Breaking News
Home / Amharic / የምዕራብ ጉጂ ዞን ነዋሪዎች ሥጋት !

የምዕራብ ጉጂ ዞን ነዋሪዎች ሥጋት !

 
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ጦር ታጣቂዎች ናቸዉ የተባሉ ኃይላት በሚቆጣጠሯቸዉ አካባቢዎች የሚኖረዉ ሕዝብ ከፍተኛ ግፍና በደል እንደሚደርስበት ነዋሪዎች አስታወቁ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ ያነጋገራቸዉ የዞኑ በተለይም የገላን ወረዳ ነዋሪዎች እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ይዘርፏቸዋል፤ያንጋላቷቸዋል፤አልፎ ተርፎ ይገድሏቸዋልም።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የኢዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀዉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በርካታ አካባቢዎችን እየተቆጣጠሩ ነዉ።ታጣቂዎቹ አብዛኞቹን አካባቢዎች በመቆጣጠራቸዉም ነዋሪዉ ከየሚኖርበት ቀበሌ ወደ ሌላ ስፍራ ለመሸሽ እንኳን አልቻለም።ነዋሪዎቹ ይደርስብናል ያሉትን ግፍና በደል የኦሮሚያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ማወቅ አለማወቃቸዉ እረግጠኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። የገላና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሞርካታ ሴሮ ግን ታጣቂዎች የወረዳውን በርካታ ቀበሌያት መቆጣጠራቸዉን አምነው፤ ችግሩ ከአከባቢው የፀጥታ አካላት አቅም በላይ መሆኑንና በየደረጃው ላሉ የመንግስት መዋቅር ማመልከታቸውን አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ የኦሮሚያ መስተዳድር የፀጥታ ኃይላት ባለስልስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገዉ ጥረት አልተሳካለትም።

Check Also

ጥያቄ ለብአዴን! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ??

ብአዴኖች እመኑኝ ብትሞቱ እንኳን አንተዋችሁም!!! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ?? እመኑኝ …

አብይ አህመድ ፋኖን ለማጥፋት መልክተኞች ወደ ጎንደር ልኳል !

Related Posts:ሰበር መረጃ - ጎንደር በመትረየስ እና በፈንጂ ስትታመስ አደረች - ለምን?በደቡብ ጎንደር ዞን ታስረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.