Breaking News
Home / Amharic / የሰው ዘር የተባለ ሁሉ ይህንን ይስማልን !! PLEASE SHARE

የሰው ዘር የተባለ ሁሉ ይህንን ይስማልን !! PLEASE SHARE

ሊታወቅ የሚገባው መረጃ ከጋዜጠኛ ገነት አስማማው! 👇

“የሰው ዘር የተባለ ሁሉ ይህንን ይስማልን”

“የቀበሌው አስተዳዳሪ እኮ ከላይ በተላለፈልኝ ትዕዛዝ ጭፍጨፋውን አስፈጽሜያለሁ አለ ወላሂ” – የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ

የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ እና የቀበሌዋ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ ኪዳኔ ወርዋ በሃገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በአራተኛ ቀናቸው ዛሬ በቶሌ ቀበሌ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ እውነታውን በህዝብ ፊት ተናዘዋል:: የቀበሌዋ አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ ኑዛዜያቸውን ሲናገሩ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ በስልክ ደውለው ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም አሉኝ፡፡

ሰራዊታችን( ኦነግ ሸኔን) ቅዳሜ የሚያካሂደው ኦፕሬሽን አለ ብለው አስፈላጊውን ትብብር እንዳደርግ ነግረውኛል ብሏል አቶ ንጋቱ፡፡

አቶ ንጋቱ እንደሚሉት አቶ ባጫ እና የጸጥታ ሃይሉ ሃላፊ፤ ሰራዊቱ ቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ማታ እንደሚገባ፤እኔ፤አቶ ኪዳነ መርዋ እና ሳጂን አሰፋ የፖሊስ አባላቱን እና የሚሊሻ አባላቱን ከቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ዕለት እንድናስወጣቸው አዘዙን ብሏል፡፡

ሰራዊቱ ወደ ቶሌ ቀበሌ ሲገባም ሰንጋ እንዲታረድለትም ታዘናል የሚሉት አቶ ንጋቱ የተባልነውን አድርገናል ብለዋል፡፡

የጸጥታ ሃይሉን ጨምሮ የቶሌ ቀበሌ ዋና ዋና አመራሮች ሃሙስ ዕለት ቀበሌዋን ለቀው እንዳደሩ የተናገሩት አቶ ንጋቱ ከቀበሌዋ በቅርብ ርቀት ሂደው ማደራቸውን ገልጠዋል፡፡

ሰራዊቱ ሃሙስ ማታ ከገባ በኋላ በቀበሌዋ የተጣለለትን ሰንጋ እየተመገበ ሲጨፍር እንዳደረ ተናግረዋል፡፡

አርብ ዕለት ቀበሌዋ ምንም አይነት የመንግስት መዋቅር ቀበሌ ሆነች የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ቀኑን ሙሉ የቶሌ ቀበሌ ሰፊ በመሆኑ እኛም ራሳችንን ቀይረን ከቀበሌው አንድም ሰው እንዳይወጣ ከሰራዊቱ ጋር ከበባ አደረግን ይላሉ፡፡

የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና ሰላም እና ጸጥታ ሃላፊው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይከታተሉ ነበር የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ዕለት ደውለውልኝ ቅዳሜ ከጠዋቱ ሁለት ጭፍጨፋው እንደሚጀመር እና ስምንት ሰአት ውስጥ እንደሚያልቅ ትዕዛዝ አስተላልፈውልኛል ብለዋል፡፡

የወረዳ አመራሮቹ ሲደውሉልኝ ሌሎች አመራሮችም ከጎኔ ነበሩ እንደ እኔ ራሳቸውን ቀይረው ከሰራዊቱ ጋር ተሰልፈዋል ብለዋል፡፡

አቶ ባጫ ቅዳሜ ተዋት ሁለት ሰአት ይጀመራል ባሉት መሰረት ጭፍጨፋውን እና ዝርፊያውን ጀመርን እስከ ስምንት ሰአትም ቆየን ብለዋል አቶ ንጋቱ

ጥቂት አማራዎች አልሞት ባይ ተጋዳይነታቸውን ሲያደርጉ የሰራዊታችን አባላት ሲመቱ ከወረዳ አምቡላንስ ተልኮልን፤የሰራዊታችንን ቁስለኞች ወደ ጊምቢ ሆስፒታል ስታመላልስ ዋለች አምቢላንስ ነበረች ያሉት አቶ ንጋቱ ኡመታ ከቀኑ ስምንት ሰአት ሲሆን በቃችሁ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ጊምቢ እየመጣ ነው የሚል ትዕዛዝ ተላልፎልን ተመልሰን ከሰራዊታችን ጋር ወደ ጫካ ሄድን፤ከዚያም እኔ እና ባልደረቦቸ መሳሪያችንን እና ልብሳችንን ቀይረን ወደ ቶሌ ቀበሌ ሰላማዊ መስለን መጣን ሲሉ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝብ በተሰበሰበበት ተናዘዋል፡፡

የቶሌ ቀበሌ የሚሊሻ ጽ/ቡት ሃላፊ አቶ ኪዳነ መርዋም በተመሳሳይ የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ የሰጡትን መረጃ ተናግረዋል፡፡

ከጭፍጨፋው የተረፉት የአማራ ተወላጆች ይህንን ከሰሙ በኋላ በከፍተኛ ዋይታ እና ጩሀት ውስጥ እንደነበሩ የአካባቢው የአይን እማኝ ነግሮኛል
አሁን ላይ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በአካባቢው መኖሩን የገለጡት ነዋሪው ገዳዮቹን መከላከያ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት እየተቃወሙ ነው ብለዋል፡፡

‘’ጨፍጫፊዎች ሲያዙ ፤ ልዩ ሃይሎቹ ያለቅሳሉ ይቆረቁራሉ የሚያዝኑት ለእነሱ ነው ለእኛ አይደለም ‘’ ሲሉ ገልጸውታል

መከላከያው ከልዩ ሃይሉም ጋር ተፋጧል የሚሉት የአይን እማኙ ጫካ የገባውም ሁነ ያልገባው አንድ ናቸው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

ከጭፍጨፋ የተረፈው ሜዳ ላይ ነው ያለው፤የሚልሰው የሚቀምሰው የለም የሚሉት ነዋሪው ለመሳፈሪያ ገንዘብ ያለው አማራ በመኪና እንኳን ተሳፍሮ እንዳይሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ሹፌሮቹ ሁሉ አኩርፈዋል አድመውብናል ብለዋል።

ከቶሌ ቀበሌ ሸሽተው በአጎራባች ግንቢ አቅራቢያ የተፈናቀሉ 3ሺ የሚደርሱ አማራዎች በለቻቸው ብር እንኳን ገዝተው እንዳይመገቡ ብራቸውን ከፍለው እንኳን የሚሸጥላቸው ነጋዴ አላገኙም ስቃይ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

አማራ እዚህ መኖር የለበትም መልሰን ስንመጣ እንዳናገኛችሁ ተብለናል የሚሉት የአካባቢው ነዋሪ፣ የተረፍነውን አዲስ አበባ ድረስ እንኳን የሚወስደን እና እሩሃችንን የሚታደገን ወገን ይድረስልን፤ ድምጻችንን አሰሙልን ሲሉ ተማጽነዋል።

ዛሬም ድረስ አስከሬን እየተቀበረ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪው፤ እኔ ራሴ እንኳን የ20 ቀን ህጻናትን ጨምሮ 19 ህጻናት ከተቃጠሉበት እና ታርደው ከተጣሉበት፤በጥይት ተመተው ከወደቁበት አንስቸ 20 ህጻናትን ጉድጓድ ቆፍሬ አንድ ላይ ቀብሬያለሁ ብለዋል፡፡ በቶሌ ጉትን ቀበሌ ብቻ ከአስር ሺ የማያንስ ጠቅላላ ብሬል እና መትረየስ የታጠቀ ሰራዊት ነው የጨፈጨፈን ብለዋል ነዋሪው።

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.