀይሎች እንደፈለጉ ሲጨፍሩብን ቆይተው እኛ ማጥቃት ስንጀምር በትዛዝ ወደኋላ እንድናፈገፍግ ይደረጋል። ለምን ብለን ስንጠይቅ ከላይ የመጣ ትዛዝ ነው ይሉናል ብለዋል።
 

Check Also

የአማራ ሀይልና መከላከያ ከወልቃይት እንዲወጡ በአቢይ አህመድ ትእዛዝ ተሰጠ።

——————–#ወልቃይትን__እናድን—-———– የኦህዴዱ አብይ አህመድ ክህደት በወልቃይት ላይ #ግርማካሳ በርካታ ሜዲያዎች እየዘገቡት ነው፡፡ የአማራ ክልልና የአማራ …

ለአማራ ሕዝብ የቀረበ ጥሪ – Please share

Related Posts:አስቸኳይ ስብሰባ ለአማራ ሕዝብ ! Please shareመልዕክት ለአማራ ሕዝብ - አማራ የሆናችሁ ምንድነው የምትጠብቁት …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.