Breaking News
Home / Amharic / አማራንና ኦርቶዶክስን አከርካርያቸዉን ሰብረናል ያለው ስብሐት ነጋ ተያዘ !

አማራንና ኦርቶዶክስን አከርካርያቸዉን ሰብረናል ያለው ስብሐት ነጋ ተያዘ !

የጥፋት ስትራቴጂስቱ እና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሐት ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
**************
የጥፋት ስትራቴጂስቱ እና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ገለጸ።
በአገራችን ላለፉት 27 ዓመታት የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ ያስተባበረ እና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሠራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሠራዊቱን ያስጨፈጨፈው የጁንታው ቁንጮ፣ ስብሐት ነጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የጁንታው ቁንጮ አመራር ስብሐት ነጋ ከተደበቀበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የጁንታውን ቁንጮ ስብሐት፣ የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀውት እንደነበር ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ገልጸው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻ እና አሰሳ፣ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ስር አውለውታል።
በተጨማሪም ከመከላከያ የከዱ ሌሎች ከሀዲ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከጁንታው መሪ ስብሐት ነጋ ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል።
እነዚሁ ከመከላከያ የከዱ የጁንታው ቡድን አመራሮች የጁንታውን ታጣቂ ኃይል በማዋጋት እና በማሠልጠን እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፣ በመጨረሻም የጁንታውን አመራር ዙሪያ ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።
እነዚህኑ የጁንታው አመራሮች ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የጁንታው ታጣቂ ኃይልም መደምሰሱን ተናግረዋል።
በዚሁ መሠረት በቁጥጥር ስር የዋሉት፣
1. የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት ስብሐት ነጋ
2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሐት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሐኪም የነበረች በኋላም በጡረታ የተገለለች
3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ-ከመከላከያ የከዳ
4. ኮሎኔል የማነ ካህሣይ-ከመከላከያ የከዳ
5. አስገደ ገ/ክርስቶስ-ከመሀል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለ እና ለጊዜው ሓላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣
6. ኮማንደር በርሄ ግርማ-የክልሉ ልዩ ኃይል ሎጂስቲክስ ሓላፊ የነበረ
7. አምደማርያም ተሰማ ተወልደ-የክልሉ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ሓላፊ የነበረ
8. የሜጀር ጀነራል ኃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረች እና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረችው ወ/ሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል በመግባት ሕይወቷ ማለፉን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልጸዋል።

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.