Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ

የአማራ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ

የአክሲዮን ሽያጭ ቀን እንደገና ተራዘመ!

የአክሲዎን ሽያጭ ቀነ ገደቡ ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል።

የተከፈለው አክሲዎን ሽያጭ 3 ቢሊየን፥ የተፈረመ ደግሞ 4.1 ቢሊየን ሆኗል።

መራዘሙ ዲያስፖራው ዋና ተሳታፊ እንዲሆን መልካም አጋጣሚን ፈጥሮላቸዋል።

አማራ ባንክ የራሱ የሆነ በማህበራዊ ሚዲያ በስሙ የተከፈተ የማስታወቂያ ገፅ የለውም።

1) ጊዜ ገደብ፦

የምስረታ ሂደትና የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜ ገደብ እስከ የካቲት 30 እንዲራዘም ተወስኗል።

በርካታ ግለሰቦች፥ ዲያስፖራው፥ ባለሃብቱና አርሶአደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በበቂ ሁኔታ እንዳልተሳተፉ ስለታወቀና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲራዘምላቸው በጠየቁት መሠረት፥ የመሥራችነት ዕድል የሚያስገኘው የአክሲዎን ሽያጭ ለሁለት ወራት ተራዝሞ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በይፋ ይዘጋል።
ከ70,000 በላይ የሚሆኑ ባለአክሲዎን በግዥ ሂደት መሣተፍ፥ የዳታ ማጣራቱን እና ሂሳብ ማስተካከሉ ስራ፥ ሌላው በቂ ጊዜና ብቁ ባለሙያ የሚፈልግ ክንውን እንደሆነ አስተባባሪዎች አምነውበታል።

2) የአክሲዮን ሽያጭ መጠን፦

እስካሁን ድረሥ 3(ሶስት) ቢሊዮን ብር የተከፈለ እና ከ 4.1 ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል መድረሡን መረጃዎች ያመለክታሉ።

“አማራ ባንክ 5 ቢሊዮን የሚደርስ አክሲዮን ሸጦ ጠንካራ ተቋም በመሆን፥ በሃገር ልማትና አለማቀፋዊ አገልግሎት በመሥጠት ረገድ ጉልህ ሚና መጫዎት አለበት” ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ለ Amhara Economic Think Tank ገልፀዋል።

3) ዲያስፖራው፦

ዲያስፖራው አክሲዮን በመግዛት ተሳታፊ የሚሆንበት አግባብ ለማመቻቸት፥ መመሪያው ከብሄራዊ ባንክ እየተጠበቀ እንደሆነ ታውቋል። የብሄራዊ ባንክ መመሪያ(Directive) በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይደርሳል ተብሏል።

4) ቅጥር፦

የአማራ ባንክ ፕሮጀክት የሠራተኛ ቅጥር አላወጣም። የሰው ሃይል ቅጥር የሚጀምረው ባንኩ ከተቋቋመ በኋላ ይሆናል።

5) ማስታወቂያ፦

የአማራ ባንክ ፕሮጀክት የማስታወቂያ ክንውን በቂ እንዳልሆነና ተደራሽነቱም አነስተኛ በመሆኑ የመረጃ ክፍተት እንደታየ አስተያየት ሰጭዎች አቅርበዋል።

ባንኩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በራሱ ስም የተከፈተ የማስታወቂያ Platform የለውም። በስሙ የተከፈቱ ገፆች በግለሠቦች እጅ የተያዙ ናቸው።

ስለሆነም ተዛማጅ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውና በህዝብ ግንኙነት ስራ ባንክ ላይ ልምዱ ያላቸው፥ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዘርፍ ተጨማሪ ስልጠና የወሰዱ ሙያተኞችን በመቅጠር በቂ መረጃ ማሰራጨት ይቻል ነበር በማለት አስተያየት ሰጭዎች አመልክተዋል።

6) አክሲዮን የገዙ መሥራቾች ጥቅም፦

ይህ ጉዳይ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ቀርቦና ውይይት ተደርጎበት፥ የሃገሪቷን ንግድ ህግና የብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት አድርጎ በመመስረቻ ሰነዱ የሚፀድቅ እንጅ፥ አሁን ባለበት ደረጃ የሚወሰን አይሆንም።

7) የተጠቀሱ ስልኮች አይሰሩም፦

ከዚህ ቀደም የተጠቀሱ ስልኮችን መሥመራቸው አንዳንድ ጊዜ እንደማይገኝ፥ እንደማይነሱ ወይም እንደማይሰሩ ይጠየቃል።
ስልኮቹ ስራ ይበዛባቸዋል። ከዚህ ባለፈ፥ ከባንኩ አስተባባሪ አባላት መካከል ለስራ ጉዳይ ከሃገር መውጣታቸው ለባለፉት ሁለት ሳምንታት ክፍተቱ ተፈጥሮ ቆይቷል።
የአክሲዮን ሽያጭ መረጃ በ10 ባንኮችና በቅርንጫፎቻቸው ቀርቦ ማግኘት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ፥ የሚከተሉት ቁጥሮች አገልግሎት ላይ ናቸው።

0912001819/0911133014/0911248160/ 0941466607
Telegram, Vibr, and WhatsApp +251911600388

ጉርሻ!

Amhara Economic Think Tank ለህዝብ የሆኑ ምጣኔ ሃብታዊ ዋልታ ተቋማት እንዲመሰረቱ እገዛ በማድረግ እየሰራ ያለ የመማክርት ቡድን ነው።

መልካም ምሽት!

Check Also

Ethnic Terrorism Continues to Stalk Ethiopia.

JANUARY 20, 2023 BY GRAHAM PEEBLES FacebookTwitterRedditEmail   Where there is division there will be conflict. …

የዘውድ ስርአት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስተባበር ይችላል! (ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር))

የዘውድ ስርአት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስተባበር ይችላል!   ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር) ከአንድ አመት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የእርስበርስ ጦርነት፤ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.