Breaking News
Home / Amharic / የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት ተፅዕኖ ስር መውደቁን ኢዜማ አስታወቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት ተፅዕኖ ስር መውደቁን ኢዜማ አስታወቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሁንም ስልጣን ላይ ባለው አስፈፃሚ ተፅዕኖ ስር መውደቁን ኢዜማ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈፃሚውን የመንግስት አካል ሊቆጣጠር ሲገባው አሁንም ያስፈፃሚው ጥገኛ ሆኖ ቀርቷል ብሏል፡፡

የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሲናገሩ በተፅዕኖ ስር ወድቆ የመቅረቱ ምክንያትም ማሳያም አሁንም በራሱ ህግ ማርቀቅ አለመቻሉ ነው ብለዋል፡፡

የሚኖርበትን ህዝብ የወከለ የምክር ቤት አባል በህዝብ ሲመረጥ በሁሉም ዘርፍ ችግራቸውን እየለየ ሊፈታላቸው ቀስቅሶ አሳምኖ ነው ያሉ ሲሆን ራሱ ችግሮችን እየለየ እነዛን ችግሮች የሚፈቱ አዋጆችና ህጎች በራሱ አቅም ማርቅቅና ማፅደቅ ሲገባው ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ የመጣለት ረቂቅ አዋጅና ህግ ላይ ድምፅ ይሰጣል ብለዋል፡፡

የሌሎች ሀገር ልምድ እንደሚያሳየው ህግና አዋጅ የሚያረቁት የምክር ቤት አባላት ናቸው ያሉት አቶ ናትናኤል እኛ ሀገር ግን ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያረቀቁትን ህግና አዋጅ ምኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ከፀደቀ በኋላ ነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድምፅ የሚሰጥበት፤ ይሄን ኢዜማ መቀየር አለበት ብሎ ያምናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ ሚኒስትሮች ምክር ቤትን ያስገረመው የምርጫ ቦርድ ተግባር ሊመሰገን ይገባል ያሉ ሲሆን የምርጫ አዋጁን ከተቋቋመው ካውንስል ጋር ቦርዱ ካወጣ በኋላ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳይልክ ቀጥታ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል ብለዋል፡፡ ለምን ተብሎ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ለቀረበለት ጥያቄ እኔ ተጠሪነቴ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው ብሎ መልሷል ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

ምክር ቤቱ አስፈፃሚውን የመቆጣጠር ስልጣኑን የሚተገብረው ህግን በማውጣት ነው ያሉት አቶ ናትናኤል ኢዜማም እጩዎቹ ከተመረጡ አዋጅና ህግ ማርቀቅ እንዴት ነው የሚሰራው፣ ሌሎችንስ አስተባብሮ እንዴት ነው በምክር ቤቱ ማፀደቅ የሚቻለው የሚለው ላይ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

በዚህ መንገድ ነው የህዝብ እንደራሴዎች የወከሉትን ህዝባቸውን ችግር ሊፈቱ የሚችሉት ብለዋል አቶ ናትናኤል፡፡
(ኢትዮ ኤፍ ኤም)
የካቲት 26/2012 ዓ.ም
—————————————————
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot

Check Also

አማራና ትግሬ ተስማሙና ኦሮሙማን መክቱ። – ሞጣ ቀራንዮ

https://fb.watch/f-ipLpwPrZ/ Related Posts:አማራና ኦሮሞ አትጣሉ። ተዋደዱ !አማራና ትግሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የኦሮሞ ክልል አስተዳደር …

ማስጠንቀቂያ ለከንቲባ አዳነች እቤቤ!

Related Posts:የጃዋር ሞሃመድ የዜግነት አወዛጋቢ ጉዳይ. ጃዋር ማስጠንቀቂያ ተሰጠው !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.