Breaking News
Home / Amharic / ከአብን ስራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ ወጥቻለሁ – ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር )

ከአብን ስራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ ወጥቻለሁ – ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር )

አብን ባለፈው የካቲት አካሂዶት በነበረው ጊዜያዊ የአስፈፃሚ ሪፎርም ላይ ንቅናቄው በቀጣይ 3 ወር ውስጥ የሚያካሂደው ሪፎርም ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ወደ ስራ አስፈፃሚ እንድመለስ የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስኖ ነበር። ወደ አመራርነት የመመለስ ፍላጎት ባይኖረኝም የድርጅቴ ውሳኔ ስለነበር ውሳኔውን ተቀብየው ቆይቻለሁ።

ለአጭር ጊዜ ብየ የተመለስኩበት ጊዜ ስለተጠናቀቀ እንዲሁም ወደፊት ጊዜው ሲደርስ በምገልፃቸው ምክንያቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአብን ስራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ የለቀቅሁ ሲሆን፤ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ግን የአብን ሪፎርም በስኬት እስኪጠናቀቅ የምቀጥል ይሆናል።

የንቅናቄው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አብን ተጠናክሮ ሲቆም ደግሞ ልክ ከአብን ሊቀ መንበርነቴ በገንዛ ፈቃዴ እንደለቀቅሁት ሁሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴንም በገዛ ፈቃዴ በመልቀቅ አዳዲስ መሪዎች በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ መወሰኔን እገልፃለሁ። አማራ በልጆቹ ትግል ሁለንተናዊ ህልውናው ይከበራል!

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር )

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.