Breaking News
Home / Amharic / በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ኣማራና ጉራጌ ደቡብ ከስራ ታግደዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ኣማራና ጉራጌ ደቡብ ከስራ ታግደዋል።

የአዲስ አበባው አዴፓ የቁም እስረኛ ሆኗል።
አዲስ አበባ የሁሉም ናት ብሎ ሊታገል የወሰነው አዴፓ እንዳይንቀሳቀስ በኦዴፓ ታስሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአዴፓ አመራሮች ከስብሰባም ከስራም ታግደዋል።

አመራሮቹ ደሞዛቸው እየተከፈላቸው ነገር ግን ከስራና አስብሰባ ታቅበው እንዲቆዩ ነው የተነገራቸው።

ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው የብአዴን/አዴፓ የአዲስ አበባ ተወካይ አመራሮች የወረዳ አመራሮች ናቸው።

በኦዴፓው አቶ ጥላሁን ፈቃዱ ስራ አስፈፃሚነትና በህወሀቱ አቶ ግዳይ ስራ አስኪያጅነት በሚመራው የቦሌ ክፍለ ከተማና በስሩ በሚገኙ ወረዳዎች የአዴፓ ተወካዬች ከስራ ውጭ ሆነዋል።

ለምሳሌ ደሞዛችን ለጊዜው ስላልቆመ ስማችን አትጥቀስ ያሉ በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 1 እና 7 አመራሮች እንደታገዱ አረጋግጫለሁ።

ጉዳዩ ከሚዲያ ደርሶ ህዝብ ከሚያውቀው ሳይሰሩ መክፈልን መርጧል የአቶ ታከለ ኡማ መንግስት።
ከዚህ በተጫማሪ በየወረዳው በደምብ ማስከበር ጽ/ቤት ሲመሩ የነበሩ የአዴፓ አመራሮች (በአብዛኛው የኮማንደርነት ማዕረግ ያላቸው )ሀላፊዎች በልዩ ልዩ ዘዴ እንዲገለሉ ተደርጓል ።

ክዚህ በፊት 24 የአዴፓ የአ.አበባ አመራሮች በከንቲባ ታከለ ኡማ ትዛዝ መነሳታቸው ይታወሳል። 1የከተማ፣ 1የክ/ከተማና 22 የወረዳ አመራሮች ነበሩ የተነሱት።

 

source: Yoni Magna. FB

Check Also

አብይ አህመድ ፋኖን ለማጥፋት መልክተኞች ወደ ጎንደር ልኳል !

Related Posts:ሰበር መረጃ - ጎንደር በመትረየስ እና በፈንጂ ስትታመስ አደረች - ለምን?በደቡብ ጎንደር ዞን ታስረው …

አብን 10 የስራ አስፈፃሚ አባላትን አገደ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ፓርቲ ዐሥር አባላቱን ማገዱን አስታወቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.