Breaking News
Home / Amharic / ከላሊበላ በውስጥ መስመር የተላከ …Achamyeleh Tamiru

ከላሊበላ በውስጥ መስመር የተላከ …Achamyeleh Tamiru

ከላሊበላ በውስጥ መስመር የተላከ. . .
“ሰላም ወንድሜ አቻሜለህ፤ ይህን መልዕክት የምጽፍልህ ከላሊባላ ከተማ ትንሽ ወጣ ብዬ ነው። የሕወሓት ተዋጊዎች ያለማንም ከልካይነት ላሊበላን የያዙት ትናንትና ከ11፡30 ጀምሮ ነው። በአሁኑ ወቅት በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ ለብዙ ሺ ዘመናት የኖሩ ጥንታዊ መጽሐፍትንና ቅርሶችን እየዘረፉ ይገኛሉ። ትናንትና ማታ ከጨለመ በኋላ እኔ ወዳለሁበት ቦታ ሸሽተው የቤተክርስቲያኑ እንደነገሩኝ ተዋጊዎቹ ቅብ መጽሐፍትን፣ የብራና መጽሐፍትንና ሌሎችንም ብርቅዬ ቅርሶችን ማታ ሲያስወጡ እንዳመሹ ደም እያነቡ ነገሩኝ። እሳቸው በድብቅ ቤተ ክርስቲያኑን ለቀው ለመንግሥት ለመጮህ በወጡበት ወቅት ከሞትንም እንሙት ብለው እዚያው ያልሸሹ አባቶችን የደበቃችሁት የወርቅ ቅብና የብራና መጽሐፍትና እንዲሁም ብርቅዬ የአለም ቅርስ አለ፤ ከደበቃችሁበት አውጡት እያሉ እየደበደቡ ነበር አሉኝ። እስካሁን ድረስ የክልሉም ሆነ የፌዴራሉ መንግሥት ኃይል የላሊበላን ዘረፋ፣ ውድመትና ምዝበራ ለማስቆም ወደዚህ አልመጣም። እጅግ ልብ ይሰብራል!”

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.