ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የጀግና ሜዳሊያ ተነፈጋቸው !
Admin
May 12, 2022
Amharic, Documents, News
619 Views
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የጀ ግና ሜዳሊያ ተነፈጋቸው!
በአማራ የህልውና ዘመቻ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላት ባህርዳር የሽልማትና እውቅና ኘሮግራም ዛሬ ተካሂዷል።
በዚህ ኘሮግራም የአሁኑ የአማራ ልዩ ሃይል አዛዥ ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ እና የአማራ ሚሊሻ አዛዥ ኮሎኔል ባምላኩ አባይ የአንደኛ ደረጃ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልመዋል።
በከፋፍለህ ግዛውን የሚተዳደረው የአማራ ብልፅግና ግን በዚህ የሽልማት ኘሮግራም በአብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የጄኔራል ተፈራ ማሞ ስም እንዳይጠራ አድርጎት አልፏል።
በመንግስት ዕዝ ስር ሆነው የዘመቱ ፋኖዎች እንደ አስተዋጿቸው በአማራ ብልፅግና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በራሳቸው መዋቅር የዘመቱ ፋኖዎች ግን ጥሪ አልደረሳቸውም።
አሸባሪው ህወሃት ደብረታቦር ሲቃረብ 60 ሚሊዮን ብር ዘርፈው ሊኮበልሉ የነበሩት የአማራ ብልፅግና አመራሮች የክብር እንግዳ ነበሩ።
አማራን የሚያሳርደው ሽመልስ አብዲሳም እንዲሁ የኘሮግራሙ የክብር እንግዳ ተደርጓል።
ዘመነ ካሴ #ፋኖ