Breaking News
Home / Amharic / ክርስቲያን ታደለ ከቂሊንጦ

ክርስቲያን ታደለ ከቂሊንጦ

  • የአብን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ክርስቲያን ታደለ ከቂሊንጦ
   ==========================
   – “እኔ የታሰርኩት ጎጃሜ ተብዬ አይደለም፤ በለጠ ካሳም የታሰረው ጎንደሬ ተብሎ አይደለም፤ በዚህ ወቅት ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር እያለ የጎጥ አጀንዳ የሚያራግብ እሱ ከእኛ አይደለም፤ ወይም በቁሙ የሞተ ነው።”- “ዶ/ር አምባቸው በእኔ በክርስቲያን ምክንያት ከአብይ ጋር የተጣላና አብኖችን አትንኩብኝ ብሎ ጥርስ የተነከሰበት ጋሻችን ነበር።” ዶ/ር አምባቸው እንደሞተ ስሰማ የተሰማኝ ስሜት እናቴ ስትሞት አልተሰማኝም ነበር፤ መግለፅ የማልፈልጋቸው ብዙ ነገሮችን አብረን ለመስራት ተነጋግረን ነበር፤ ከታሰርኩ በኋላ ሲመረምሩኝ የተጠየቁኩት ጥያቄ “ከእነ አምባቸው ጋር ታይተሃል” የሚል ነበር።’

   – “በሰኔ 15ቱ ክስተት ብዙ ተፈትነናል፤ ብዙ ወገኖችም ፈተናውን ማለፍ አልቻሉም፤ ሆኖም አማራ ናቸውና መክረንና ገስፀን ልንመልሳቸው ይገባል እንጂ አማራ አማራ ላይ መዝመት የለበትም።”

   – “ምግባሩ አዴፓ ውስጥ ፖለቲካ የገባው ብቸኛ ሰው ነበር፤ የከሚሴውን ችግር የፈታነው ከምግባሩ ጋር ሆነን ነበር፤ እነሱን በማጣታችን ትልቅ አቅም ነው ያጣነው።”

   – “ብ/ጄ. አሳምነፅ ፅጌ በመቶ አመት ውስጥ አንድ ጊዜ የሚፈጠር ጀግና ነው፤ ምናልባትም በእኛ ዘመን የተፈጠረ ቴዎድሮስ ነው።”

   -“እኛ ስለታሰርን እኛን እንደ ጀግና ያልታሰሩትን ደግሞ እንደ ከዳተኛ በመቁጠር አሉባልታ የሚነዙትን ልትታገሏቸው ይገባል፤ እኛን አስረው ያልታሰሩትን ደግሞ ስማቸውን የሚያጠፉት አብንን ለማዳከም ስለሚፈልጉ በመሆኑ ህዝባችን ሊነቃባቸው ይገባል።”

   – “አሁን እየተደረገ ያለው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከሚጎዳ እኔ እዚህ ቂሊንጦ ውስጥ መበስበስን እመርጣለሁ።”

   – “አብንን፣ አስራትንና ሌሎች የአማራ ህዝብ ትግል ውጤት የሆኑ ተቋማትን አግዙ፤ ህዝባችን በርትቶ ከታገለ ተቋማቱ ጠንካራ ይሆናሉ፤ መድከማቸውም መበርታታቸውም እንደ ህዝባችን ነው፤ ግን አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን እንችላለን፤ ቀጣይ አመት ስልጣን ይዘን የምንወዳቸውን ህዝባችንን እናገለግላለን።”

   ፍትህ ለመሪያችን!

Check Also

ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል (FANO) የተሰጠ መግለጫ!!

ቢዘገይም ፍላጎታችንና መሆን ያለበት እየሆነ ነው እናመሰግናለን ጀግኖቻችን ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል የተሰጠ መግለጫ!! ××××××××××××××××××××××××××× የአማራ …

የአማራ ፋኖ (የአማራ ህዝባዊ ኃይል ) በአዲስ መንፈስ ተቋቋመ!

Related Posts:የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ውይይቶች በ4 የአውሮፖ ከተሞችበአዲስ አበባ ጉዳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን(አብን) አቋም …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.