Breaking News
Home / Amharic / አብይ አማራውን በምርጫ አታሎ ከተመረጠ በኋላ ክዶታል!

አብይ አማራውን በምርጫ አታሎ ከተመረጠ በኋላ ክዶታል!

ተናግሬአለሁ!
Dr. Agegnehu !
 
አብይ አማራውን በምርጫ አታሎ ከተመረጠ በኋላ ክዶታል። አሁን ህወሃቶች ተዋግተው ራያንና ወልቃይትን መረከባቸው አይቀርም። የምጠረጥረው እነ አብይ ህወሃቶችን ደግፈው ወልቃይትንና ራያን እንዲረከቡ በማድረግ የአገኘሁ ተሻገር በህወሃት እንዲበላ በማድረግ የክልሉ ህዝብ አሁንም መሪ አልባ(መሪ ባይሆኑም) በማድረግ ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ የማድረግ ፕሮጀክታቸውን አሳክተው ሀገሪቱን ይበትናሉ። የመጨረሻው መጨረሻ ላይ ደርሰዋል። ኦሮሙማ እየተሳካለት ነው። ለማኙ አገኘሁም ልመና እንዲወጣ አድርጎታል። አማራው መዋጋት ቢኖርበትም ጦርነቱን በቶሎ አሸንፎ እንዲያጠናቅቅ አብይ አይፈቅድለትም። አትልፉ!! ዝም ብላችሁ ህዝብ ሳታስጨርሱ ትኩረት ማድረግ ታለባችሁ የኦሮሙማ ጉዞ ላይ ነው።
 

ራያን በተመለከተ – ግርማካሳ

አንዳንድ መረጃዎች ልስጣችሁ፡፡ በነገራችን ላይ ጋዜጠኛ ወይንም ተከፋይ ብሎገር አይደለሁም። እኛ እዚህ የምናደርገውን የመደበኛ ሜዲያ አባላት ነበሩ መስራት ያለባቸው።፡መረጃዎች እየሰበሰቡ፣ ወደ አካባቢው እየደወሉ ኅዝብ ማወቅ ያለበትን እንዲያውቅ ማድረግ። እድነ አንድ ትልቅ ሜዲያ ሁለት ሶስት ጊዜ እንድናጣራ መጠበቅ የለባችሁ። የደረሰንን ስናቀርብም፣ ስህተት ሆኖ ሊገኝም ይችላል። ስለዚህ ከኛ የሰማችሁትን ቢቻል ከሌላ ሰውም ላማጣራት ሞክሩ።
ቀደም ሲል
– ወያኔዎች አላማጣን ለመያዝ እንደተንቀሳቀሱ ገለዤ፣
– የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ፣ በአላማጣ ህዝቡ፣ ሚሊሺያው ፣ የአማራ ልዩ ኃይል የወያኔዎችን ጥቃት ለመመከት እንደተዘጋጀ የገለጹበትን ቃለ ምልልስ ሼር አድርጌ
– ወያኔዎች ኮረምን መያዛቸውን በተመለከተም ፣ እነ ሮይተርስ ቢዘግቡትም፣ መንግስት መግለጫ እስኪሰጥበት ድረስ ፖስቶቼንም ማንሳቴ አሳወቄ
ነበር፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በፎት በደረሰኝ መረጃ፣ የአሸባሪው የህወሃት ቡድን በዋጃ አላማጣ በኩል ቆርጦ ለመግባት ሲሞክር የአማራ ሚሊሺያና እና በአማራ ልዩ ሀይል ባደረገው የመከላከል ተግባር ገፍቶ መሄድ አልቻለም፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ፣ ወያኔ አስታጥቆ የላካቸው ሕጻናት ታጣቂዎች ሞተዋል፡፡ ያው ጦርነት እንደመሆኑም፣ ከአማራ ሚሊሺያና ልዩ ኃይል አባላትም መካከል መስዋእት የሆኑም አሉ፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ አላማጣ ከአሸባሪው የወያኔ ቡድን ነጻ እንደሆነችና በጣም ከፍተኛ ጉዳት በአማራ ልዩ ኃይል ወያኔ ስለደረሰባት ከአላማጣ ርቃ ማፈግፈጓን ነው የደረሰኝ መረጃ የሚገልጸው፡፡
ኮረምን በተመለከተ ፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ኮረምን አልፍ እስከ ማይጨው ደርሶ ነበር። ግን እንዲወጣ መታዘዙን ነው መጀመሪያ የወጡ መረጃዎች የሚያመላክቱት። ሆኖ ከአላማጣው ሽንፈት በኋላ፣ በመልሶ ማጥቃት ኮረምም ተመልሳ በአማራ ልዩ ኃይል ከወያኔ ነጻ የመውጣት እድሏ ሰፊ ነው።
ሕወሃት በአማራ ማህበረሰብ ላይ ጦርነት አውጃለሁ እንዳለችው ሁለት ጊዜ በወልቃይት ጥቃት ለማድረግ ሞክራ ተደምስሳለች፡፡ የራያው ጥቃት ግን እጅግ በጣም የጠነከረ ጥቃት ነበር፡፡
የፌዴራል መንግስቱ ተኩስ አቁሚያለሁ እያለ ሕወሃት በዚህ መልኩ ራያና ወልቃይት እየገባች የሕዝቡን ኑሮ ስታውክ ፣ ሁሉን ነገር ለአማራ ክልል ብቻ ትቶ፣ እስከ መቼ ድረስ ዝም ብሎ እንደሚጠብቅ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የራያና ወልቃይት ሕዝብስ ዛሬ ነገ ጦርነት ይነሳብኛል ብሎስ እስከመቼ፣ መንግስት እያለ በመፍራት ይኖራል ????
በኔ እይታ የአማራ ክልል መንግስትና የአማራ ብልጽግና ፡
1ኛ እንደ አብን ካሉ ጋር አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ቁጭ ብሎ ስትራቲጂ ማውጣት አለበት፡፡ አንድ ሆነው ተናበው መስራት መጀመር አለባቸው፡፡
2ኛ የፊዴራል መንግስቱ በወልቃይት ላይ ያለውን ዝልፍልፍ፣ እዚህና እዚያ የሚረግጥ፣ ከሕወሃት ጋር በሚስጥር ሳይስማማ አይቀርም በሚል እንዲጠረጠር ያደረገውን አቋም እንዲያስተካክልና በአስቸኳይ በነወልቃይት ዙሪያ የፖለቲካ ውሳኔ እንዲወሰን፣ በወልቃይትና በራያ ወያኔዎችን እየመከተ ላለው የአማራ ክልል ሰራዊት አስፈላጊውን የትጥቅ፣ የሎጂስቲክ የባጀት ድጋፍ እንዲያደርግ እና የመከላከያ አየር ኃይልና መካናይዝድ ብርጌዶች በዚያ እንዲሰማራ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ተገዶ የተጠየቀውን እንዲያደርግ ማስገደድ መቻል አለበት። እነዚህን ማድረግ ያልቻለ ወይም ፍቃደኛ ያልሆነ የፌዴራል መንግስት የአሸባሪው ሕወሃት ተባባሪ ብቻ ሳይሆን የአማራ ማህበረሰ ጠላት የሆነ መንግስት መሆኑን በመገንዘብ ከአብይ አገዛዝ ጋር እስከመፋታት መድረስ መቻል አለበት።
ፈረንጆች deterrence የሚሉት ነገር አለ። የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከተጠናከረ ወያኔዎች የኃይል ሚዛኑን አይተው የጦርነት ነጋሪታቸውን ያቆማሉ። በዚያ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ይረዳል። ከአማራ ማህበረሰብ የሚሞት አይኖርም፤ የትግራይ ወጣቶች ሕይወት ይተርፋል።
 
 

Check Also

የሺመልስ አብዲሳ ንግግር: “ነፍጠኛና ወያኔን አሸንፈናል”!

Related Posts:የሺመልስ አብዲሳ ግጭት ቀስቃሽ ንግግር !!አሸንፈናል ! እንኳን ደስ አለን!መልእክት ለዶ/ር አብይና ለሺመልስ አብዲሳ!የግል …

የአማራ ክልል ምክር ቤት ይልቃል ከፋለን (ዶ.ር) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡

“ዓላማችን ወራሪውን ቡድን አቁስሎ መተው ብቻ ሳይሆን ዳግም የሀገራችን ስጋት እንዳይሆን ማስወገድ ብቻ ነው” የአማራ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.