Breaking News
Home / Amharic / የአሜሪካ ኮንግሬስ ዉሳኔ: (resolution 97) ወደ አማርኛ ተተረጎመ::

የአሜሪካ ኮንግሬስ ዉሳኔ: (resolution 97) ወደ አማርኛ ተተረጎመ::

የአንድ መቶ አስራ ሰባተኛው ኮንግረስ የሴኔቱ ውሳኔ 97 እንደሚከተለው ነው።

1. የኢትዮጵያ ክፍለ ግዛት በሆነው ትግራይ የሚደረገው የጦርነት እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም ይጠይቃል
2. በሲቪል ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በጽኑ ያወግዛል
3. የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ያሉ ወታደሮቹን በአስቸኳይና በሙሉ እንዲያስወጣ እንጠይቃለን። የደረሰውን የሰብዐዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ፣ ዘረፋ፣ አስገድዶ መድፈርን እና ሌሎችንም በኤርትራ ወታደሮችም ይሁን ሌሎች ሃይሎች በትግራይ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን በጽኑ እናወግዛለን
4. በኢትዮጵያ መንግስትና በህወአት መካከል የተፈጠሩት ፖለቲካዊ አለመግባባቶች ወደ ወታደራዊ ግጭት ማደጋቸውን በጽኑ እንቃወማለን
5. የኤሌክትሪክ፣ የባንክ፣ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በትግራይና በሌሎች አገልግሎቶቹ በተቋረጠባቸው ቦታዎች ሁሉ ተመልሰው አገልግሎት እንዲጀምሩ እንጠይቃለን
6. ከሃገራቸው ሸሽተው በሱዳን የተጠለሉ ስደተኞችን ለመቀበል ፍቃደኝነትን በማሳየቷ ሱዳንን እናደንቃለን
7. የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ የሚከተሉትን እንዲያደርግ እናሳስባለን
ሀ) ለአለም አቀፉ የምግብ ድርጅትና ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን በተገባው ቃል መሰረት የዜጎችን ተደራሽነት የሚያሻሽሉ ተጨባጭ እርምጃዎች እንዲወሰዱ
ለ) ለተፈጸሙ የሰብዐዊ መብት ጥሰቶችና አሰቃቂ ጥቃቶች ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ እና
ሐ ከሴናተር ኩንስ ጉብኝት በኋላ የተስተዋሉ በትግራይ ክፍለ ግዛት ያለውን ግጭትና የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋትን በሚያውኩ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ መሻሻሎች እንዲታዩ
8. የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን
ሀ) የህወአት አባላት ሲታሰሩ በተቻለ መጠን አነስተኛ ኃይልን በመጠቀም እንዲሆንና የተያዙትም የኢትዮጵያና አለም አቀፉ ህግ በሚፈቅደው መሰረት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው
ለ) የኤርትራ ሃይሎች ወዲያውኑና በሙሉ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ እንዲደረግ
ሐ) በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውና አመለካከታቸው ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት፣ ደጋፊዎች፣ አክቲቪስቶች እንዲሁም በሪፖርት አቀራረባቸው የተነሳ የታሰሩ ጋዜጠኞች በሙሉ እንዲፈቱና የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃሳብን በነጻ የመግለጽና ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸውም በብሄር፣ በርእዮትና በፖለቲካ ቡድንተኝነት እንዲከበር እና
መ) ተዓማኒነት ያለውና ሃገር አቀፍ የሆነ ብሄራዊ የእርቅና የመግባባት እንቅስቃሴ ሰላማዊ የሆኑ ፓርቲዎችን፣ ብሄረሰቦችን፣ የሃይማኖት ቡድኖችንና ሲቪል ማህበረሰቦችን ባካተተ መልኩ ቅሬታዎችን በቀጣይነት ለመፍታትና ለሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ አቅጣጫ ለመተለም የሚያግዝ አሰራር እንዲኖር
9. በግጭት ላይ ያሉ ወገኖችንም:-
ሀ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ያላቸውን ልዩነት ፖለቲካዊ መፍትሔዎች እንዲፈልጉላቸው፣ አለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲያከብሩ፤ ግጭቶችን ከሚቀጥሉ፣ ከሚያባብሱ፣ በተለይ ደግሞ ሲቪል ሰዎችን ኢላማ ከሚያደርጉ ጥቃቶች እንዲቆጠቡ
ለ) እርዳታ የሚሰጥባቸውን አካባቢዎች ያለምንም ገደብ በአስቸኳይ ተደራሽ ለማድረግ ተጨባጭና የሚታዩ መሻሻሎችን እንዲያደርጉ፣ እርዳታ ሰራተኞችና አቅርቦቶቻቸው፣ የተጎዱ አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ እንዲሁም ሲቪል የሆኑ ሰዎችን ደህነነት፣ የስደተኞች፣ ለተፈናቃዮች፣ እንዲሁም የእርዳታ ሰራተኞች ደህነንት እንዲጠበቅ እና
ሐ) በነበረው ግጭት ምክንያት በትግራይ ክልልና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልልሎች ለደረሰው የሰብአዊ መብት መጣስ ነጻና ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድና አጥፊዎች ተለይተው ቅጣት የሚያገኙበት ተዐማኒነት ያለው አሰራር እንዲኖር እንዲፈቅዱና እንዲተባበሩ እና
10. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ፣ የአሜሪካ አለም አቀፍ ተራድኦ አስተዳዳሪ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኤጀንሲዎች ጋር በመሆን:-
ሀ) ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከኤርትራ መንግስት ጋር፣ ከህወአት ጋር ግጭቱን ለማቆምና የኤርትራ ሃይሎችን ለማስወጣት እንዲሰሩ፣ የደረሰውን ሰብዐዊ ቀውስ ለመግታትና ሁሉንም ያካተተ ብሄራዊ መግባባት እንዲደግፉ
ለ) የቆሙት ለኢትዮጵያ ይሰጡ የነበሩ ለህይወት አስፈላጊ ያልሆኑ እርዳታዎች የሚቀጥሉበትን መመዘኛዎች በአስቸኳይ እንዲያዘጋጁና ሰብዐዊ የሆኑ አስቸኳይ እርዳታዎች ለስደተኞችና ተፈናቃዮችንም ጨምሮ እንዲቀጥሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ በመላ ሃገሪቱም ግጭቶች እንዲወገዱና እርቅ እንዲኖር እንዲያግዙና ኢትዮጵያም ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንድታደርግ እንዲረዱ
ሐ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን በየካቲት ፪፯ ፳፪፩ እንደተጠየቀው በሁሉም የሰብዐዊ መብት ጥሰቶችና የጭካኔ ተግባራት ሪፖርቶች ላይ የተሟላ፣ ነጻና አለምዐቀፍ ምርመራ እንዲደረግባቸውና ለጥፋቶቹ ኃላፊነት ባለባቸው ላይ የተጠያቂነት እርምጃ መወሰዱ እንዲረጋገጥ ተከታታይ እርምጃዎችን እንዲወስዱ
መ) ሁሉንም አይነት የዲፕሎማቲክ የልማትና ህጋዊ መንገዶችን በመጠቀም መንግስታዊ ባልሆኑ የታጠቁ ቡድኖች በቀጣይ የሚፈጽሟቸው ብሄር ተኮር ጥቃቶች እና የጭካኔ ተግባራትን እንዲከላከሉና ኢትዮጵያ መድበለ ፓርቲዎች የሚወዳደሩበት የዲሞክራሲ ስርአት እንዲኖራት እንዲያግዙ እና
ሠ) በትግራይና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላለው ግጭት መፍትሔ ለመፈለግ ከአለም አቀፍ አጋሮችና ከባለብዙወገን ድርጅቶች ጋር የቅርብ ትብብር እንዲያደርጉና ግጭቱ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ አለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ እንዲያደርጉ::
 
 

Check Also

አማራና ትግሬ ተስማሙና ኦሮሙማን መክቱ። – ሞጣ ቀራንዮ

https://fb.watch/f-ipLpwPrZ/ Related Posts:አማራና ኦሮሞ አትጣሉ። ተዋደዱ !አማራና ትግሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የኦሮሞ ክልል አስተዳደር …

ማስጠንቀቂያ ለከንቲባ አዳነች እቤቤ!

Related Posts:የጃዋር ሞሃመድ የዜግነት አወዛጋቢ ጉዳይ. ጃዋር ማስጠንቀቂያ ተሰጠው !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.