Breaking News
Home / Amharic / አቶ በለጠ ሞላ ከአብን ተወገዱ ! አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተደራጀ ።

አቶ በለጠ ሞላ ከአብን ተወገዱ ! አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተደራጀ ።

#ሰበር_ዜና!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)የማዕከላዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን በሚከተለው መልኩ እንደገና አደራጅቷል።
አዲሱ ሥራ አስፈፃሚም፦

👉 1) ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም – ሊቀመንበር

👉 2) አቶ ክርስቲያን ታደለ – ም/ሊቀመንበር እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ

👉 3) አቶ ደመወዝ ካሴ – የውጭ ጉዳዮችና ዓለማቀፍ ግንኙነት ኃላፊ

👉 4) አቶ ዘሪሁን ገሰሰ – የማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ

👉 5) አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም – የህግና ስነ–ምግባር ጉዳዮች ኃላፊ

👉 6) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

👉 7) አቶ ተሰማ ካሳ – የፖሊሲና ስትራቴጂ ኃላፊ

👉 8) አቶ ሀሳቡ ተስፋው – የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ጠቅላላ ጉባኤው ወስኗል።

የመንግስት የካቢኔ ስልጣን የተቀበሉትን ጠቅላላ ጉባኤው መርምሮ እስካሁን ለነበራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ አመስግኖ አሰናብቷቸዋል። በሌላ በኩል አቶ ጋሻው መርሻ የአማራን ህዝብ በመከፋፈሉ እና የድርጅቱን ደጋፊዎችን በእጅጉ ስለጎዳ ሕጋዊ እርምጃ ወስዶበታል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

👉 #ጋሻመልቲሚዲያ

Check Also

ጥያቄ ለብአዴን! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ??

ብአዴኖች እመኑኝ ብትሞቱ እንኳን አንተዋችሁም!!! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ?? እመኑኝ …

አብይ አህመድ ፋኖን ለማጥፋት መልክተኞች ወደ ጎንደር ልኳል !

Related Posts:ሰበር መረጃ - ጎንደር በመትረየስ እና በፈንጂ ስትታመስ አደረች - ለምን?በደቡብ ጎንደር ዞን ታስረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.