Breaking News
Home / Amharic / አማራን ያስጨፈጨፈው ሽመልስ አብዲሳ ነው። – Hangasa Ibrahim

አማራን ያስጨፈጨፈው ሽመልስ አብዲሳ ነው። – Hangasa Ibrahim

ዶ/ር ዐብይ፣ ሽመልስ አብዲሳን እሰር!!

በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል

አቶ ሀንጋሳ ዛሬ ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ::

– አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣
– አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር ቤት በማስገባት ሰላም ይስፈን፣
– ዶ/ር አብይ ከለማ የቀረበ ወዳጅ አልነበረህም በሱ ላይ የጨከንክ በሽመልስ ላይ መጨከን እንዴት አቃተህ፣
– ዶ/ር አብይ የኦሮሚያ ክልልን ካቢኔን አፍርሰህ በአዲስ ተካ፣ ይህንን ካላደረክ አማራ እንዲጨፈጨፍ የምታደርገው አንተ ነህ ወደሚል ድምዳሜ እሄዳለው፣
– እኔ ብሞት እንኳን ወንድሞቼ (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች) እውነቱን ስሙ (እወቁት)
– ዶ/ር አብይ መሬት ላይ ወርደህ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቅ፣ አንተን እና ህዝቡን ለይተው ሊበሉህ ደጅህ ላይ የቆሙ ጅቦች አሉና ቅደማቸው፣
– ዶ/ር አብይ እሰር፣ ቀፍድድ፣ ወስን እና ጨክን፤ አንተን ገለው ቤተመንግስት ሊገቡ ያሰቡ ሰዎች ሰፈራችን ላይ ደርሰዋል (አጃቢዬን ዛሬ ገለውታል ነገ እኔንም ቢገሉኝ እውነት እናገራለሁ)
– ኦነግ ለዘመናት ወለጋ ውስጥ ነበር፣ ኦነግ ሀረርጌ እና አርሲ አለ፤ አሁን ኦነግ የመግደያ፣ የመጨፍጨፊያ አቅሙን ከየት አመጣው ብለህ ጠይቅ፤ እኔ ግን እነግርሃለው ሀይሉን እና አቅሙን ያገኘው ከክልሉ መንግስት ነው
– እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ ሊጨርሱህ ነው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ
– አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣
– የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ስንት ገዳይ እንፈልጋለን፣ ለፍትህ እናቀርባለን ብላችሁ ስንቱን አሳካችሁ፤ ምኑንም አላሳካችሁም ወሬ ብቻ፤ በዚህ መሃል ግን ወንድም እና እህቶቼ (አማራዎች) ወለጋ ውስጥ አለቁ
– መቼ ነው ዶ/ር አብይ ከአትክልት ስራ ወጥተህ ጠንከር ያለ ስራ የምትሰራው፤ መቼ ነው የከበበህ መከራ የሚታይህ፣ መቼ ነው ሊበላህ የተነሳው ጅብ የሚታይህ
– ዛሬ አማራን እየገደለ የሚመጣው ሀይል መቆሚያው አንተ ቤት (አራት ኪሎ) ነው
– ሽመልስ እና ፍቃዱ ታደሰን ወደ እስር ቤት ካላስገባህ ከዚህ ጥቃት ጀርባ አንተ አለህ ማለት ነው፣
– ለአብዲ ኢሌ ክፍት የሆነ እስር ቤት ለሽመልስ እና ፍቃዱ ዝግ የሆነው ኦሮሞ ስለሆኑ ነው ወይስ አዛዡ አንተ ስለሆንክ
– አጉል ጥጋብ እና ሁኔታ ውስጥ ገብታችሁ የአማራን መገደል የምትደግፉ የኦሮሞ ወንድሞቼ እረፉ (ዋ እረፉ ብያለሁ)፣ ነገ ጠዋት አማራ ኦሮሞ ላይ እንዲነሳና እርስ በእርስ እንድንትላለቅ ነው ፍላጎቱ፣ የኦሮሞ ወንድሞቼ ንቁ (በጭራሽ በኦሮሞ ብልጽግና ገመድ እንዳትጠለፉ)
– አንተን (አብይን) እያስጠሉ ያሉት ዙሪያህን የከበቡህ እና ሰው ያደረካቸው መናዎች ናቸው
– ኦሮሚያ የሁላችንም ቤት ነው፣ አማራው ተመርጦ ሲታረድ ለምን ካላልን ነገ መከራው በኛና በልጆቻችን ላይ ይደርሳል
– ዶ/ር አብይ እስኪ ድንገት ጅማ፣ ሀረርጌ፣ ገራሙለታ፣ አርሲ፣ ወለጋ፣ ባሌ፣ ጭሮ ሂድና ህዝቡን ስማ (መሬት ላይ ያለውን መከራ እይ)፣ ያኔ ምን አይነት የሚመር ዜና እንደምትሰማ እነግርሃለው
– የኦሮሞ ካቢቤ ተጠራርጎ እስር ቤት ካልገባና ለፍርድ ካልቀረበ የአማራ መጨፍጨፍም አይቆምም ሀገርም ሰላም አትሆንም ብለዋል። እባካችሁ #ሼር አድርጉት🙏

Check Also

አማራና ትግሬ ተስማሙና ኦሮሙማን መክቱ። – ሞጣ ቀራንዮ

https://fb.watch/f-ipLpwPrZ/ Related Posts:አማራና ኦሮሞ አትጣሉ። ተዋደዱ !አማራና ትግሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የኦሮሞ ክልል አስተዳደር …

ማስጠንቀቂያ ለከንቲባ አዳነች እቤቤ!

Related Posts:የጃዋር ሞሃመድ የዜግነት አወዛጋቢ ጉዳይ. ጃዋር ማስጠንቀቂያ ተሰጠው !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.