Breaking News
Home / Amharic / ከአዲስ አበባ ለኢትዮጽያ ንቅናቄ (አ•ለ•ን) የተሰጠ መግለጫ

ከአዲስ አበባ ለኢትዮጽያ ንቅናቄ (አ•ለ•ን) የተሰጠ መግለጫ

ከአዲስ አበባ ለኢትዮጽያ ንቅናቄ
(አ•ለ•ን)
የተሰጠ መግለጫ
:- አ•ለ•ን እንደሚታወቀው በአዲስ አበባ ዙሪያ በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ሲሆን ቢሮ ከፍቶ የሚንቀሳቀስ ሲቪክ ማህበር መሆኑ ይታወቃል ሕጋዊ ፈቃዱን ለማግኘት መንግስት የሚያሳትመውን የነጋሪትን ጋዜጣ ህትመት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል በአዲስ አበባ ዙሪያ አሉታዊም ይሁን አወንታዊ ጉዳዬችን በመከታተል የተለያዩ መግለጫዎችን አሳልፈናል ይሁን እና ከግዜ ወደ ግዜ የምናየው የአዲስ አበባ ህዝብ መፈናቀል እና መጠለያ አልባ መሆኑ ሳያንስ በቀጣይ ቀናቶች ከመቶ ሺህ የማያንሱ ነዋሪዎችን በፌደራል ፖሊስ ጭምር በመታገዝ ለማፈናቀል እንደታቀደ በጊዜያዊነት ከተቀመጡት እና የስድስት ወር የስልጣን ግዜያቸው ካለፈው ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አንደበት ሰምተናል በተለያዩ ሚዲያዎችም ተነግራል ይህ ድርጊት እጅግ ሰብአዊነት የጎደለው እና አንድን ክልል አስተዳድራለሁ ለህዝብ ነው የቆምኩት ከሚል የማይጠበቅ እና ፈፅሞ ሰብአዊነት የጎደለው እርምጃ በመሆኑ አንደ አዲስ አበባ ተወላጅ እና ነዋሪነታችን አጥብቀን እየተቃወምን ጉዳዩን በቅርበት እና በንቃት የምንከታተለው መሆኑን እያሳሰብን የባልዳራሱ ባለአደራ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከኛ አላማ ጋር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ አዲስ አበባን በሚመለከት ጉዳይ ከጎኑ በመቆም ድጋፋችንን እናረጋግጣለን 
አዲስ አበባ የኢትዮጽያዊነት ማሰሪያ ውል ናት !! 
አዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ንቅናቄ ሲቪክ ማህበር !!
(አ•ለ•ን)

Check Also

የሴት ሚንስትሮቹ ሁሉ የት ገቡ?

የዘጠኝ ወር እርጉዝ በሜንጫ ታርዳ አልሰሙም ማለት ነው? ወይስ ጠቅላዩ ዝም ሲል እነሱም ዝም አሉ??? …

ሽመልስ አብዲሳ በአደባባይ ላይ ”ነፍጠኛን ላይመለስ ሰባበርነው….

።#ኦህዴድ መራሹ የዶር አብይ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠረዉ የዘር ማጥፉት ወንጀል 97% ለወንጀሉ ተጠያቂ መሆን አለበት …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.