Breaking News
Home / Amharic / አብኖች እያሉ ያሉት “አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፤ ይህን የሚቃረን ካለ ግን…

አብኖች እያሉ ያሉት “አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፤ ይህን የሚቃረን ካለ ግን…

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ፀጋዬ!
~~
1.
የአንድነት ፖለቲካ አቀንቃኝ ነኝ ብሎ አዲስ አበባ የከተመው ሃይል ለውጡ እንዳይቀለበስ በሚል “ታከለ ኡማን አትተቹ፤ አብይን አትተቹ” ከማለት ያለፈ ለአዲስ አበባ የሚጠቅም አቋም አላየሁበትም።
2.
የአንድነት ሃይሎች ለአብይ ከማሸርገዳቸው የተነሳ “በስመ አብ” ከማለት ይልቅ “በስመ አብይ” ማለት የሚቀላቸው ሁሉ ይመስለኛል።
3.
አብኖች እያሉ ያሉት “አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፤ ይህን የሚቃረን ካለ ግን ከምኒሊክ ጀምሮ ስለነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከሁለትና ከሶስት መቶ አመታት በፊት ስለነበረችው በረራ ከተማ የተፃፈውን ታሪክ ለማውሳት እንገደዳለን” ነው።
4.
አዲስ አበባ ላይ እየተሰራ ያለውን ድብቅ ሴራና ተንኮል እየታገሉ ያሉት፣ ትክክል ያልሆኑ አካሄዶችን እያጋለጡና መረጃውን እያወጡ ያሉት አብኖች ብቻ ናቸው።
5.
የብሄር ፖለቲካ ደጋፊ አይደለሁም፤ የብሄር ፖለቲካ ባይኖር እመርጣለሁ ግን ማንንም ለመጉዳት ካልሆነና ራስን ለማዳን ከተደረገ አደረጃጀት ጋር ምንም ፀብ የለኝም።
6.
በነገራችን ላይ “አዲስ አበባ የሁላችንም ናት” ብሎ ከሚያምንና ከታሪክ ጋር ፀብ ከሌለው ድርጅት ጋር አብሬ ለመስራት ፈቃደኛ ነኝ። አብኖች ባሏቸው አቋሞች ባብዛኞቹ 100% እስማማለሁ።
~~
አዲስ አበቤዎች #ከአብን ጋር ወደፊት!
#ተዘጋጁ!
#አዲስአበቤነታችሁን_ከፍ_ለማድረግ_ተዘጋጁ!

Check Also

ኤርትራ ከአማራ ህዝብ ጋር መቆሟን አስታወቀች !

Related Posts:የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ የነበረው ችግር እንደተፈታ አስታወቀች::ኤርትራ ለአማራ ልዩ ኃይል እና …

ጥቁር ጣልያን በአዲስ አበባ። ለታሪክ አስቀምጡት። ሼር

Related Posts:የመሬት ዝርፊያ በአዲስ አበባ !የኦሮሞ ባንዲራ በአዲስ አበባ !በአዲስ አበባ የሚሰራዉን ተንኮል ተመልከቱና ፍረዱ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.