Breaking News
Home / Amharic / አብን ተወደደም ተጠላም የአማራ የሕልውና አደጋ የወለደው የአማራ ባለጉዳይ ነው።

አብን ተወደደም ተጠላም የአማራ የሕልውና አደጋ የወለደው የአማራ ባለጉዳይ ነው።

ብአዴን ስሪቱ ጸረ አማራ ስለሆነ ወደ አማራ ለመቅረብ በሞከረ ቁጥር የበለጠ እየራቀ የሚሄድ ድርጅት ነው። አብን ደግሞ ተወደደም ተጠላም የአማራ የሕልውና አደጋ የወለደው የአማራ ባለጉዳይ ነው። ብአዴን ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምክትልነትን ነባር ይዞታው አድርጎ ጌቶቹ እየሆኑ ለሚሰየሙ የበላዮቹ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነ ሽንፍላ ነው። ብአዴን የተፈጠረውና ዛሬም ድረስ የሚሰራው የአማራ ያልሆነውን ጸረ አማራ ነገር ሁሉ በአማራ ላይ ለመጫን ነው። ብአዴን የተቋቋመው የአማራ ክልል ያልሆነውን የአማራ ጠላቶች እቅድ የአማራ ክልል ለማድረግ፤ ሕገ መንግሥት የሚሉትን አማራ ያልተሳተፈበትንና ከአማራ አንጻር የተዋቀረውን የፋሽስት ወያኔ የቅሚያና የግድያ ደንብ የአማራም ሕግ ለማድረግ መለስ ዜናዊ መንግሥታዊ ያደረገውን ሰይጣናዊውንና ጸረ አማራውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መመሪያው አድርጎ የተፈጠረ ነውረኛ ድርጅት ነው።

በአማራ ላይ የተጋረጠው የሕልውና አደጋ የወለዳቸው የአብን ልጆች ቀደም ሲል የሕወሓት እንደራሴል፤ አሁን ደግሞ የኦሕዴድ ጉዳይ አስፈጻሚ ከሆነው ከብአዴን ጋር አብሮ ለመስራት ማሰባቸው ብአዴን የአማራ ውክልና እንዳለው እውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል። በኔ እምነት አማራ መታገል ያለበት ከብአዴን ጋር አብሮ ለመስራት ሳይሆን የአማራ ውክልና ሳይኖረው የአማራን ሳይሆን የጌቶቹን ጉዳይ ለማስፈጸም የተሰየመበትን ወንበር ለመንጠቅና ለአማራ ለማድረግ መሆን ይኖርበታል። የጌቶቹ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው ብአዴን ከአብን ጋር እንዲሰራ መፍቀድ የአማራ ባለጉዳይ የሆነውን አብንን ተጠግቶ የአማራ ባለጉዳይ ተደርጎ እንዲቆጠር እድል ማመቻቸት ነው፤ አልፎም የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው ብአዴን መቆሚያ መሬትና ማስቻያ ሜዳ እንዲያገኝ ማገዝ ነው። ዛሬ አብን ብአዴንን የአማራ ባለጉዳይ አድርጎ ከብአዴን ጋር ከተዋዋለ ነገ በአማራ ጉዳይ ጌቶቹ ብአዴን ይወከል ሲሉ ብአዴን አማራን አይወክልም ብሎ ለመናገር የሚያስችል አመክንዮ ሊኖረው አይችልም።

መታወቅ ያለበት እውነት ብአዴን ሲጠናከር አማራ ይዳከማል፤ አማራ ሲጠናከር ብአዴን ይዳከማል፤ ብአዴን ሲዳከም እንደራሴ ያደረጉት በአማራ መካከል መቆሚያ ያጣሉ፤ አሁን አማራ እየተጠናከረ ባለበት ሁኔታ ነፍስ አልባው ብአዴን ነፍስ ካለው አብን ጋር የሚመሰርተው ኅብረት ከተዳከመበት አፈር ልሶ እንዲሳ የሚያደርግና አማራን የሚያዳክምበት ጉልበት እንዲያገኝ የሚያደርግ ነው።

ኦሕዴድ ወይንም ኦነግ ኦሮሞን እንወክላለን ቢሉና ኦሕዴድ ከኦነግ ጋር በአንድ ቢሰለፉ ሁለቱም የኦሮሞ ባለጉዳይ ስለሆኑ ነው። ብአዴን ግን ጸረ አማራ እንጂ የአማራ ወኪል ተደርጎ ሊቆጠር አይችልም። ስለዚህ ብአዴንንና አብንን በአንድ ማሰለፍ አፕልና ብርቱካን እንደማደባለቅ አይነት በሁለቱ መካከል ያለውን ተቃርኖ አለማጤን ነው። አብን የሚበላ አፕል ሲሆን ብአዴን ደግሞ የተበላሸ ብርቱካን ነው። የተበሳሸ ብርቱካን ደግሞ እጣ ፋንታው መጣል ነው። ንብ እና ዝንብ ማኅበርተኛ ሆነው ማር ሊሰሩ አይችሉም፤ ቢሰሩም እንኳን ውጤቱ ማሩን ማቆሸሽ ነውና አብን ብአዴን የጌቶችን ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲል ዝንብ አድርጎ ሊያጠፋው ወዳዘጋጀለት ወጥመድ ውስጥ እንዳይገባ መጠንቀቅ ያለበት ይመስለኛል።

ሕዝባችን በየአካባቢው ባደረጋቸውና እያደረጋቸው በሚገኙ ምድር አንቀጥቅጥ ጸረ ፋሽስት ወያኔና እንደራሴዎቹ ተጋድሎና በከፈለው ከባድ መስዕዋትነት ርስ በርሱ ሊተማመንና አብሮ ሊሰራ የሚያስችል የጋራ ትግል እርሾ ፈጥሯል። በሌላ አነጋገር ዛሬላይ አማራው ራሱንና ወገኑን ከፋሽስት ወያኔ ርዝራዦችና የጌቶቹ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የአማራ ባለጉዳይ ካልሆነው ከብአዴን ለመላቀቅ የሚችልበት መተማመን ላይ ደርሷል። ዛሬ ላይ ሕዝባችን ሳይፈራ ከወንድሙ ጋራ በፋሽስት ወያኔ ርዝራዦችና የአማራ ባለጉዳይ ባልሆነው በብአዴን ላይ መዶለት ይችላል። በዚህ ማስቻያ ሜዳ ላይ መካሄድ ያለበት ትግል ብአዴን በጌቶቹ እንደራሴነት በሚገዘግዛቸው አካባቢዎች ሁሉ ነጥቆ በመውሰድ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነውን ብአዴንን ማቆሚያ ማሳጣት እንጂ ለብአዴን ሕጋዊነት በማላበስ ስር እንዲሰድ እድል ማመቻቸት መሆን የለበትም።

ባጭሩ አማራው በመየንደሩ፣ በየሰፈሩ፣ በየቀበሌውና በየወረዳው የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው፣ የጸረ አማራው ሥርዓት በእንደራሴነት ተሰይሞ ፍዳችንን የሚያራዝመውን ብአዴንን ማቆሚያ እንዲያጣ በማድረግ፤ የየራሱን አካባቢ ሕጋዊነት ከሌለው ከእንደራሴው ብአዴን አገዛዝ ነጥቆ በመውሰድ የባዕድ ምንደኞች በመሆን ተጭኖት የኖረውን ነውረኛ ድርጅት ነቅሎ ጥሎ ራሱን ማስተዳደር በመጀመር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋራ በጋራና በእኩለት የሚኖርባትን አገር፣ ሕግና ሥርዓት ለመመስረት መደራደር መጀመር አለበት።

[የግል አስተያየት]

Check Also

ልደቱ አያሌው ከኤርፖርት እንዲመለስ ተደረገ!

የአብይ አህመድ አስተዳደር እልም ያለ አምባገነን መንግስት ከወያኔ የባሰ ነው:: ቺግሩ በሁሉም ሰው ላይ ሊደርስ …

ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የዉይይት መድረክ እነሆ ! እንዳይቀሩ !

Related Posts:ለአማራ ምሁራን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የቀረበ ጥሪ !ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ –አብን ብሔራዊ ምክር ቤት …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.