Breaking News
Home / Amharic / አብንን በተመለከተ ጥያቄዎች !

አብንን በተመለከተ ጥያቄዎች !

አብንን በተመለከተ ጥያቄዎች የምትጠይቁኝ አላችሁ:: አውቃለሁ ብዙ መደናገር አለ:: ድርጅቱ ስብሰባ አድርጎ የሚወስነውን ማየት ጠቃሚ ነው::
አቶ ጣሂር መሃመድና ወንድም በለጠ ሞላ የተሰጣቸውን ስልጣን ተርክበው ቃለ መሃላ አድርገዋል:: ያንንም በማድረግቸው እንደ ከሃዲ በአንዳንዶች እየተቆጠሩ ነው:: ያ ስህተት ነው::
የፓርቲው አባላት በሰሜን በህልውና ጦርነት ውስጥ ያሉ አሉ:: ተሰባስበው ስብስባዎች ማድረግ የሚችሉበት ሁኔታ እልነበረም:: ፓርቲው ተሰብስቦ ውሳኔ እስኪሰጥ በጊዚያዊነት ለመስራት መዘጋጀታቸው ችግር የለውም::
ፓርቲው ስብሰባ ሲያደርግ ከአራት ነገሮች አንዱ ነው ሊሆን የሚችለው ብይ አስባለሁ:
1) “ከብልፅግና ጋር በአገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት የግድ የመንግስት አካል መሆን አያስፈልግም” በሚል እነ በለጠ ሞላ የተሰጣቸውን ሹመት እንዲመልሱ ሊወስን ይችላል:: ያኔ እነ በለጠ እምቢ ካሉ በይፋ አብንን ለቀው ብልፅግናን ተቀላቀሉ ማለት ነው የሚሆን:: አብን አዲስ አመራር መርጦ ይቀጥላል:::
2) ከብልፅግና ጋር ሲሰራ ጊዜ ገደብ ተቀምጦ መሰረታዊ በሆኑ እንደ ህገ መንግስት ማሻሻያዎች : የአወቃቀር ለውጦች : ተፈናቃዮችን የመመመስ : ወያኔን ከአማራ ክልልና ከአፋር የማስወጣቱና በወለጋና መተከል ጄኖሳይዶችን የማስቆም ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ስራዎች የማይሰሩ ከሆን ሃላፊነት የወሰዱ ለቀው እንደሚወጡ የሚገልፅ መግለጫ በማውጣት የነ በለጠ ሞላን ጊዚያዊ ውሳኔ በጊዚያዊነት ሊያፀድቅ ይችላል::
3) በድርጅቱ ውስጥ በዚህ ጉዳይ መክፋፉል ተፈጥሮ ድርጅቱ ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል:: ቀላል የማይባል የአብን አባል ደስተኛ ካልሆነ እነ በለጠ ለድርጅቱ አንድኑት ሲሉ ሹመታቸውን መተው አለባቸው:: ወይም በፍቃዳቸው መልቀቅ ኑው የሚሻለው:: ለሶስት ሰዎች ተብሎ ድርጅት መፍረስ የለበትም::
4) ፓርቲው ምንም አይኑት ቅድመ ሁኔታዎችና ቀነ ገደቦች ሳያስቀምጥ ሶስቱ ተሹዋሚዎች እንዲቀጥሉ ይስማማል:: ይሄ ደግሞ በይፋ እብን የብልፅግና ቅርንጫፍ ተደርጎ እንዲወሰድ የሚያደርግ ነው የሚሆነው::
በኔ እይታ አብኖች ምክሬን ከሰሙ የምመርጥው ተራ ቁጥር ሁለትን ነው:: ያ ካልሆነ ደግሞ ተራ ቁጥር አንድ:: ከዚያ ውጭ ያሉ አማራጮች ለአብን የውድቀት አማራጮች ናቸው::
-Girma Kassa

Check Also

የፓርላማ ተወካዮች ፀረ አማራ የሆኑ ዝርዝር ከነስልክ ቁጥራቸው

Related Posts:የህዝብ ተወካዮች ስልክ ቁጥር ዝርዝር።ይሄ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው ሀንጋሳ ኢብራህም የሚባለው ኦህዴድን ብልጥግናን ወክሎ …

የህዝብ ተወካዮች ስልክ ቁጥር ዝርዝር።

ሼር ይደረግ! የህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት በነገው እለት በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀውን የእልቂት አዋጅ ለማፅደቅ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.