Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የተሰጠ መግለጫ!

ከአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የተሰጠ መግለጫ!

 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ሥቃይ እና እንግልት አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የተሰጠ መግለጫ!
በሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ ከአድዋ በዓል ማግስት ጀምሮ ከፍተኛ ስቃይና እንግልት እንዲሁም የመብት ጥሰት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡የጥቃቱ መነሻ <<ለምን የአጼ ምኒልክ ምስል ያለበት ወይም ንጉሡን የሚያስታውስ ቲ-ሸርት ትለብሳላችሁ?>> የሚል የድንቁርና እና ግብዝነትን ጥግ የሚያሳይ አሳፋሪ ምክንያት ነው፡፡
በተደጋጋሚ የምናስተውለው የታሪክ ክህደት ማንኛውም ታሪክ መሥራት የተሳነው እና የበታችነት ስሜት የሚሰማው ቡድን የሚያደርገው የተለመደ ተግባር ቢሆንም ይህ ጉዳይ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጥቃት ምክንያት መሆኑ በእጅጉ ያሳስበናል፡፡ይህንን ዘር ተኮር ጥቃት ከሌላው ለየት የሚያደርገው ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው መንግሥት መቀመጫና የሁሉም ኢትየጵያዊ መኖሪያ በሆነቸው አዲስ አበባ የሚከናወን መሆኑ ነው፡፡በጥቃቱ በቁጥር ቀላል የማይባሉ ተማሪዎች ከመታሰራቸውም በላይ በርካታ ተማሪዎች የአካል ጉዳት እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።በአሁኑ ሰዓትም ብዙዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ በተለያየ ቦታ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ጥቂት ተማሪዎች ደግሞ ለደኅንነታቸው ምንም አይነት ዋስትና በሌለበት ሁኔታ በግቢው ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ወከባው በአማራ ክልል ውስጥም የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) አመራሮችን በማሳደድ የተቀናጀ ሲሆን በዛሬው ዕለት የማህበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ታስሯል፡፡በመጨረሻም የፌደራል እና የክልሉ መንግሥት ተማሪዎች በማንነታቸው ተለይተው የሚደበደቡባት፣የሚፈናቀሉባት፣የሚታሰሩባትና የሚገደሉባት የጋራ ሀገር እንደማትኖረን ተገንዝቦ በአስቸኳይ የታሠሩትን እንዲፈታ እና የተማሪዎችን ሁለንተናዊ ደኅንነት በማረጋገጥ አጥፊዎቹን ለሕግ እንዲያቀርብ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

መጋቢት 5 2014 ዓ.ም
የአማራ ትውልድ ተቋም!!!

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.