Breaking News
Home / Amharic / አስቸኳይ የአቋም መግለጫ ከአማራ ተማሪዎች !

አስቸኳይ የአቋም መግለጫ ከአማራ ተማሪዎች !

አስቸኳይ የአቋም መግለጫ ከአማራ ተማሪዎች !

ባለፉት ሁለት ሶስት ቀናት የአማራ ውድ ልጆች በሀረማያ በአሶሳ በመዳወላቡ እና ሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች መጠነ ሰፊ ጥቃት በኦሮሞ ተወላጆች በኩል ሲደርስባቸው እንደቆየ ይታወቃል፡፡

በትናንትናው እለትም እስካሁን እንዳሳለፍነው ሶስት ሬሳ ከአሶሳ በስጦታ ተልኮልናል በዚህ ረገድ እኛ ለሰላም ባለን ቁርጠኛ አቋም በክልላችን የሚገኙ የሌሎች ክልል ተወላጆች ሳይሳቀቁ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ሰፊ እንቅስቃሴ አድርገናል፡፡አሁን ላይ የአማራ ተማሪዎች መገደላቸው ሳያንስ በጅምላ እስርና ከግቢ መባረር እየደረሰባቸው ይገኛል በዚህም ምክኒያት ከጥቃት ሸሽተው ወደተለያዩ ጫካዎች ተበትነው ይገኛሉ፡፡

ግቢ ያልለቀቁትም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ የሚሹ ቢሆንም አተማ ነገሩን በሰከነ መልኩ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል በዚህም ረግድ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንንን ፣የትምህርት ሚኒስቴር ዲኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱን ለማነጋገር ሞክረናል፡፡

ከዚህም አልፈን የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር አመራሮችን እና የቄሮ ተወካይ የተባሉትን ለሰላማዊ ድርድር ጥያቄ አቅርበናል፡፡ከሁሉም ዘንድ አሁን ለሚደርሰው ጥፋት የሚደርስ አስቸኳይ መፍትሄ እንደማናገኝም ተረድተናል፡፡ውድ የአማራ ልጆች ሆይ አተማ ወጣትነት የገፋው ግብታዊ ውሳኔ እንዳልወሰነ ከላይ የጠቀስናቸው መረጃዎች በቂ ናቸው ስለሆነም ህይዎታቸው በግፍ ያለፈ የአማራ ልጆች ሬሳቸው በክብር ወደ ትውልድ ስፍራቸው እንዲመለስ፣እየታደኑ የታሰሩ የአማራ ተማሪዎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ፣ስጋት ላይ የወደቁ የአማራ ተማሪዎች አስፈላጊው የህግ ከለላ እንዲሰጣቸው ስንል እንጠይቃለን፡፡ከላይ የቀረቡት ጥያቄዎች መልስ እስከሚያገኙ የሚቆይ የአንድ ሳምንት የትምህርት ፕሮግራሞች መቋረጥ በሁሉም የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም አማሮች በሚማሩባቸው ሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲተገበር ወስነናል፡፡

በዚህ እንቅስቃሴ ወቅት በመንግስት አመራሮች በኩል የሚደረግ ትንኮሳ እና ጥቃት እንቅስቃሴያችንን ወደ ሌላ ምዕራፍ ሊዎስደው እንደሚችል እያሳሰብን የጸጥታ አካላት ጥያቄያችን ህገመንግስታዊ መሆኑን ተረድታችሁ ከማደናቀፍ እንድትታቀቡ እናሳስባለን፡፡

ውድ የአማራ ልጆች ሆይ የጭንቁ ዘመን ማለቂያው አሁን እንዲሆን በያላችሁበት እንድታግዙን እያሳሰብን በዚህ የመከራ ሰዓት ያልደገፈን ማንኛውም የአማራ ማህበር፣ምሁር፣ወጣት በሙሉ የወንድሞቹ ደም በእጁ እንዳለ ይወቅ፡፡ሁሉም የአማራ ተማሪ በአንድነት እንዲቆም እያሳሰብን ምንም ዓይነት የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይኖር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል፡፡

መንግስት ጥያቄው ምንም ፖለቲካዊ ሽፋን የሌለው የማንም እጅ የሌለበት ፍጹም የአማራ ተማሪዎች ጥያቄ መሆኑን በማመን ምንም ዓይነት ቅድመ ፍረጃ ሳያደርግ መልስ እንዲሰጥ እናሳስባለን፡፡ይሄ የመጀመሪያ እንቅስቃሴ ሲሆን መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ካልሰጠ ለሚፈጠረው ጥፋት አተማ ሃላፊነት እንደማይወስድ ከወዲሁ እንገልጻለን!!!!!! አባላቶቻችን ፖስቱ ለሚመለከተው ሁሉ እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን፡፡

አማራ በከዋክብት ልጆቹ ይደምቃል!!!!!

® የአማራ ተማሪዎች ማህበር/አተማ

Check Also

የፓርላማ ተወካዮች ፀረ አማራ የሆኑ ዝርዝር ከነስልክ ቁጥራቸው

Related Posts:የህዝብ ተወካዮች ስልክ ቁጥር ዝርዝር።ይሄ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው ሀንጋሳ ኢብራህም የሚባለው ኦህዴድን ብልጥግናን ወክሎ …

የህዝብ ተወካዮች ስልክ ቁጥር ዝርዝር።

ሼር ይደረግ! የህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት በነገው እለት በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀውን የእልቂት አዋጅ ለማፅደቅ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.