Breaking News
Home / Amharic / ትዉልድ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሀገራቸው መኪና ይዘው ገብተው አንዳይሰሩ ከባድ ቀረጥ ተጣለ:: መኪና 500% ቀረጥ ያገለገለ ትራክተር 400%

ትዉልድ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሀገራቸው መኪና ይዘው ገብተው አንዳይሰሩ ከባድ ቀረጥ ተጣለ:: መኪና 500% ቀረጥ ያገለገለ ትራክተር 400%

ሀሳብዎን ያካፍሉ!

በኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ተረቅቆ እና በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው አዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ካነሣቸው ጉዳዮች አንዱ ከውጭ በሚገቡ መኪኖች ላይ ከ100%-500% ታክስ ለመጣል አቅዷል።

ከዚህ በፊት በነበረው አዋጅ ቁጥር 307/2002 መሠረት መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ይከፈል የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ እንደ ሲሲያቸው መጠን ነበር።

ይኸውም፦

እስከ 1ሺ300 ሲሲ 30%፣
ከ1ሺ 301 እስከ 1ሺ 800 ሲሲ 60%፣
ከ1ሺ801 ሲሲ በላይ ደግሞ 100 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ ይህ አመዳደብ ለአዳዲስ ብሎም ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ተመሳሳይ ነበር።

አዲስ የተረቀቀው አዋጅ:-

ከ0-1 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች=100%
ከ1-2 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች=150%
ከ2-4 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች=200%
ከ4-7 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች=300%
ከ7 ዓመት በላይ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች=500% ኤክሳይስ ታክስ እንደሚጣልባቸው ይደነግጋል።
ያገለገለ ትራክተር 400%

ይህ ረቂቅ ሕግ ከነዳጅ ፍጆታ፣ የአገር ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በማነቃቃት የሥራ ዕድል ከመፍጠር፣ መለዋወጫ መሣሪያዎችን ከውጭ ለማስገባት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ወጭ ከማዳን፣ የተሽከርካሪ አደጋ ከመቀነስ፣ የአካባቢ ብክለትን ከማስቀረት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች አንጻር የሚኖረውን ፋይዳ እንዴት ያዩታል?

Natnael Nana Mesfin ፈጽሞ ፈጽሞ ባለ አዕምሮ እንደዚህ አያስብም የአንድ መኪና ወጋን ማናር ሳይሆን ነገን ማሰብ መልካም ነው የመኪና ዋጋ ጨመረ ማለት እመኑኝ ሳንቲም እየለቀሙ የሚተዳደሩት የትራንስፖርት ሰጪ አካላት በመለዋወጫ ዕቃዎች መናር የዚህን ዘርፍ አካላት ምሬት ውስጥ እንደሚከትና ሀገሪቱን የሌለ ቀውስ ውስጥ እንደሚከት ከግምት ውስጥ ያላሰገባ መሆኑን እንዲሁም የሀገሪቱን መንገድ ግንባታ ላይ የሚሰማሩ መኪኖች ዋጋ፣የትራክተር መሰል መኪኖች ዋጋ መናርና የመለዋወጫ ዕቃ የማይቀመስ ወጋ ሆኖ መናር ብዙዎችን ወዳላሰፈለገ ተቃውሞ እና ብጥብጥ እንዲያመራ እና ሀገሪቱን የለሌ ቀውስ ውስጥ የሚያሰገባ ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚያሰገባ መሆኑን በማጤን ህዝቡም ላይ የእለት ግብአቶች ላይ የሚኖረው አሉታዊ ዋጋ ንረቶችን የሚያሰከትል መሆኑን አውቆ መንግስት ወይም የሚመለከተው አካል ከወዲሁ እንዲያስብበትና እጁን ከዚህ ተግባር እንዲሰበስብ እንደባለአዕምሮ እንዲያሰብ ምክሬ ነው! !!

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.