Breaking News
Home / Amharic / የላሊበላን ጉዳይ በተመለከተ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ!

የላሊበላን ጉዳይ በተመለከተ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝባችን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች ተገቢዉ ጥበቃ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ይታገላል። ቀደም ሲል በነበሩና ባብዛኛዉ ሆነ ተብለዉ በሚተገበሩ ድርጊቶች ምክንያት በርካታ ጥፋቶች መሰራታቸዉን እንገነዘባለን። በላሊበላ ላይ የተከሰተዉን ችግር በተመለከተ በተለይ ሰሞኑን በህዝባችን ልጆች በተደረገዉ የማጋለጥ እና ትኩረት እንዲሰጠዉ የሚል ርብርብ ምክንያት በመንግስት ጭምር የተቸረዉ ትኩረት አበረታች ነዉ። ይሄን ጉዳይ በተመለከተ በአብን በኩል በብዙዎች በግልፅ በሚታወቅ መልኩ ከፍተኛ ክትትል ሲደረግ ቆይቷል። በዚህም በርካታ ችግሮችን ለመለየት ችለናል። በአጠቃላይ ታዋቂ የአማራ አክቲቪስቶች ከለዯቸዉ ችግሮች ጋር ተመሳሳይነት አላቸዉ። ስለሆነም የሚከተሉት ተግባራት በተያያዥነት እንዲከናወኑ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አጥብቀን እናሳስባለን:—

1) በላሊበላ ላይ የተሰራው መጠለያ በቀጥታ መቅደሶቹ ላይ ጉዳት እንዳስከተለ በጥናት ተረጋግጧል። በመንግስት በኩል ይህ ተግባር ባግባቡ መጣራት አለበት። በዚህ ሁኔታ ጉዳት ሲደርስ ደግሞ ህጋዊ ምርመራ ተከናዉኖ ጥፋተኛ የሚሆነዉ ወገን ላይ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል። ስለዚህ የክልሉ መንግስትም ይሁን የፌዴራሉ መንግስት ገንዘብ የመሰብሰብ ስራ ላይ ብቻ ማተኮር የለባቸዉም። በተመሳሳይ ግርግሮች ምክንያት ላሊበላ በዚህ መጠን እንዲጎዳ ሆኗል።  የህዝቡ የፍትህ ጥያቄ ተድበስብሶ መቅረት የለበትም። በዚህ ቅርስ ስም እስካሁን የፈሰሰውን የፕሮጀክት ገንዘብ እና የተሰሩት ስራወችን ህጋዊነት በገለልተኛ ባለሞያወችና በህዝብ ተወካዮች አማካኝነት ባስቸኳይ እንዲጣራና ውጤቱ ለህዝብ እንዲገለፅ በማለት እንጠይቃለን።

2) ከዚህ በኋላ ላሊበላ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ የቦታውን ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ያገናዘበ እና ከብክነት እንዲሁም ከስርቆት የጸዳ መሆን ይኖርበታል። ለዚህም እዉቀቱ ባላቸዉ እና ገለልተኛ በሆኑ ባለሞያዎች እየታገዘ የአካባቢዉ ህዝብ በቅርሶቹ ጥበቃ ረገድ፣ ወደፊት በሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት በሚዘረጉ የቁጥጥር ስርአቶች ላይ ጭምር የአካባቢዉ ህዝብ ተሳታፊ የሚሆንበት ህጋዊ መንገድ እንዲፈጠር በማለት እናሳስባለን።

3) ህዝባችን የማይሳተፍባቸው ውሳኔወች በፍፁም ተግባራዊ ሊሆኑ አይገባም። በተለይም የቅርስ ጥበቃ ሃላፊወችን በተመለከተ ባለን ተጨባጭ መረጃ መሰረት የውሸት ሪፖርት ለዩኔስኮ በመጻፍ፣ ላሊበላን በተመለከተ የሚቀርበውን አቤቱታ ሲፈልጉ በማስፈራራት ሌላ ጊዜ ደሞ የውሸት ተስፋ በመስጠት ህዝቡን ለከፍተኛ ምሬት የዳረጉ በመሆኑ በአሁኑ ሰአት ህዝቡ ቅርሳችንን ያድኑልናል የሚል ዓመኔታ ፈጽሞ የሌለዉ በመሆኑ በቀጣይ ይህ ጉዳይ ሊታሰብበት እና ሊታረም ይገባል እንላለን፡፡

4) ላሊበላ ላይ የተሰራዉ መጠለያው ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ፕሮጀክቶች ህዝቡንና ቅርሱን እጅግ በሚጎዳ መልኩ ተተግብረዋል። የአካባቢዉ ህዝብም ከቱሪዝም ዘርፉ እምብዛም ተጠቃሚ የሚሆንበት አሰራር የለም።  በዚህ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዬች ዙሪያ ወደፊት እየተከታተልን ተጨማሪ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃወች እናሳውቃለን።

ጥቅምት 22 ቀን 2011 ዓ/ም
አዲስ አበባ ፣ ሸዋ ፣ ኢትዬጵያ

Check Also

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !!

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !! ********************************************** #ሼር እናድርግ #እናዛምት ከቅዳሜ ግንቦት 5/2015 …

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። መሳይ መኮነን

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። እነአብይ አሁን ብቻቸውን አይደሉም። ከእነጌታቸው ረዳ ጋር ተጣምረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.