Breaking News
Home / Amharic / ኬንያኖች ኃይለ ሥላሴ ጎዳና ብለው ከሰየሙት ወደ 58 አመት ሆኗቸዋል።

ኬንያኖች ኃይለ ሥላሴ ጎዳና ብለው ከሰየሙት ወደ 58 አመት ሆኗቸዋል።

ባጠገቡ ባለፍኩ ቁጥር ሁሌ አነሳዋለሁ እያልኩ ዛሬ ተሳክቶልኝ ፎቶግራፍ አነሳሁት። ኬንያኖች ኃይለ ሥላሴ ጎዳና ብለው አንዱን ትልቅ መንገዳቸውን ከሰየሙት ወደ 58 አመት ሆኗቸዋል።
ኬንያኖች ለምን በግርማዊ ቀዳማዊ ሐይለ ሥላሴ ጎዳንቸውን ሰየሙ ብለን ብንጠይቅ መልሱ በጣም ቀላል ነው። ኬንያኞች በቅኝ ግዛት ቀምበር በነበሩበt ጊዜ ኢትዮጵያ ነፃነታቸውን እንዲያገኙ ብዙ እርዳታ አርጋ ነበር። ስለዚህም ኬንያኖች ውለታን ስለማይረሱ ነው ብለን መመለስ እንችላለን።
በንጉሱ ጊዜ የተሰሩትን ትልቅ ሥራዎች እንደ እነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እነ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እነ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና ሌሎችን አሰብኩ እና ኬንያኖችን አደነኩ። ያው ሁሌ ሰው ሀገሩን ነው የሚያስበውና እዛስ የሆነው እንዴት እኛም ጋር አልሆነም ብዬ ማሰቤ አልቀረም።
ጎረቤታችን ኬንያ ከኖርኩ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል። ኃይለ ሥላሴ ጎዳና ብቻ አይደለም እዚህ ያለው። ምንም እንኳን በፖለቲካ ባይስማሙም በጎሳም ቢለያዩም ሁሉም መሪዎች በሠሩት ሥራ እንዲታወሱ በስማቸው መንገዶች እና ሌሎችም ነገሮች ተሰይሞላቸዋል። ለእኔ ይሄ ትልቅነት ነው።
እኔ ብቻ አይደለሁም ይሄን የማስተውለው። ባለስልጣኖቻችን እዚህ ናይሮቢ ለጉብኝት ሲመጡ ከአሮፕላን ማረፍያው ትንሽ እንደተጓዙ ኬንያታ ጎዳና እና ኃይለ ሥላሴ ጎዳና ሁሌ ነው የሚታያቸው። ምን ይሆን የሚያስቡት እነዚህን ጎዳናዎች እያዩ ሲያልፉ ብዬ መጠየቄ አልቀረም።
በነገራችን ላይ አንድ ኬንያዊ ስለሀገሩ ታሪክ በደንብ ነው የሚያውቀው። ትምህርት ቤት የሚያስተምሩትም ታሪክ ልጆቹን ወደፊት ስኬታማ እንዲሆኑ ታስቦ ነው። ጆሞ ኬንያታ ኪኩዩ ስለሆኑ ስለሳቸው ሌላ ክልል ውስጥ መጥፎ ታሪክ አይተርክም። ዳንየል አራፕሞይ ካሊንጂ ስለሆኑ ሌላ ክልል ውስጥ ሰለሳቸው መጥፎ ታሪክ አይወራም። ጆሞም ሆነ ሞይ ጥፋት ሳይኖራቸው ቀርቶ አይደለም። ያንን ብቻ ቢያስተምሩ ኖሮ ኬንያ ዛሬ ህዝብ ለሕዝብ ተጠላልቶ እንኳን ሊመሰጋገኑ ቀርቶ ግጭት ነበር ውጤቱ። የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ መሪዎቻችን አንዱ ስለ አንዱ ተሞክሮ ይወያዩ ይሆን?
እኛ ኢትዮጵያኞች አስተሳሰባችንን መቀየር አለብን። አንድ ሰው ከየትም ይሁን የትም በሂውት ዘመኑ ጥሩ ነገሮችን ለሚቀጥለው ትውልድ አስተላልፎ ከሄደ እኛም እንደ ጎረቤታችን ኬንያ አመስግነን እውቅና መስጠት ይኖርብናል። ጥፋት ላይ አናተኩር። ምንድነው ጥቅሙ? ህይወታችንን አያሻሽለውም። ልጆቻችንንም አይጠቅማቸውም። እንዲሁ ስንናደድ እኖራለን። ምንም አናተርፍም።
ለዚህም ነው በዓይናችን የተሰሩትን ስራዎች እያየን አልተሰሩም ብለን ምንከራከረው። ለምሳሌ አንድ ሰው ተነስቶ ውጭ ልጓዝ ቢል ያንኑ ንጉሡ የመሰረቱን አየር መንገድ ተጠቅሞ ነው የሚሄደው። ቢሆንም መስራቹ ማነው ሲባል ወገባችንን ይዘን እንከራከራለን ምንም አይነት ምስጋና አይገባም ብለን ስለምናስብ።
ያለፉትን ስራዎች ካላመሰገንን እኛን ወደፊት ያመሰግኑናል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። ለኬንያኖች አክብሮቴን እገልፃለሁ።

Check Also

አማራና ትግሬ ተስማሙና ኦሮሙማን መክቱ። – ሞጣ ቀራንዮ

https://fb.watch/f-ipLpwPrZ/ Related Posts:አማራና ኦሮሞ አትጣሉ። ተዋደዱ !አማራና ትግሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የኦሮሞ ክልል አስተዳደር …

ማስጠንቀቂያ ለከንቲባ አዳነች እቤቤ!

Related Posts:የጃዋር ሞሃመድ የዜግነት አወዛጋቢ ጉዳይ. ጃዋር ማስጠንቀቂያ ተሰጠው !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.