Breaking News
Home / Amharic / ታምራት ላይኔ የአማራ ባንክ ምስረታን ሊያደናቅፍ ሲሞክር መያዙ ተሰማ::

ታምራት ላይኔ የአማራ ባንክ ምስረታን ሊያደናቅፍ ሲሞክር መያዙ ተሰማ::

ታምራት ላይኔ የአማራ ባንክ ምስረታን ሊያደናቅፍ ሲሞክር መያዙ ተሰማ
—–
የቀድሞው ም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ታምራት ላይኔ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ኘሮግራም ላይ ሳይጠራ ተገኝቷል።
ዝርዝር መረጃውም እንዲህ ነው። አቶ ታምራት ላይኔ ምንም አይነት የጥሪ ወረቀት ሳይደርሰው ከሆቴሉ ባለቤቶች ጋር ባለው የግል ቅርርብ ብቻ ወደ ኘሮግራሙ ዘልቆ ለመግባት ይሞክራል።
የኘሮግራሙ አስተባባሪዎች የጥሪ ወረቀት እንዲያሳያቸው ቢጠይቁትም አቶ ታምራት የለኝም የሚል ምላሽ ይሰጣቸዋል። በዚህም የጥሪ ወረቀት ያልያዘ ሰው መግባት እንደማይችል ይነገረዋል።
አቶ ታምራት ግን ክልከላውን በመጣስ ወደ አደራሹ ለመግባት ሲሞክር ከአስተባባሪዎች ጋር ግርግር ይፈጠራል። የተፈጠረውን ግርግር ከርቀት የተመለከቱት የእለቱ የክብር እንግዶች እነ አቶ መላኩ ፋንታ እና አቶ መላኩ አለበልም ወደ ግርግሩ ቦታ በመዝለቅ ለማጣራት ይሞክራሉ።
አቶ ታምራትም፣ የሚመሰረተው የአማራ ባንክ የአማራ ህዝብ እስከሆነ ድረስ የመገኘት መብት አለኝ ይላቸዋል። እነ አቶ መላኩም እኛም ተጋብዘን ነው የተገኘነው በማለት ለአስተናጋጆቹ እንዲታዘዝ ይነግሩታል።
በዚህ ጊዜም አቶ ታምራት በሃይል ጥሶ ለመግባት ሲሞክር የበለጠ እረብሻ ተፈጥሯል። በመጨረሻም ኘሮግራሙ ከሚበጠበጥ አቶ ታምራት ወደ አዳራሹ ዘልቆ እንዲገባና ከሗላ ወንበር እንዲቀመጥ በቀረበው ምክረ ሀሳብ መሰረት ገብቶ ስብሰባውን ታድሟል።
በዚህ ጊዜም የእጅ ስልኩን በማውጣት አብሮት ያለው የደህንነት ሰው/ለግል ጠባቂው/ ፎቶ እንዲያነሳው አድርጓል ተብሏል።
ከባንኩ ሀላፊዎች እንዳረጋገጥነውም፣ አቶ ታምራት የአማራ ባንክ እንዲመሰረት ከማይፈልጉ ሰዎች ተልዕኮ ይዞ እንደመጣ ነገረውኛል።
የትኛው አካል እንደላከው የሚያውቁት ነገር ካለ ስንጠይቃቸው ግን፣ እሱን አሁን ለመግለፅ አንፈልግም። ወደ ፊት ግን ስለሁኔታው ከጠበቃ ጋር ተነጋግረን በዝርዝር እናሳውቃለን ብለዋል።
ቴወድሮስ ዳግም ተነሳ::

Check Also

ኦነግ ሽኔን ያቋቋመው አብይ አህመድ ነው:: የደህነቱ ሹም አቶ አያሌው መንገሻ ይናገራሉ!

Related Posts:ወላይታ ምድር ያበቀላቸው ኢትዮጵያዊ የታሪክ ምሁር ታዲዬስ ታንቱ ይናገራሉ::አቶ ልደቱ አያሌው እቅጩን ተናገሩ!ልደቱ አያሌው …

ኦነግ ሸኔ የኦህዴድ ብልፅግና ወታደራዊ ክንፍ ነው !

Related Posts:ፋኖና የአማራ ሀይል ከጠላት የማረከዉን መሳሪያ የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት እየነጠቀዉ ነዉ::

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.