Breaking News
Home / Amharic / በዘር ፍጅት የቆመው ብልጽግና! መተከልንም ሆነ ወለጋን የሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ነው።

በዘር ፍጅት የቆመው ብልጽግና! መተከልንም ሆነ ወለጋን የሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ነው።

 
*****
መተከልንም ሆነ ወለጋን የሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ነው። የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮችን የሚያስተዳድረውም ይኸው የብልጽግና ፓርቲ ነው። በኮማንድ ፖስት እና አጣሪ ግብረኃይል ስምም በቦታው ስምሪት የሰጠውም ብልጽግና ፓርቲ የራሱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ነው። አማራ/አገው ራሱን ከአጥቂዎች እንዳይከላከል የነፍስወከፍ መሣሪያ እንዳይታጠቅ፤ ከታጠቀም እንዲፈታ ያደረገው የብልጽግና ፓርቲ ነው። በተለይ በመተከል በአማራ/አገው ላይ እየተፈፀመ ባለው የዘር ፍጅት አመራሩ ጭምር እየተሳተፈ መሆኑን ብልጽግና ራሱ ያመነው ነው።
 
በሌላ አገላለጽ አማራውን/አገውን እየገደለና እያስገደለ ያለው ብልጽግና ፓርቲ ነው። አማራውን ወክላችሁ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ወንድሞችና እህቶች ከአራጁ ጋር ትቀጥላላችሁ ወይስ አራጁን ታስወጣላችሁ? በመደማመጥ፣ መከባበርና መተማመን ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃቀኛ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊስት ኃይሎች በገዥው ብልጽግናም ሆነ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ዘንድ ቢኖሩም በተለይ የአማራ ብልጽግናዎች ለአራጁ ቡድን በምታሳዩት ከልክ ያለፈ ትእግስት ነው ዝምታን የመረጡት።
 
እናንተ ያላከበራችሁትን አማራነት አራጁ ቡድን አያከብረውምና ደጋግማችሁ አስቡበት። የፍትኅ፣ እኩልነትና ዴሞክራሲ እከክ የሆነውን አራጅ ቡድን ከላያችሁ ላይ አራግፉት። አልያ ግን እናንተም ለወገኖቻችን መታረጃ ካራን በጓዳ አቀብላችሁ ከፊት ለፊት ከደሙ ንፁሕ ነኝ ለማለት በሙሾ እጃችሁን የምትታጠቡ ጲላጦሳውያን እንደሆናችሁ እንቆጥራለን።
ሕዝብን ይዘን የማናሸንፈው ትግል አይኖርም!
 
written by
 

Check Also

አቡነ ሳዊሮስ ማናቸው ? Who is Abene Sawiros?

★ ” አቡነ” ሳዊሮስ ማናቸው ? ★ ★ ከሁለት ሴቶች ዲቃላ(ከሕጋዊ ጋብቻ ውጪ) የወለዱ ምንኩስናቸውን …

ከጀርመን ሃገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ !

Related Posts:ከመንግስት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!ከአብን …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.