Breaking News
Home / Amharic / ባለፋት ጊዚያት የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች የተሰሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ!

ባለፋት ጊዚያት የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች የተሰሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ!

አብን***

ባለፋት ሶስት ጊዚያት በኢትዮጵያ በተካሄዱት የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች የተሰሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አሳሰበ፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 08/2011 ዓ.ም(አብመድ) ባለፋት ሶስት ጊዚያት የተካሄዱትን የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች መነሻ በማድረግ ቀጣይ በሚካሔደው ቆጠራ ስጋቶች እና መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ በአዲስ አበባ ውይይት እያካሄደ ነው።

ባለፋት የቆጠራ ጊዚያት የተሠሩት ስህተቶች መጋቢት 29 /2011 ዓ.ም በሚካሄደው 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዳይደገሙ ሁሉም የአማራ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍ ንቅናቄው ጠይቋል፡፡
በተለይም ምሁራን ህዝቡን በማንቃት እና ቆጠራው በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ነው ንቅናቄው የጠየቀው፡፡

የአብን ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ‹‹ባለፋት ቆጠራዎች የአማራ ህዝብ ቁጥር ‹‹ሆን ተብሎ›› እንዲቀንስ ተደርጓል፤ በዚህም ክልሉ በብዙ ዘርፎች ተጎድቷል›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ የሚካሔደውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤታማ በማድረግ የክልሉ ህዝብ ማግኘት ያለበትን ማህበራዊ እና ኢኮኖማያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥነ ህዝብ እና ዲሞግራፊ መምህር ዶክተር ሲሳይ ምስጋናው በኢትዮጵያ ባለፉት ጊዚያት የተካሄዱት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራዎች ችግሮችና የ2011 ዓ.ም ቆጠራ ስጋቶችን መሠረት የደረገ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በጥናታዊ ጽሁፋቸው እንዳመላከቱትም ባለፋት ቆጠራዎች የአማራ ክልል ህዘብ ቁጥር በ1987 ዓ.ም ከነበረው በ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቀንሷል፡፡ በሶስቱ ቆጠራዎች ደግሞ 6 ሚሊዮን የሚሆን የአማራ ክልል ህዝብ አለመቆጠሩን ተናግረዋል።

የህግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት በበኩላቸው ‹‹የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ህግ ማዕቀፍ›› በሚል ርዕስ የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮዎች እያጣቀሡ አቅርበዋል፡፡
በጽሁፋቸውም ቆጠራውን ያካሔደው ተቋም ገለልተኛ እና ነጻ አለመሆን ከአሁን በፊት በተካሔዱት ቆጠራዎች ለተፈጠሩት ስህተቶች ምክንያት ነበር ብለዋል፡፡ አደረጃጀቱ አለመቀየሩም ለአሁኑ ቆጠራ ስጋት እንደሚሆን ነው ያቀረቡት፡፡

ዘጋቢ፡-በለጠ ታረቀኝ- ከአዲስ አበባ (ከአማራ ማስ ሚዲያ ኢጀንሲ ከማህበራዊ ገጽ የተወሰደ)

Check Also

ጥያቄ ለብአዴን! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ??

ብአዴኖች እመኑኝ ብትሞቱ እንኳን አንተዋችሁም!!! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ?? እመኑኝ …

አብይ አህመድ ፋኖን ለማጥፋት መልክተኞች ወደ ጎንደር ልኳል !

Related Posts:ሰበር መረጃ - ጎንደር በመትረየስ እና በፈንጂ ስትታመስ አደረች - ለምን?በደቡብ ጎንደር ዞን ታስረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.