Breaking News
Home / Amharic / እንደ ገዳ ባህል ጨፍላቂ የለም – አቶ ተክሌ ይሻው !

እንደ ገዳ ባህል ጨፍላቂ የለም – አቶ ተክሌ ይሻው !

Check Also

ልደቱ አያሌው ከኤርፖርት እንዲመለስ ተደረገ!

የአብይ አህመድ አስተዳደር እልም ያለ አምባገነን መንግስት ከወያኔ የባሰ ነው:: ቺግሩ በሁሉም ሰው ላይ ሊደርስ …

ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የዉይይት መድረክ እነሆ ! እንዳይቀሩ !

Related Posts:ለአማራ ምሁራን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የቀረበ ጥሪ !ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ –አብን ብሔራዊ ምክር ቤት …

One comment

 1. ብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦች፡ና፡ክልሎች፡ከፅንስ፡እስከመቃብር

  የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ፅንስ፡ሃሳብ፡ኢትዮጵያ፡ምድር፡ከመድረሱና፡የኢትዮጵያውያንን፡የዴሞክራሲ፡ጥም፡የፍትህ፡የውክልናና፡የመልካም፡ኣስተዳደር፡መጓደል፡የሚቀርፍ፡በምድረ፡ኢትዮጵያ፡የሚኖሩ፡የተለያየ፡ቋንቋ፡የሚናገሩ፡የተለያየ፡ባህል፡ያላቸው፡ወንድማማች፡ህዝብን፡ሁለንተናዊ፡መስተጋብር፡ያሻሽላል፡ ተብሎ፡ ወደ፡ምድረ፡ኢትዮጵያ፡ከመስረፁ፡በፊት፡ከፍልስፍና፡ ወደ፡ ኣስተምህሮ፡ ከዚያም፡ ወደ፡ህግነት፡በሂደት፡ጐልምሶና፡ዳብሮ፡ በቀድሞዋ፡ መስኮብ፡ ወይንም፡ USSR፡ ለሁለት፡ኣስትርት፡ዓመታት፡ በሥራ፡ላይ፡ ውሎ፡ ነበር። የዚህ፡ፍልስፍና፡ኣባት፡ኣቀንቃኝና፡በሃገረ፡መስኮብ፡ብቻ፡ሳይሆን፡መስኮብ፡ስር፡በወደቁ፡ኣቅመ፡ኣናሳ፡የሶሻሊስት፡ፍልስፍና፡ተከታይ፡ሃገሮች፡ኣንባሪው፡የመስኮቡ፡የቦልሼቪክ፡ፖርቲ፡ና፡የታላቋ፡ሃገር፡መሪ፡ጆሴፍ፡ስታሊን፡ነው።

  የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ሶሺያሊስት፡ፍልስፍና፡ምድረ፡ኢትዮጵያን፡ በተለይም፡የአዲስ፡ኣበባ፡ዩኒቨርሲቲ፡ተማሪዎችን፡በፅሁፍ፡ና፡በውይይት፡መልክ፡የጐበኝው፡እንደ፡ኤ.ኣ. ፡በ1960ዎቹ፡መባቻዎች፡ነው። ከዚያም፡ለሁለት፡ኣሥርት፡ዓመታት፡ዘውዳዊው፡ኣገዛዝ፡በወታደራዊው፡የደርግ፡ሥርዓት፧በ1974፡ከተተካ፡በኋላ፡ወታደራዊ፡ሥርዓቱን፡የተቃወሙና፡ከኢትዮጵያ፡የቅኝ፡ግዛትነት፡ነፃ፡እንወጣለን፡ብለው፡የትጥቅ፡ትግልና፡ፍልሚያ፡ውስጥ፡በገቡ፡የተገንጣይ፡ትግል፡ኣራማጅ፡ነፃ፡ኣውጭ፡ድርጅቶች፡ነፃ፡እናወጣሃለን፡የሚሉትን፡ ህዝብ፡ለመቀስቀሻነትና፡ለማታገያነት፡በመሣሪያነት፡በሚገባ፡ተጠቅመውበታል። ይህም፡ለመሆኑ፡የትህነግና፡የኦነግ፡መሪዎች፡ምንም፡ሳያፍሩ፡በተለያየ፡ኣጋጣሚ፡በኣደባባይ፡ነግረውናል።

  በኢትዩጵያ፧ህዝብ፡የታክስ፡ክፍያ፡ትምህርት፡የቀመሱ፡ነገር፡ግን፡ትምህርታቸውን፡በቅጡ፡ባልተማሩ፡ግልብ፡ተማሪዎች፡የሚመሩ፡የተገንጣይ፡ድርጅቶች፡በምእራባውያንና፡በኣረብ፡ሃገሮች፡ታላቅ፡ቁሳዊና፡ስትራቴጅያዊ፡እርዳታ፡ታጅብው፡፲፯፡ኣመታት፡የፈጀ፡ጦርነት፡ኣካሂደው፡የሽኣብያና፡የትህነግ፡ተገንጣዮች፡ጥምር፡ኣዲስ፡ኣበባን፡በ1983: ተቆጣጠረ። ሽኣብያ፡ኤርትራን፡ይዞ፡ፈረጠጠ። ትህነግ፡በኣምሳያው፡ከፈጠራቸው፡ድርጅቶች፡ጋራ፡ጥምር፡ፈጥሮ፡ኢህኣደግ፡ነኝ፡ኣለ። ኢህኣደግ፡ወታደራዊውን፡መንግስት፡ተክቶ፡የመንግስትነትን፡መንበር፡ተረከበ። ኢህኣደግ፡ሳይደላደል፡ግርግር፡እንዳይበዛበት፡ከኦነግ፡ጋራ፡ለመስራት፡ቆርጫለሁ፡ኣለ።

  ኢህኣደግና፡ኦነግ፡ጊዜ፡ኣላባከኑም፡በልባቸው፡የታተመውን፡የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ፍልስፍናና፡ጣሊያን፡ኢትዮጵያን፡ሲወር፡የተጠቀመበትን፡የከፉፍለህ፡ግዛው፡ክልሎች፡ወስን፡ማእከላዊ፡የኣገዛዝ፡መሳሪያቸው፡ኣድርገው፡ከጫካ፡ኣሽባሪነትና፡ቁምጣ፡ለባሽነት፡ወደ፡ሱፍ፡ለበስ፡ኢትዮጵያን፡የሚፀየፍ፡የኢትዮጵያ፡መሪነት፡ተቀየሩ። የምኒሊክን፡ቤተ፡መንግስት፡ኢትዮጵያን፡ለማፍረስ፡ለኣቀዱት፡ኣላማ፡የባንዳዎች፡ማእከላዊ፡ፅህፈት፡ቤት፡ኣደረገት። ኢትዮጵያን፡ማፍረስ፡በጫካ፡ሳይሆን፡በገሃድ፡ከምኒሊክ፡ቤተ፡መንግስት፡መመራት፡ጀመረ። በመጀመሪያም፡ለኢትዮጵያ፡ኣንድነት፡የቆሙ፡የፖለቲካ፡ድርጅቶችን፡ከድርድር፡ኣስወጥተው፡”ከፋፍለህ፡ግዛውን”፡ ለማንበር፡ለሚመቸው፡ህገ፡መንግስት፡ታዋቂ፡ግለስቦችን፡መልምለው፡የቀኝ፡ገዥዋች፡ኣፓራታይዳዊ፡ህገ፡መንግስት፡ኣርቅቀው፡ኣፀደቁ። ኣለቀ፡ደቀቀ! ጊዜ፡የዋጀውን፡የኢትዮጵያን፡ታሪካዊ፡ተፈጥሮኣዊ፡መልከኣ፡ምድራዊ፡የኣስተዳደር፡ክፍላተ፡ሃገራትን፡ኣውራጃዎችን፡ወረዳዎችን፡ኣፈረሱ። ክፍላተ፡ሃገራትን፡ኣፈርስው፡በዘር፡ክልል፡ተኩ። ክልሎች፡በስንደቅ፡ኣላማ፡በኣንድ፡ዘር፡ቋንቋ፡በወስን፡ተለይተው፡የየግላቸውን፡ህገ፡መንግስት፡ኣወጡ። በክልሎች፡ውስጥ፡የሚኖሩ፡ብሄር፡ብሄረስቦች፡የክልል፡ባለቤትነት፡ለተስጣቸው፡ኣብይ፡ብሄሮች፡ኣፋሽ፡ኣጎንባሽ፡እንጅ፡እንዲያው፡ምን፡ኣግብቶኣችሁ፡ተባሉ። ይህም፡በመሆኑ፡ዘረኝነት፡በህግ፡መዋቅራዊ፡ይዘት፡ተበጀለት። ይህም፡በመሆኑ፡በኢትዮጵያ፡ውስጥ፡በኣጭር፡ጊዜ፡ኣንዱ፡የሃገር፡ባለቤት፡ሌላው፡ሃገር፡ኣልባ፡ኣንዱ፡ተፈናቃይ፡ሌላው፡ኣፈናቃይ፡ኣንዱ፡ገዳይ፡ሌላው፡ተገዳይ፡ኣንዱ፡ዘር፡ኣጥፊ፡ሌላው፡የዘር፡ማጥፉት፡ወንጀል፡በጠራራ፡ፀሐይ፡በገሃድ፡የሚፈፀምበት፡ሆነ።

  የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡የእርኩስት፡ከፋፍለህ፡ግዛው፡ሥርዓት፡ክሽፈት፡በኢትዮጵያ፡ኣልተጀመረም። ይህንን፡ኣስተሳስብ፡ኣስርፀው፡ኣንድ፡ሃገር፡በመገንባት፡ፉንታ፡የታላቋን፡መስኮብ፡ሪፕብሊኮች፡እንደተለያዮ፡ሃገሮች፡ግን፡በሶሺያሊስት፡ወንድማማች፡ኣስተምህሮ፡የተጠረነፉ፡ኣድርገው፡በማዋቀራቸው፡የሶሺያሊስት፡ኣስተምህሮና፡ሥርዓት፡በዓለም፡ሲከሽፍና፡የመስኮብ፡ማእከላዊ፡መንግስት፡በፖለቲካና፡በኢኮኖሚ፡ሲዳከም፡እናታቸውን፡መስኮብን፡ከጀርመን፡የመስፋፋት፡ኣባዜ፡የታደገቻቸውን፡ኣገር፡ጥለው፡ለመፈርጠጥ፡ጊዜም፡ኣልፈጀባቸው። በዚህ፡ታሪካዊ፡ኣጋጣሚ፡ “በስው፡ቁስል፡እንጨት፡ስደድበት፡” ሆነና፡ መስኮብ፡በለውጥ፡ስትናጥና፡ማእከላዊው፡መንግስት፡ሲዳከም፡መዳከሙን፡እንደትልቅ፡ጠላትን፡የበለጠ፡ማዳከሚያ፡ስልትነት፡በጉጉት፡ሲጠብቍ፡የነበሩ፡የምእራባውያን፡ህብረት፡ወርቃማውን፡ኣጋጣሚ፡ተጠቅመው፡ብዙ፡የመስኮብ፡ሪፕብሊኮች፡ነፃነታቸውን፡እንዲያውጁ፡ኣማለሏቸው፡ነዋይ፡ኣፈስሱላቸው፡ኣስኮበለሏቸው። ምእራባውያን፡በነፃነት፡ስም፡ከመስኮብ፡ያማለሏቸው፡የቀድሞው፡የመስኮብ፡ሪፑብሊኮች፡በኣሁኑ፡ወቅት፡የት፡እንደደረሱ፡ዞር፡ብለን፡ስንመለከት፡ሪፑብሊኮቹ፡ከተራገፉ፡በኋላ፡መስኮብ፡(ራሽያ)፡ለራሷ፡ካመጣችው፡ኣንፃራዊ፧የፖለቲካና፡የኢኮኖሚ፡መሻሻል፡ሲነፃፀር፡ነፃ፡ወጣን፡ብለው፡ከሚያስቡት፡የቀድሞ፡የመስኮብ፡ሪፑብሊኮች፡ባያሌው፡ይሻላል። የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡የእርኩስት፡ከፋፍለህ፡ግዛው፡ሥርዓትና፡ኣስተሳስብ፡የመስኮብ፡ሪፑብሊኮች፡ከመስኮብ፡እንዲገነጠሉ፡ብቸኛና፡ለኣደጋ፡ተጋላጭ፡እንዲሆኑ፡ከኣደረጓቸው፡መሠረታዊ፡ምክነያቶች፡ኣንዱ፡ነው።

  በተመሳሳይም፡ይህ፡ፍልስፍና፡ጠንካራ፡የሪፑብሊክ፡ግዛቶችና፡ደካማ፡ማእከላዊ፡መንግስት፡በሚል፡መርሆ፡የተንጠለጠለ፡በመሆኑ፡ በዮጎዝላቪያ፡ውስጥ፡በተከስተው፡ከህገ፡መንግስቱ፡የመነጨ፡የማእከላዊ፡መንግስቱ፡መዳከምና፡ የእራስን፡በራስ፡ማስተዳደር፡ውክልና፡ጥያቄ፡በኣግባብና፡በስላማዊ፡መንገድ፡መመለስ፡ባለመቻሉ፡ለዘመናት፡ኣብሮ፡ና፡ተጋምዶ፡የኖረ፡ህዝብ፡መሀከል፡የእርስ፡በርስ፡ጦርነት፡ቀስቅሶ፡ዮጎዝላቪያ፡ ወደስድስት፡የተለያዩ፡ሪፕብሊኮች፡እንድትገነጣጠል፡ከምክነያቶቹ፡ትልቁን፡ድርሻ፡ይወስዳል።

  ሃገር፡ኣፍራሹ፡የብሄር፡ብሄረስቦች፡ና፡ህዝቦች፡ኣመለካከት፡ኣስተሳስብ፡ና፡ኣስተምህሮ፡የፖለቲካ፡ፖርቲዎችና፡ድርጅቶች፡ዋናኛ፡መርህ፡ሆኖ፡እንዳይስራ፡በብዙየኣፍሪካ፡ሃገሮችም፡በህግ፡የታገደ፡ነው።

  የኢትዩጵያ፡የብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦች፡ና፡ክልሎች፡ተሞክሮ፣

  መልካም፡መልካምን፡ይወልዳል። በፈረንጆች፡ኣባባልም፧ ጥሩ፡ነገር፡ከምንጩ፡ያስታውቃል፡ማለት፡ሲፈልጉ፣ ” ኣፕሉ፡ከዛፉ፡ርቆ፡ኣይወድቅም” ይላሉ። ይህም፡ማለት፡ከጥሩ፡የኣፕል፡ዘር፡ፍሬ፡ጥሩ፡ኣፕል፡ይበቅላል፡ነውና። ጥሩና፡መልካም፡ኣስተሳስብ፡ጥሩ፡ስነ፡ምግባርን፡ይወልዳል። ይህም፡ለመልካም፡መስተጋብር፡ታላቅ፡መስረት፡ነው። በመሆኑም፡የኣስተሳስብ፡መዛባት፡ስርዓታዊ፡የሆነ፡የስነልቦናና፡የመስተጋብርን፡መዛባት፡ይፈለፍላል። የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡የእርኩስት፡ከፋፍለህ፡ግዛው፡ሥርዓት፡ በኢትዮጵያ፡ መዋቅራዊና፡ስርአታዊ፡የስነልቦናና፡የመስተጋብር፡መዛባት፡ ፈጥሯል። በዚህም፡ምክነያት፡ኣስተዳደራዊና፡ፍትሃዊ፡መዛባቶች፡ተቀባይነት፡ኣግኝተው፡በስፊው፡እንዲንስራፉ፡ኣድርጓል። መሳደድ፡መፈናቀል፡መገደልና፡ዘር፡ማጥፉት፡የእለት፡ተለት፡ተግባር፡እንዲሆን፡ኣድርጓል። ይህ፡ፍልስፍና፡ከኣስተሳስብነት፡ወደ፧ህግነት፡እና፡ኣስተዳደራዊ፡ሥሪት፡ኣድጓል። ይህን፡ክፉ፡ሥርኣት፡በስው፡መስለን፡በኢትዮጵያ፡ምድር፡የፈፀማቸውን፡እና፡ያስፈፀማቸውን፡ገድሎች፡እንመለከት፣

  ገድል-፩ – ኣስገንጣይነት
  በቅርብ፡ዘመን፡በኤርትራነት፡የምትጠራዋን፡የኢትዮጵያን፡ጥንስስ፡ባለ፡ጥልቅ፡ታሪኳን፡ባሕረ፡ነጋሽን፡ከእናቷ፡ከኢትዮጵያ፡ለጊዜውም፡ቢሆን፡፵፡ዓመት፡በፈጀ፡ኣውዳሚ፡የወንድማማቾች፡ጦርነት፡እንድትለይና፡በውስጧም፡የሚኖር፡ወንድም፡ህዝብ፡ድሮ፡ከነበረበት፡ለባስና፡ለከፉ፡ድህነትና፡ኣፈና፡ዳርጓል!

  ገድል-፪ – ግፈኝነት
  በምእራባውያንና፡በኣረብ፡ሃገሮች፡ያለስለስ፡የገንዘብ፡የመሳሪያ፡የታክቲክ፡እርዳታ፡ታጅቦ፡ስልጣን፡ከደርግ፡የነጠቀው፡የተገንጣዮች፡ስብስብ፡በኣገኝው፡ኢትዮጵያን፡የመግዛት፡የታሪክ፡ኣጋጣሚ፡”ይቺ፡ኣገር፡” የሚል፡ስም፡ኣውጥቶላት፡ በዘመኑ፡ “ነፍስ፡በላ፡” የሚባል፡ “የቀይ፡ሽብርና፡” ፡ “የፍየል፡ወጠጤ፡” ጌታን ፡ተክቶ፡የ፡ “የቀይ፡ሽብርና፡” ፡ “የፍየል፡ወጠጤን፡” ጌታ፡ ገድሎችን፡የሚያስንቅ፡የግፍ፡ተግባሮችን፡ በብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ስም፡ፈፅሟል። ለነዚህ፡የግፍ፡ተግባሮች፡በየቦታው፡የኣይን፡እማኝነት፡ምስክር፡የሚስጡ፡በፎቶግራፍ፡በቪዲዮና፡በፅሑፍ፡የተመዘገቡ፡በቅርብ፡ቀን፡በዘር፡ማጥፉት፡ቤተ፡ቅርስ፡የሚቀርቡ፡ዘግናኝ፡ተግባሮችን፡ፈፅሟል፡ኣስፈፅሟል።

  ገድል-፫ – ክህደት
  የተገንጣዮቹ፡ስብስብ፡በሽኣቢያ፡መሪነት፡ትህነግና፡ኦነግ፡በኢትዮጵያውያን፡ላይ፡በር፡ዘግተው፡የከፉፍለህ፡ግዛውን፡ህገ፡መንግስት፡ሲያረቁ፡የኢትዮጵያን፡ከ፬ሽህ፡እስከ፡፯ሽህ፡ኣመታት፡ጥልቅ፡ታሪክ፡ከቁም፡ነገር፡ሳይቆጥሩ፡ ነው። “በእንቅርት፡ላይ፡ጆሮ፡ደግፍ፡” እንዲሉ፡እንዲያውም፡የኢትዮጵያ፡ታሪኳ፡ከዓፄ፡ምኒሊክ፡ይጀምራል፡ኣሉ። ከዚያም፡በኣፄ፡ምኒሊክ፡ተስፉፊነት፡በኣም፡ሃራ፡ቅኝ፡የተገዛን፡ብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦች፡ነን፡ብለው፡ደመደሙ። የኢትዮጽያን፡ረዥም፡ታሪክ፡ያነሳ፡ሁለ፡እርኩስ፡መንፈስ፡ሆነ። ተገንጣዮች፡ነገሡ። ኢትዮጵያዊነት፡ረከስ፡ተከስስ፡ኮስስ። ኢትዮጵያን፡በራሳችን፡ኣምሳያ፡ድንክዬ፡ኣድርገን፡እንፈጥራታለን፡ኣሉ። የሚቃወም፡ሳይሆን፡የሚያስጥል፡ጠፉ።

  ህገ፡መንግስቱን፡ለማርቀቅ፡ሲንደረደሩ፡ኢትዮጵያ፡ከዚህ፡በፊት፡ኖራ፡እንደማታውቅ፡ለሽህ፡ኣመታት፡በሉኣላዊ፡ምድሯ፡በኣባቶቻቸውና፡በራሳቸው፡ደምና፡ኣጥንት፡ክስካሽ፡ኢትዮጵያዊ፡ዜግነትን፡ ያፈሩ፡ኢትዮጵያውያን፡እንደሌሉ፡ተቆጥሮ፡ተካዱ። ኢትዮጵያ፡የዜጎቿ፡ሳትሆን፡በውስጧ፡በሚኖሩ፡በብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ፈቃድና፡ይሁንታ፡የተመስረተች፡ናት፡ኣሉ። ኣመስጠሩ! ምስጢሩም፡ሉኣላዊነትን፡ከኢትዮጵያ፡ገፈው፡ለብሄራዊ፡ክልሎች፡መስጠት፡ሆነ። ከዚያም፡በ፲፬ ክፍላተ፡ሃገራትና፡ሁለት፡ራስ፡ገዝ፡ኣስተዳደሮች፡(ኣዲስ፡ኣበባንና፡ኣስብን፡ጨምሮ፡ በ፲፮፡ኣስተዳደሮች፡በጠንካራ፡ማእከላዊ፡መንግስት፡ትመራ፡ የነበረችውን፡ጥንታዊዋን፡ኢትዮጵያ፡ምንም፡ግንዛቤ፡ውስጥ፡ባለመጨመር፡ገነጣጠሏት። ለመገንጠል፡እንዲመቻቸውም፡የየግል፡ ካርታቸውን፡ይዘው፡ወደ፡ድርድር፡ብቅ፡ኣሉ። ህገ፡መንግስቱ፡በመግቢያው፡ኢትዮጵያ፡የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ናትን፡ደነገገ። ኢትዮጵያዊነትንና፡ዜግነት፡ከዜጎች፡ከግለስቦች፡ተገፈፈ!
  በብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡ስሌት፡ሽኣቢያ፡ትህነግና፡ኦነግ፡እንደሚስማማቸው፡እንደቀረፁት፡ካርታና፡የወደፊት፡ምናባዊ፡ሀገሮቻቸው፡በሚስማማ፡መልኩ፡፲፮ መስተዳደርቾን፡ወደ፡ኣስር፡ኣውርደው፡ኢትዮጵያን፡ተቀራመቱ። ሽኣቢያም፡ድንክዬ፡ኤርትራን፡ኣስብን፡ጨምሮ፡ያለ፡ኮርቻ፡ፈረጠጠ።

  ትህነግ፡ከጐንደርና፡ወሎ፡ክፍላተ፡ሃገራት፡በጉልበት፡የገመስውን፡ወልቃይት፡ጠገዴንና፡ራያን፡በክልል፡ኣንድ፡ገቢ፡ኣደረገ። ትህነግ፡ኣም፡ሃራን፡የጠላ፡ሁሉ፡ወዳጄ፡ነው፡ብሎ፡ሽዋን፡ገማምሶ፡ባሌን፡ኣርሲን፡ኢሊባቡርን፡ግማሽ፡ወለጋን፡ግማሽ፡ከፋንና፡ግማሽ፡ሐረርን፡ኣክሎ፡ኦሮሚያ፡የሚባል፡ምንም፡ኢትዮጵያዊ፡የታሪክ፡መስረት፡የሌለው፡ክልል፡ፈጠረ። ይህ፡የፈጠራ፡ክልል፡የትህነግና፡የኦነግ፡ምናባዊ፡ፍጡር፡ሳይሆን፡በጀርመን፡የፕሮቴስታንት፡ሃይማኖት፡ኣስፉፊች፡ከመቶ፡ሃምሳ፡ኣመታት፡በፊት፡ታልሞ፡ኢትዮጵያን፡ቆርሶ፡ ጀርመኖች፡በጊዜው፡የጥቁር፡ጀርመኖች፡ለሚሏቸው፡የኢትዮጵያና፡የኬንያ፡ኦሮሞ፡ማህበረስብ፡ፕሮቴስታንታዊ፡የኦሮሞ፡ሃገር፡ለመቆርቆር፡የታስበ፡ነው። ጀርመኖች፡ያወጡለትም፡ስም፡ኦርማንያ፡ይባላል። ይህም፡ጀርማንያ፡ከሚለው፡የጀርመን፡ስም፡ለማመሳስል፡ነው፡ሲሉ፡በዚህ፡ርዕስ፡ጥልቅ፡ጥናትና፡ምርምር፡ያደረጉ፡ፃሕፍት፡ይነግሩናል። ኣጃኢብ፡ነው፡ትህነግ፡ኦርማንያ፡በኦሮሚያ፡ተከሽኖ፡ከኢትዮጵያውይን፡ተነጥቆ፡ኬኛ፡ለተጠናወተው፡ኦነግ፡ሲያደላድል፡በዛሬይቱ፡ኦሮሚያ፡የሚኖሩትን፡ባለ፡ሃገሮች፡ኢትዮጵያውያንን፡ፍፁም፡ክዶ፡ነው። ምክነያቱም፡በኦሮሚያ፡ውስጥ፡የሚኖሩትን፡ኦሮሞነትን፡ያልመረጡና፡ያልሆኑትንም፡በ፳ሚሊዮን፡የሚቆጠሩ፡ኢትዮጵያውያን፡ውክልና፡ማሳጣት፡ብቻ፡ሳይሆን፡ሃገር፡ኣልባ፡ያደረገ፡ክህደት፡በመሆኑ፡ነው።

  ገድል-፬ – እርኩስት
  የብሄር፡ብሄረስቦች፡ኣስተምህሮ፡ኣንድ፡ክልል፡ለኣንድ፡ለተለየ፡ብሄር፡በበላይነት፡እንዲመራ፡ካልፈለገም፡ከኢትዮጵያ፡እንዲገነጠል፡የተስጠ፡ነው ይላል። ለምሳሌ፡የኦሮምያ፡ህገ፡መንግስት፡የኦሮሞ፡ማህበረስብ፡ኦሮምያን፡በበላይነት፡ይመራል፡ይላል። ይህ፡ማለት፡ኦሮሞ፡ያልሆነ፡ኦሮሚፋ፡የማይናገር፡የኦሮሞ፡ባህልን፡ያልተላበስ፡ኢትዮጵያዊ፡በኦሮሚያ፡ውስጥ፡የብሄር፡ብሄረስብ፡መብት፡የለውም፡ማለት፡ነው። ለዚህም፡ነው፡ባለቤትና፡መጤ፡ወይንም፡ስፉሪ፡የሚለው፡የእርኩስት፡እሳቤ፡በወጣቱ፡ትውልድ፡እንዲስርፅ፡የተደረገውና፡ሆን፡ተብሎ፡ለ፴፡ዓመታት፡በጥናትና፡በእቅድ፡የተስራበት።

  ገድል-፭- ማፈናቀል
  እርኩስት፡በስራ፡ሲተገበር፡ውጤቱ፡መጤ፡ስፉሪ፡የተባለውን፡ማሳደድ፡ማፈናቀል፡መዝርፍ፡ለዘመናት፡ከኖረበት፡እንዲነቀል፡ማድረግ፡ነው!

  ገድል-፮- መግደል
  ከማሳደድ፡ማፈናቀል፡መዝርፍ፡የተረፈውንና፡በፍርሃት፡ኣካባቢውን፡ለቆ፡ኣልስደድም፡ያለውን፡ኣጋጣሚ፡እየጠበቁ፡መግደል። ግድያውንም፡በኣስቃቂ፡ሁኔታ፡መፈፀም። ገድሎም፡ሬሳው፧እንዳይነሳ፡በመከልከል፡”እኔን፡ያህ፡ተቀጣ፡” ኣይነት፡ሽብር፡ፈጥሮ፡የኣካባቢው፡ስው፡ለቆ፡እንዲወጣ፡ማሽበር።

  ገድል-፯ – የዘር፡ማጥፋት፡ወንጀል
  ግለስቦችን፡በብዛት፡በየቦታው፡መግደል፡ውጤት፡በቂ፡ሽብር፡ፈጥሮ፡የዘር፡ማፅዳት፡ባልተቻለባቸው፡ቦታዎች፡ለምሳሌ፡ያህል፡በኣሁኑ፡ወቅት፡በወለጋና፡በመተከል፡የጅምላ፡ ግድያን ፡በኣስቃቂ፡ሁኔታ፡ማንንም፡ሳይመርጡ፡በህፃናት፡በኣዛውንት፡በሴቶችና፡ወንዶች፡ላይ፡በመፈፀም፡ትልቅ፡የሃገር፡ውስጥ፡ፍልስት፡መፍጠር። በኣሁኑ፡ወቅት፡በዘር፡ማጥፉት፡ወንጀል፡ምክነያት፡በመቶ፡ሽዋች፡የሚቆጠሩ፡ኢትዮጵያውያን፡ፍልስት፡ረሃብና፡እርዛት፡በኢትዮጵያውያን፡ተፈፅሞባቸዋል። ይህ፡የዘር፡ማጥፋት፡ወንጀልና፡ፍልስት፡ይዘቱ፡ስፉቱና፡መጠኑም፡በጣም፡እየጨመረ፡መጥቷል።

  ገድል-፰- የጅምላ፡መቃብር
  በመተከል፡ኣውራጃ፡በቡለን፡ወረዳ፡እ.ኤ.ኣ. በDecember, (ታህሳስ) 23,2020 ራሱን፡ ቤነንስደድ (የቤንሻንጉል፡ነፃነት፡ንቅናቄ፡ለስላምና፡ዴሞክራሲ፡ድርጅት፡) ብሎ፡ የሚጠራ፡ኣሽባሪ፡ድርጅት፡በ፫መቶ፡የሚቆጠሩ፡የኣም፡ሃራ፡ኣገውና፡ሽናሻ፡ማህበረስብ፡ላይ፡ኣስቃቂ፡ግድያና፡በኣካባቢው፡ማህበረስብም፡ትልቅ፡ሽብር፡ፈፅሟል። በብሄር፡ብሄረስብ፡ኣስተምህሮና፡ህግ፡መስረት፡ቤነንስደድ፡ሌሎች፡የሚላቸውን፡ኢትዮጵያውያንን፡በቤንሻንጉል፡መኖረቸውን፡መስራታቸውና፡ታክስ፡መክፈላቸውን፡እንደወንጀል፡ይቆጥርባቸዋል። በመሆኑም፡በቡለን፡ወረዳ፡ለብዙ፡ኣመታት፡በሚኖሩበት፡ቀዬ፡ገብቶ፡ኣስቃቂ፡የጅምላ፡እልቂት፡ፈፅሞባቸዋል። ይህ፡ኣስቃቂ፡ግድያ፡መፈፀሙ፡ኣልበቃ፡ብሎ፡እኒህ፡ስማእታት፡ኣስከሬናቸው፡ሳይቀር፡ክብር፡ተነፍጎ፡በጅምላ፡መቃብር፡በግሬደር፡ተዝቅው፡እንደቆሻሻ፡ እንዲጣሉ፡ሆነዋል። የጅምላ፡ግድያ፡ፈፃሚው፡ቤነንስደድ፡ሲሆን፡ኣስፈፃሚው፡ኦነግ፡ነው። ከጥይትና፡ካራ፡ባለፈ፡ዋነኛው፡የግድያ፡መሳሪያ፡የብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦችና፡ክልሎች፡ኣይነኬ፡የሚባለው፡የኦነጋውያን፡የስልጣን፡ማስጠበቂያ፡ኣለያም፡ገሚስ፡ኢትዮጵያን፡የሚቆርሱበት፡የህወትና፡የሽኣብያ፡ህገ፡መንግስት፡ነው።

  ይህ፡ሁሉ፡በኢትዮጵያውያን፡ላይ፡ሲፈፀም፡የብሄር፡ብሄረስቦችና፡ህዝቦች፡የፌደራሊዝም፡ማእከላዊ፡መንግስት፡እርምጃ፡ኣልወስደም!! ለምን? ፌደራሊዝሙ፡የቆመለትን፡ኣላማ፡በትክክል፡እየተገበረ፡ስለሆነ!

  በመጨረሻም፡ የብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦችና፡ክልሎች ፡ኣስተሳስብና፡ህገ፡መንግስት፡እ.ኤ.ኣ. በ1983 በኢትዮጵያ፡ህልው ፡ከሆነበት፡ጊዜ፡ጀምሮ፡በብዙ፡ሽህ፡የሚቆጠሩ፡ኢትዮጵያውያንን፡በግፍ፡እንዲገደሉ፡በመቶ፡ሽዎች፡ኢትዮጵያን፡ለቅቀው፡እንዲስደዱ፡በሚሊዮኖች፡የሚቆጠሩም፡የሃገር፡ውስጥ፡ፍልስት፡እንዲፈፀምባቸው፡ኣድርጓል። በእርግጥ፡ይህንን፡ግፍ፡ፈፃሚዎቹ፡ስዎች፡ናቸው። ኣሁን፡ፈፃሚውን፡ትተህ፡ይህን፡ከኣፈፃፀም፡ጉድለት፡እንጅ፡ምስጢሩ፡ያልተገለፀልህን፡ዴሞክራሲን፡በኢትዮጵያ፡ማንበሪያ፡መሳሪያችንን፡ኣትንካ፡ኣትኮንን፡ለምትሉ፡ግልፅ፡ባለ፡ቋንቋ፡ ልትገነዘቡት፡የሚገባው፡ የብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦችና፡ክልሎች፡ኣስተሳስብና፡ህገ፡መንግስት፡ ትህነጋውያንና፡ኦነጋውያን፡በብሄር፡ብሄረስቦች፡ስም፡እምንታቆለፖፐሷቸውን፡ ኢትዮጵያውያን፡ክብር፡ነፍጎኣቸው፡ በኣንድ፡መቃብር፡እንዲቀበሩ፡ኣድርጓል።

  በብሄር፡ብሄረስቦች፡ህዝቦችና፡ክልሎች፡ኣስተሳስብና፡ህገ፡መንግስት፡ኢትዮጵያ፡በኣስተሳስብ፡መጥበብ፡ብቻ፡ሳይሆን፡ስብኣዊነት፡ፍፁም፡የረከስባት፡የእርኩስት፡መንፈስ፡የተጠናወታት፡ሲኦል፡ገደል፡ኣፉፍ፡ላይ፡ኣድርሷታል። ይህ፡በመሆኑም፡ይህ፡እጅግ፡ኣደገኛ፡እሳቤ፡ከመክሽፍ፡ኣልፎ፡ከፈጣሪው፡ከትህነግ፡ጋራ፡ኣብሮ፡ሞቶኣል። የሚቀጥለው፡የለየት፡ፍልሚያ፡በእራሱ፡ተፈጥሮኣዊ፡ሂደት፡የሞትን፡እሳቤና፡ህገ፡መንግስት፡ ለማስቀጠል፡ በሚውተረተሩ፡በመሽባቸው፡ኦነጋውያንና፡ኢትዮጵያውያን፡መሃከል፡ነው።

  ኢትዮጵያን፡ምርጫ፡ከፍልሚያ፡ኣይድናትም፡ያፉጥነዋል፡እንጅ!! ጊዜው፡የብሄራዊ፧እርቅና፡በኣዲስ፡ብሄራዊ፡ሽንጎ፡ህገ፡መንግስት፡የሚረቅበት፡ነው። ምርጫ፡ከእርቅና፡ከህገ፡መንግስት፡ማሻሻል፡ኣይቀድምም!!!!!!!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.