Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ አስቸኴይ ጥሪ ! Share !

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ አስቸኴይ ጥሪ ! Share !

ቀን 17/05/2012 ዓ.ም
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ፤
***
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ምክር ቤት ጥር 16 እና 17፣ 2012 ዓ.ም 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ የንቅናቄያችንን አጠቃላይ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ፤ የምርጫ ዝግጅት፤ የታሠሩ የአብን አመራሮችና አባለትን፤ የታገቱ አማራ ተማሪዎችን እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ እና አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ አማራ ጠል የተሳሳተ ትርክት በፈርጣጭ ብሔርተኞች መቀንቀን ከጀመረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያሳለፈ ቢሆንም ለሦስት አስርት ዓመታት መዋቅርና ሕግ ሆኖ አማራን እንደ ህዝብ ለመጨቆን ሥራ ላይ ውሏል። የአማራ ህዝብ የተገንጣይ ብሔርተኞች የተሳሳተ ትርክት እንዲቆም ብሎም ኢትዮጵያዊያን በሰላምና በአንድነት ተከባብረው እንዲኖሩ ሲታገል ቆይቶ በ2010 ዓ.ም ለውጥ እንዲመጣ ቢያድርግም ለውጡን እንመራለን እና እናሻግራለን የሚሉት ተረኛ ነን ባዮች የቆየውን ትርክት ለማስቀጠል በሚያደርጉት ልፊያ ህዝባችን በተደጋጋሚ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል።

የአማራ ህዝብ በሰላምና በመተሳሰብ እሴቱ ከሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር ተዋዶና ተከባብሮ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ህዝብ መሆኑ በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ ሀቅ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያዊያንን የቆየ እሴት የማይወክሉ ብሎም እንቆምለታለን ብለው የሚምሉለትን ህዝብ ዓላማና ፍላጎት የማያውቁ ተገንጣይ የፖለቲካ ቡድኖች በሚያቀነቅኑት የአማራ ጠል ትርክትና እንቅስቃሴ የተነሳ የአማራ ህዝብ ለከፍተኛ ጭቆና ተዳርጎ ቆይቷል። የአማራ ህዝብ ትግል የህልውናና ፀረ ጭቆና መሆኑ የታወቀ ሲሆን ባለፉት ዓመታትም ጭቆናን ሲታገል የነበረው አንደኛው ጨቋኝ በሌላኛው ጨቋኝ እንዲቀየር አልነበረም፤ አይደለምም።
ሆኖም ግን “የአማራን ህዝብ ማህበራዊ ረፍት መንሳት” የሚለው ትህነጋዊ ትርክት በተረኛ መንግስት ነን ባይ ቡድኖችና ተቀፅላዎች በመተካቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት የአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው። በመሆኑም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ምክር ቤት በ5ኛ መደበኛ ጉባኤው በሚከተሉት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔና አቅጣጫ አስቀምጧል።

የታገቱ አማራ ተማሪዎችን በተመለከተ፡- በደንቢዶሎ ዩንቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ አማራ ተማሪዎች ታግተው ከጠፉ ሁለት ወራት አልፈውታል። ይህ የአሸባሪነት ተግባር በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠውና የታገቱ ልጆች እንዲለቀቁ አብን መጠየቁ ይታወሳል። የአማራ ህዝብ እና ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይህን ነውረኛ የአሸባሪነት ተግባር አውግዞ መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ በትዕግስት ሲጠይቅ ቆይቷል። የአብን ብሔራዊ ምክር ቤት በዚህ የአሸባሪነት ተግባር የታገቱ አማራ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሸባሪዎችም ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ እያሳሰበ፤ ለታገቱ አማራ ተማሪዎች ድምፅ ለማሰማት በተለያዩ ከተሞች በአማራ ወጣቶች የተጠራውን ሰልፍ አብን የሚደግፍ መሆኑን ያረጋግጣል። ሰላማዊ ሰልፉም ከየትኛውም ጥቃትና ጥፋት ነፃ በሆነ መንገድ በሰላም እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃና ከለላ የማድረግ ኃላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣ እናሳስባለን፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የአማራ “ክልል” መንግስትና ማዕከላዊ መንግስቱ ላሳዩት የበዛ ቸልተኝነት ተጠያቂነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጊቱን ላልተገባ የፖለቲካ ቁማር ከማዋል ተቆጥበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ መላው የአማራ ህዝብ ቀጣይ በልጆቹ ዙሪያ መንግስት የሚሰጠውን ምላሽ እየተከታተለ ለቀጣይ ትግሎችም ራሱን እንዲያዘጋጅ አብን ጥሪውን ያቀርባል።

የፖለቲካና የህሊና እስረኛ የሆኑ የአብን አመራርና አባላትን በተመለከተ፡- የአማራ “ክልል” ከፍተኛ አመራሮች እና የፌዴራል የጦር መኮንኖች ግድያ ተከትሎ “የክልሉ”ም ሆነ ማዕከላዊ መንግስት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ከመሆኑም በላይ ካላንዳች የፖለቲካ ትርፍ ስሌት ሃቁን በወቅቱ ለህዝብ ማቅረብ ሲገባቸው፤ በህዝብ ላይ የደረሰውን አሳዛኝ በደል እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ይባስ ብሎ ንጹሃን የንቅናቄያችን አመራሮችና አባሎቻችንን በታሪክ አጋጣሚ መንግስት የመሆን እድል የገጠመው ቡድን ለአማራ ህዝብ ካለው የተሳሳተ የጥላቻ አመለካከት በመነሳት በግፍ አግቷቸው እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ገዢው መንግስት የንቅናቄያችንን አመራሮችና አባላት በቂ ባልሆነ ማስረጃ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ብቻ ላለፉት ሰባት ወራት በእስር ላይ አቆይቷቸዋል፡፡ የአማራን ህዝብ ሰላምና ደኅንነት ብሎም የሀገርን ህልውና ግምት ውስጥ በማስገባት ያለአግባብ የታሰሩ የአብን አመራሮችና አባላት በውይይት እንዲፈቱ ከ7 ወራት በላይ ኃላፊነት በተሞላበት እጅግ ከፍተኛ ትዕግስት የጠየቅን ከመሆኑም በላይ ጓዶቻችን ያልተገባ መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም አስመልክቶ ንቅናቄያችን ለህዝብና ለመንግስት በተከታታይ ያሳወቀ ቢሆንም ከመንግስት በኩል ፍትህ በመነፈጉ ምክንያት ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ቀጣይ የሰላማዊ ትግል አማራጮችን ለመጠቀም ተገደናል፡፡ ስለሆነም መንግስት ያለአግባብ በአፈሳ የፈፀመውን እስር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ክሳቸው ተቋርጦ በአንድ ወር ውስጥ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እያሳሰብን፤ በተቀመጠው ጊዜ የማይፈቱ ከሆነ በየደረጃው ያሉ የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ህዝባችንን በማስተባበር እንደሚከተለው በተገለጸው የጊዜ ቅደም ተከተል መሰረት ሁሉንም የሰላማዊ ትግል አማራጮች እንተገብራለን፡፡

የካቲት 22/2012 ዓ.ም፡- በተመረጡ የሃገሪቱ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል፤

የካቲት 26 እና 27/2012 ዓ.ም፡- አድማ ይደረጋል፤
ከመጋቢት 3/2012 ዓ.ም ጀምሮ አመራሮቻችን እና አባሎቻችን እስከሚፈቱ ድረስ ለተከታታይ ቀናት ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲካሄድ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ የወሰነ ሲሆን ለዚህም ከወዲሁ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ከዩኒቨርሲቲዎች ስለተፈናቀሉ ተማሪዎች፡- መንግስት ሀገር የመምራት ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በሰላም ትምህርታቸውን መከታተል ካለመቻላቸውም በላይ አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊና የሞት አደጋ ገጥሟቸዋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የዩኒቨርሰቲ ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ይህ በአማራ ተማሪዎች ላይ የሚፈጸም በደል አማራ ላይ የእውቀት ሽግግር እንዳይኖር ሲደረግ የኖረው መንግስታዊ ጭቆና መገለጫ መሆኑን አብን ይገነዘባል፡፡ ስለዚህ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ተማሪዎቹ ደኅንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበትን መንገድ በአስቸኳይ እንዲያመቻች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያሳስባል፡፡

ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ፡-
ንቅናቄያችን ያዘጋጀው የምርጫ ማኒፌስቶ ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ምክር ቤቱም ተጨማሪ ጉዳዮች ተካተውበትና በተለያዩ አካላት ውይይት እንዲደረግበት እንዲሁም ንቅናቄያችን በቅርቡ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲፀድቅ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመጨረሻም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያለ መላው የአማራ ህዝብና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በማንኛውም ቡድን የሚፈጸምን ኢሰብአዊና የአሸባሪነት ተግባር ተባብሮ እንዲያወግዝ ብሎም ለፍትህ፣ እኩልነትና ነጻነት እንዲሁም የህግ የበላይነት መረጋጋጥ እንዲታገል ንቅናቄያችን ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

አማራ በልጆቹ ትግል ታሪኩን ያድሳል !

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

2 comments

  1. What do you if government uses excessive force?

  2. Listen to the talk between Tsegaye Ararssa and The notorious Ezekiel Gabissa on Kush Media. The want to tear down Abiys govt. And take over. They even speak about how close they were to control state power. They are working with the TPLF to depose Abiy and then settle score with the Neftegna.
    Now the question is whose side is Abin?
    What purpose would this move accomplish?

    Any civil disobedience in Amara kilil will only have counter effect. It will deteriorate the already frgile economy of the region. Make life hard to the poor… just look at the Oromo kilil… investors are abandoning the region. Economy is badly hampered.
    I don’t think you would carry out civil disobedience outside your kilil. Not even in Addis Ababa. So you will only damage your own home..
    Dr. Desalegn, think about it. Weigh the matter again.
    Strike and civil disobedience will only harm your people before the govt. feel its effect…

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.