Breaking News
Home / Amharic / ኦሮምያ ሀገር ሆነች እንዴ?
Oromo_Flag_4500x1800@25%_v3

ኦሮምያ ሀገር ሆነች እንዴ?

 
(ደጋግመው ያንብቡት)
ኦሮምያ ሀገርም ትሁን ክፍለሀገር በአሻጥርና በሚስጥር ሳይሆን ሁሉም ነገር በግልፅና ያለ ግብፅ መደረግ አለበት።
በህገመንግስቱ መሰረት ከውጭ መንግስታት ጋር ሀገርን ወክሎ ግንኙነት ማድረግ የክልሎች የስልጣን ደረጃ አይደለም። የኦሮምያው አቶ ሽመልስ አብዲሳ ግን በጎርቫቾቩ ጠቅላያችን ፈቃድ እስካሁን ከጅቡቲ፣ ከሱማሊያ፣ ከኤርትራ እና ከሱዳኑ ጋጠወጥ ጄኔራል አብዱርሀኒ ጋር ተገናኝቶ መክሯል። በኦሮምያ የዜግነት ቢሮ ከተከፈተ 2 ዓመት አልፎታል።
ለመሆኑ ኦሮምያ እንደ ሀገር መንቀሳቀስ ጀምራለች እንዴ?
እስቲ ማሳያዎቹን ለጥቀን እንይ። ኦነግ ወለጋን ተቆጣጥሯል። “ከኦሮምያ መንግስት በጀት ይሰጠን ነበረ” ያለው የቀድሞው የኦነግ መሪ አይደል እንዴ? አሁን ደግሞ ከወራሪዎች ጋር ሆኖ እራሱ ኦነግ ቤኒሻንጉልንም እያመሰ ነው። ከህዋሀት ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ወግቷል።የሀገሪቱ አኬልዳማነት ያሳሳመማቸውና የህዝብ ጩኸት የሰሙ የፓርላማ አባላት ኦነግና ህዋሀት በአሸባሪነት ይፈረጁ የሚል ጥያቄ አንስተው ጥያቄያቸው ታፍኗል። የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ሁለት ተጨማሪ ክልል ተመስርቷል። ተቀናቃኝ የሚባለው ህዋሀት እንዲጠፋ ሆኗል። 33 ዙር የተመረቀ የኦሮምያ ልዩ ሀይል ሳይሳተፍ በስርዓቱ ያልታጠቀና በቂ ስልጠና የሌለው የአማራ ሚሊሻና ልዩ ሀይል የሀገር አድን የክተት አዋጅ ጥሪ ብቻ ሰምቶ ከህዋሀትና ከሱዳን ጋር ፊት ለፊት እንዲፋጠጥ ተደርጓል። ለአማራ ክልል ልዩ ሀይል ስልጠና በጀት የለንም ያለው ራሱ ዶ/ር አብይ ነው።
ፊንፊኔ ኬኛ አስተሳሰብ ስር ሰዷል። በአዲስ አበባ ከንቲባነት ኦሮሞ ብቻ ይሾማል። የፈለገውን ሀብት ዘንጥሎ ይወስዳል። አየር መንገድ፣ ቴሌ፣ ምድር ባቡር እና ኤልፓን በከፊል እንዲሸጡ ተወስኗል። አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከአፍሪካ አንደኛ ግዙፍ ተርሚናል እንዲሰራ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል።
ህዋሀትን የሚያክል ተራራ የናደው መንግስት ጉሙዝ ዞንን ዝም ብሎ ያያል። የዚህ ምስኪን ህዝብ ሰቆቃ የሚቀረው መቼ ነው? በተለይ “የአማራ” ህዝብ የሚሳደደው ለምንድን ነው? አስክሬን በአካፋ የተዛቀበት እኮ የህዳሴ ግድብ ያለበት ክልል እኮ ነው። እንዴት ይህ አካባቢን በስርዓቱ መጠበቅ ይሳናል?
በዚህ የአጣብቂኝ ጊዜ ዶ/ር አብይ ምን እያደረገ ነው? ዲፕሎማሲ? የጦር መሳሪያ ግዢ? ወይስ የጤና መቃወስ? ሀገሪቱ እንኳን ማንንም ታሳብዳለች። በአንፀሩ የሚያሳብዳት ነው በስልጣን የሚከርመው። አብይ ህዝብን ማረጋጋትና በአንድነት ፀንቶ እንዲቆም ማነቃቃት ሲገባው የጠፋው በጤናው ከሆነ ስህተት ነው። ሚዲያውና ህዝቡ እንቅልፍ ለሽ ብለዋል። በዚሁም የሀሰት መረጃ ለሚያሰራጩ ዩቲዩበሮች ተጋላጭ ሆናል። የመንግስት አድር ባይ ሚዲያዎች በዩቲዩበሮች እየተመሩ ናቸው።
በዶ/ር አብይ ዙሪያ የሚባሉ ነገሮች እውነት ካልሆኑ የፋና ወይም የኢቢሲ ጋዜጠኞች ነባራዊ ሁኔታውን ለህዝብ መንገር እንዴት ያቅታቸዋል? በመጨረሻም ዶ/ር አብይ በስራ ገበታው ላይ አለ ብዬ አላምንም? ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ተክቶ እየሰራ ይገኛል። ዛሬ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያይቷል። አብይ ከሚዲያ ከተሰወረ አንድ ወር ከሳምንት አልፎታል። ለማንኛውም ለአብይና ለሀገራችን ጤንነትን ተመኘሁ!
ኦሮምያ ሀገር ሆነች እንዴ?
መስፍን ሙሉጌታ

Check Also

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !!

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !! ********************************************** #ሼር እናድርግ #እናዛምት ከቅዳሜ ግንቦት 5/2015 …

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። መሳይ መኮነን

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። እነአብይ አሁን ብቻቸውን አይደሉም። ከእነጌታቸው ረዳ ጋር ተጣምረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.