Breaking News
Home / Amharic / አዲሱ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ማን ናቸው?

አዲሱ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ማን ናቸው?

አዲሱ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ማን ናቸው?

ኮሚሽነር አበረ አዳሙ!!!

ተወልደው ያደጉት በቀድሞው አጠራር ጎጃም ክፍለ-ሀገር ቆላ ደጋ ዳሞት አውርጃ ውስጥ ነው። ኮሚሽነር አበረ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከጨረሱ በዃላ ፖሊስ ኮሌጅ አካዳሚ ውስጥ በመግባት በፖሊስ መኮነንነት ተመርቀዋል። በተለያዩ ክፍለ-ከተማዎችም ኢንስፔክተር እና ኮማንደር በመሆን አገልግለዋል።
=====

ህወሐት መራሹ የአፓርታይድ አገዛዝ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአማራ ብርቱ ነቀርሳ መሆኑን ቀድመው የተረዱት ኮሚሽነር አበረ ከጥብቅ የትግል አጋሮቻቸው ከነጄኔራል ተፈራና ጄኔራል አሳምነው ጋር በመሆን የወያኔን አገዛዝ ገልብጦ ለመጣል በተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ውስጥ ታሪክ ወደፊት ጎልጉሎ የሚያወጣው ብርቱ ጥረትና ትግል ፈፅመዋል።
=====

ኮሚሽነሩ ስለራሳቸው መናገር ስለማይወዱ ብዙዎቻችን ለኒህ ጀግና ሰው ታሪክ በእንግድነት ባጅተናል። አሁን ግን መነገር ስላለበት ኮሚሽነሩ ባይፈቅዱልንም የምናውቀውን ለመናገር ተገደናል። የአማራ ህዝብ በተለይም ወጣቱ የህግ ማስከበር ሀላፊነቱን በፍታውራሪነት የተረከቡት ሰው ማን እንደሆኑ በጥቂቱም ቢሆን ሊያውቅ ይገባል ብለን ስለምናምን ነው ይህንን ማድረጋችን።
=====

ኮሚሽነር አበረ የወጣትነት ዘመናቸውን የጨረሱት ነፍጥ አንስቶ ጫካ በመግባት ከወያኔ ሰራዊት ጋር ዕልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ነው። በመተከል ፡ በጋምቤላ፡ በአሶሳ፡ በሱዳን፡ በኤርትራ በርሃዎች ሰራዊት በማደራጀትና በማንቀሳቀስ ለወያኔ የዕግር እሳት ሆነው መቆየታቸውን የአርበኞች ግንባርና የአዴሃን ፋኖ ጓደኞቻቸው ምስክርነት ሰጥተዋል። በመጨረሻም ኮማንደር አበረ ውጊያ ላይ እንዳሉ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት በድርጅታቸውና በአለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ትብብር UNCHR ዕርዳታ ወደምዕራብ አውሮፓ ተወስደው የህክምና ዕርዳታ በማግኘት ሂወታቸው ሊተርፍ ችሏል።
=====

ኮሚሽነር አበረ ከጉዳታቸው ካገገሙ በዃላም አርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ ሃላፊነቶች ላይ በመሆን ባመኑበት መስመር ትግላቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ቢሆንም ድርጅቱ በሚሰራቸው ስራዎች ሳይስማሙ በመቅረታቸውና ጉድለቶች እንዲስተካከሉ አበክረው በመታገላቸው ለከፍተኛ ጫና እና ውግዘት ተዳርገው መኖራቸው ይታወቃል። ቢሆንም ድርጅቱን ለማንም ጥየ አልሄድም፡ ድርጅቱ የሚደገፈው በብዙ አማሮች ነው፡ በድርጅቱ ተስፋ የጣሉ አማሮችን አደራ አልበላም፡ ውስጥ ሆኘ የቻልኩትን ያክል እታገላለሁ በማለት እስከመጨረሻዋ ሰዐት ድረስ የድርጅቱን ብልሹ አመራሮችና ስራ በቆራጥነት ሲታገሉ ኖረዋል። ጎን ለጎንም ከአማራ ወጣቶች ጋር በመገናኘት ጠንካራ የሆነ የአማራ ድርጅትና ሚዲያ እንዲፈጠር ሌት ተቀን ሰርተዋል። ከገዘፈው የትግል ልምዳቸውም በማካፈል ልዩ ልዩ የፓለቲካና የህዝባዊ አደረጃጀት ስልጠናዎችን ሰጥተዋል። በሂደቱም ብዙዎቻችን የአማራ ልጆች ለኒህ ሰው ላቅ ያለ ፍቅርና ክብር አለን። በዚህ ረገድ እኒህ ሰው ስላደረጉት አስተዋፅኦ ቀሪውን እነምስጋናው አንዷለም፡ ራስ ሀመልማልና ቴዎድሮስ አምደፅዮን፡ ተካበ ጌታቸው እማኝነታቸውን ይሰጣሉ ብየ እገምታለሁ።
=====

ኮሚሽነር አበር በአለምአቀፍ ህግ የማስተርስ ዲግሪ ሲኖራቸው ልዩ ልዩ አለምአቀፍ ሰብዐዊ ድርጅቶችን በማማከር ስራ ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል።
ኮማንደር አበረ የሁለት ህፃናት ልጆች አባት ሲሆኑ የአማራ ክልል መንግስት “ና! ታስፈልገናለህ!” ብሎ ሲጠራቸው የሞቀ ኑሮአቸውንና ለጋ ቤተሰባቸውን ትተው ወደሃገራቸው በመመለስ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽነርነት ስልጣን ተረክበው ያደጉበትን ትግል ቀጥለውበታል።
====

የአማራ ወጣቶች ከኒህ ጀግና ኮሚሽነር ጋር በመሰለፍ እርዷቸው። ለኒህ ሰው ከማንም በላይ የሚያስጨንቃቸው በአማራ ወጣቶች ላይ ሲደርስ የኖረው ዘርፈ ብዙ በደል ባጭር ግዜ ውስጥ የሚለወጥበት ሁኔታ ነው። በየአካባቢው ያላችሁ የአማራ ወጣቶች ማህበራት ከኒህ ሰው ጋር እየተገናኛችሁ ተወያዩ። ለክልላችሁ ሰላምና ልማት አብራችሁ ስሩ። 
=====

ኮማንደር አበረ ያላቸውን አገርና አለምአቀፍ ልምድ ተጠቅመው ለዶር አምባቸው ታላቅ ብርታት እንደሚሆኑ እምነታችን ፅኑ ነው።
=====

መልካም የስራ ዘመን ኮማንደር!!!

እግዚአብሄር ከእርሰዎ ጋር

ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

Check Also

ኤርትራ ከአማራ ህዝብ ጋር መቆሟን አስታወቀች !

Related Posts:የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ የነበረው ችግር እንደተፈታ አስታወቀች::ኤርትራ ለአማራ ልዩ ኃይል እና …

ጥቁር ጣልያን በአዲስ አበባ። ለታሪክ አስቀምጡት። ሼር

Related Posts:የመሬት ዝርፊያ በአዲስ አበባ !የኦሮሞ ባንዲራ በአዲስ አበባ !በአዲስ አበባ የሚሰራዉን ተንኮል ተመልከቱና ፍረዱ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.