Breaking News
Home / Amharic / ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻቸው መዓድ ለማጋራት እንዲዘጋጁ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ!

ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻቸው መዓድ ለማጋራት እንዲዘጋጁ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ አንድ ቤተሰብ ለሌላ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ለማካፈል የሚያስችል ዝግጅት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ማዕድ ማጋራት” ሲሉ በሰየሙት መንገድም መንግስት የኮሮና ወረርሽኝ የከፋ ጉዳት ቢያደርስ በየቤቱ ምግብ ለማድረስ አቅሙም ሆነ መንገዱ ስለማይኖረው፤ ሰዎች በምግብ እጦት እንዳይጎዱ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ሌላ ቤተሰብ ለማቅረብ ዝግጅት እንዲደረግ እና እንደቤተሰብ ምክክር እንዲደረግ አሳስበዋል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ወጣቶችም እረፍታቸውን ተጠቅመው ከዚህ ችግር እንዴት መሻገር እንደሚቻል ጥናት፣ ምርምር እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የጥበብ ሰዎችም የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ የተለያየ የስነ-ጥበብ ስራ በመስራት በሽታውን ለማሸነፍ የሚቻልበትን የተስፋ መንገድ እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

=======================================================
ይሄን በተመለከተ አንድ የግል ድርጅት በድያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ለወገኖቻቸው ምግብ ወይም ሌላ ስጦታ የምያቀርቡበት መድረክ አዘጋጅቶአል::

ስጦታ ወደ ኢትዮጵያ ይላኩ

Check Also

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !!

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !! ********************************************** #ሼር እናድርግ #እናዛምት ከቅዳሜ ግንቦት 5/2015 …

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። መሳይ መኮነን

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። እነአብይ አሁን ብቻቸውን አይደሉም። ከእነጌታቸው ረዳ ጋር ተጣምረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.