Breaking News
Home / Amharic / አገር ማለት ምን ማለት ነው ???

አገር ማለት ምን ማለት ነው ???

 አገር ማለት ህዝቧ ማለት አይደለም እንዴ ? ሕዝብ ከሌላ አገር የለም፡፡
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኦሮሙማ መንግስት ጄኖሳይድ እየፈጸመ ነው፡፡ ስንት ሰው ቢጨፈጨፍ ነው እነ ነዓምን ዘለቀና ግንቦት ሰባቶች መንግስት መቃወም አለብን የሚሉት ? አንድ ሺህ? መቶ ሺህ ? አንድ ሚሊዮን ???? የስንት ሰው ሕይወት ቢያልቅ ነው ከንጹሃን ዜጎች ጎን የሚቆሙት ????
“አገር እንዳትበተን” የሚሉት የትኛዋን አገር ነው? እስቲ ሻሸመኔ ያሉትን ይጠየቁ:: እስቲ ወለጋ ልጆቻቸው የታረዱባቸው ቤተሰቦች ይጠይቁ ፡፡ እስቲ ቻግኒ ተፈናቃዮች ካምፕ ያሉትን ይጠይቁ፡፡ እስቲ ደሴና ሃይቅ ከወለጋ ተፈናቅለው መንገድ ላይ የተበተኑትን ይጠይቁ ፡፡ “አገር አላችሁ ወይ?” ቢባሉ ምን የሚመልሱ ይመስላቸዋል ?? እነ ነዓምን አገር የሚሉት የአማራ ማህበረሰብን የቀነሰች አገር ነው እንዴ???????
በጣም ያሳዝናል፡፡ አገር እንዳትበትን፣ ኢትዮጵጵያ አንድነቷ ተጠብቆ እንድትቀጠል ቢፈልጉ ኖሮ፣ ኢትዮጵያን እየበተነና እያፈረሰ ያለውን የአብይ መንግስት መሆኑ ተረድተው፣ ተደራቢና ተለጣፊ፣ አጨብጫቢ ዳንኪራ መቺ ከመሆን፣ መርህ ገዝቷቸው ጄኖሳይዶችን የዘር ጭፍጨፋዎችን በመቃወም አገር በታኞችን ለመታግል ይነሱ ነበር፡፡
የኦሮሞ ብልጽግናን ኦነግን መታገል ኢትዮጵያን የማዳን ትግል ነው፡፡ ለኦሮሞ ብልጽግናና ለኦነግ ተቃውሞ ሲቀርብ ለምን ማለት ወይንም ዝም ማለት ኢትዮጵያን በማፍረስ ሂደት ላይ ተባባሪ መሆን ነው፡፡
አገርን ለማዳን ከተፈለገ ኦሮሙማን መታገል ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ እነ ነ ዓምንን መስማት አገርን ለውድቀት መዳረግ ነው፡፡
 

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.