Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ መግለጫ!

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ መግለጫ!

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአቋም መግለጫ
*****
1ኛ / ትህነግ መሩ የሽብር ጥምረትና የዳግም ወረራ ስጋት፣
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለ27 ዓመታት በሐገራችን እና ህዝባችን ላይ ከቅኝ ግዛት አቻ የሆነ ስርዓት በመጫን ለአስከፊ ጭቆና እና ብዝበዛ ዳርጓት ኖሯል። ይህ አልበቃ ያለው ትህነግ በህዝብ ትግል ከተገፋ በኋላ ከማዕከላዊ መንግስቱ አፈንግጦ ትግራይ ውስጥ በመመሸግ ለጦርነት ሲዘጋጅ ወዲያው በጊዜው ርምጃ ባለመወሰዱ የተነሳ ሐገራችን ለከፍተኛ ኪሳራ፣ ህዝባችን ለእልቂትና ዘረፋ ሊጋለጡ ችለዋል። በተለይ የአፋር እና የአማራ ህዝቦች የወረራው ቀጥተኛ ተጋላጭ በመሆናቸው የብዙ ወገኖች ህይዎት እንዲቀጠፍ፣ ኃብት ንብረት እንዲወድም እና ከፍተኛ ማህበራዊ ምስቅልቅል ተፈጥሮባቸዋል።
የትህነግ ወረራና የመስፋፋት ዘመቻ በወገን ሀይሎች እልህ አስጨራሽ ርብርብ ከተገታ በኋላም እንደገና ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በአፋር ክልል በኪልበቲ ዞን ላይ ጥቃት በመክፈት አምስት ወረዳዎችንና አንድ የከተማ መስተዳድር ማለትም በአብአላ ከተማ አስተዳደር ላይ ወረራ መፈፀሙን የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አረጋግጣል። በተጨማሪ ወራሪው ሀይል ሰርዶን በመያዝ የኢትዮ ጂቡቲን መስመር ለመቆጣጠር፣ አፋርን መደራደሪያ ለማድረግና ካሁን በፊት ሚሌን ለመያዝ ያደረገውን ትግል በማጠናከር በራህሌና ኮነባን በቁጥጥሩ ስር እንዳዋለ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
በሌላ በኩል በአማራ ክልል በርካታ የራያ አካባቢውቸን ተቆጣጥሮ የሚግኝ ሲሆን በቆቦ እና ጠለምት አካባቢውችም ተመሳሳይ ወረራ እና መስፋፋት ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ከተለያዩ የራያ አካባቢወች በድጋሚ ተፈናቅለው በቆቦ የተጠለሉ ከ 50ሸህ በላይ ወገኖች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው ይገሉኛ፡፡
የአፋር ህዝብ በበኩሉ የህልውና ዘመቻው ከተጀመረበት እለት ጀምሮ በቀጥታ ወራሪውን ቡድን በጀግንነት በመመከትና ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ደጀን በመሆን ሐገራችንን ከመፍረስ መታደግ ያስቻለ ገድል ፈፅሟል። የአፋር ህዝብ የኢትዮጵያን አንድነት በመስዋእትነቱ ያፀና ለመሆኑ ባለፈው አንድ ዓመት ያሳየው ተጋድሎ አይነተኛ ምስክር ነው። የአፋር ህዝብ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ መፈናቀል እና ጦርነት ተዳርጎ ይገኛል።
ስለሆነም:-
ሀ/ መላዉ ኢትዮጵያውያን በአፋር በኩል ላለው ግጭት ትኩረት እንዲያደርጉ፣ ከአፋር ህዝብ ጎን እንዲቆሙ
ለ/ የፌድራሉ መንግስት ለአፋር ህዝብ አስፈላጊውን ትኩረት እንዲሰጥና እገዛ ዕንዲያደርግ
ሐ/ በራያና ጠለምት ህዝብ ላይ እየሆነ ያለው ድርብርብ ቀውስ አፋጣኝ መንግስታዊ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አጥብቀን እንጠይቃለን።
ትህነግ የተባለውን አሸባሪ ቡድንም ሙሉ በሙሉ መደምሰስ አማራጭ እንደሌለው አበክረን እናስገነዝባለን።
2ኛ / በኦሮሚያ ክልል በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው የሽብር፣ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀል፣
በኦሮሚያ ክልል በተለይ በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል እና ንብረት ማውደም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። አሸባሪው የሸኔ ቡድን በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ከሰሞኑ በፈፀማቸው ጭፍጨፋዎች በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች 81 ወገኖቻችን ተግድለዋል፣ እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎች በድምሩ168 ወገኖች መገደላቸው ተረጋግጣል። ወገኖቻችን ሐገራችን ብለው እየሰሩና ወልደው ከብደው በሚኖሩበት ቀዬ በተፈፀመ የዘር ተኮር ጥቃት ውድ ህይወታቸውን በግፍ ተነጥቀዋል።
ትህነግ መራሹን የአፈና ስርዓት በማስወገድና አንፃራዊ ለውጥ በመምጣት ረገድ ከፍተኛውን ድርሻ የተወጣው የአማራ ህዝብ በትግሉ ካመጣው የለውጥ ትሩፋት ሊቋደስ ቀርቶ ከመነሻው ጀምሮ ላልተቋረጡ ዘር ጭፍጨፋዎች፣ መፈናቀሎችና ዘረፋዎች ተዳርጓል። ህዝባችን በአምድ በኩል በከፋው የጥፋት ሀይል ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል በሚልና የወንጀልና የሴራ ጥምረቶችን ታሳቢ በማድረግ፣ ሌላው ችግር በሂደት ሊሻሻል ይችላል በሚል ግምት እና ለሐገር አንድነት ቅድሚያ በመስጠት ብሶቱን አምቆና ዝምታን መርጦ ከርሟል። ነገር ግን ጥቃቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ መጥቷል፣ ዘር ተኮር ጭፍጨፋው ፍፁም ሊያባራ አልቻለም። ስለሆነም እንደተለመደው ህዝቡ ጥቃቶችን እየተቀበለ ብቻ ይቀጥላል የሚል ግምት ስህተትና ተገቢነት የሌለው መሆኑን መረዳት ይገባል።
በዚህ ረገድ ወንጀሉ የሚፈፀመው በከፊሉ የመንግስት አመራር ደንታ ቢስነት እና በከፊሉ ቀጥተኛ ተሳትፎ የመሆኑ ጉዳይ ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ህዝባችን የሚያስፈልገው በህይወት የመኖር መብቱን የሚያስከብርለት ዝቅተኛ መንግስት (minimal state) እንጂ ነባራዊ ተጨባጭነት የሌለው መዋቅር እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባል።
የአማራ ህዝብ ፍላጎት በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በሰላምና በእኩልነት መኖር ብቻ ነው። ከዚህ የህዝባችን ፍላጎት በተቃራኒ ያለግብሩ ግብር እና ያለስሙ ስም በመስጠት በማምነቱ ለማሸማቀቅ፣ ለማጎሳቆል፣ ለመጨፍጨፍ እና በመጨረሻ እረፍትና እሴት አልባ ሆኖ እንዲጠፋ አቅደው በተግባር የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የሐገር አንድነት ጠንቅ መሆናቸው ታውቆ ፈጣንና አስተማማኝ ርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። በህዝባችን ላይ ጥቃቱን የፈፀሙ አካላት በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ እና ለተበዳዮች ካሳ እንዲከፈል ስንል እንጠይቃለን።

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.