በአሸባሪው ኦነግ ላይ እርምጃ መንግስት ካልወሰደ እኛ እንወስዳለን አሉ! Admin April 8, 2019 Amharic 1 Comment 502 Views Related Articles ለአማራ ባንክ ምዝገባ ! 4 days ago ዘመን አይሽሬ ስህተት ! 5 days ago የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ! 7 days ago የእራት ግበዣ – አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው! 2 weeks ago በዐቢይ የሚመራው የኦሮሙማ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመው ያለው ወረራ! 2 weeks ago 53 ቢሊዮን ብር ተበላ!! 3 weeks ago በመላው አማራ ክልል ለአብይ ድጋፍ እንዲወጣ ማድረግ? 3 weeks ago ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስልጣናቸውን ይልቀቁ! የ13 ተቋማት ጥያቄ! January 29, 2021 Related Posts:188 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል!በአማራ ክልል የዳቦ ዱቄትን ላልተገባ ጥቅም ባዋሉ ከ600 ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ::ፋኖና መንግስት ዛሬ ተስማሙ! ፋኖ ትጥቅ አይፈታም!ሃገረ መንግስት ምስረታ (State formation) የራሱ ትልቅ ሂደት አለው ።ሁለት መንግስት ባለበት ሀገር እንዴትነዉ ፍትህ የሚኖረዉ?በህገ መንግስት ማሻሻል ላይ የተፈጠረው ውዝግብ ! Share Facebook Twitter Google + LinkedIn Pinterest
ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ!
• የአማራ ክልል ባለስልጣናት ዘገምተኛ ከሆነ አካሄድ ወጥተው ወቅቱ የሚፈልገውን ፍጥነት መላበስ ይኖርባቸዋል:: መረጃን አስቀድሞ በመሰብሰብ ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት የመከላከል አቅምን በማጠንከር እርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል:: የሚያስተዳድሩትን ክልል ተብዬ በቅጡ ማወቅ እና በየጎጡ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግንዛቤ እና ወቅታዊ መረጃ ሊኖራቸው ይገባል:: ለዚህም የየአካባቢውን አደረጃጀት በደንብ ተጠናክሮ ስልጣን በአራቱም የአማራ ክልሎች በማደላደል ኃላፊነትን ማከፋፈል እና ክልሎቹን ማጠናከር ይኖርባቸዋል:: ከዚህም ባለፈ አሁን የአማራ ክልል ተብሎ ከተሰየመው ክልል ውጭ የሚኖሩትን አማዋዎች ማደራጀት እና ባሉበት ቦታ ልውክልና ማብቃት ይኖርበታል::
• አሁን ያለ ባለስልጣን በጎጃም አካባቢ የተጠራቀመ ሲሆን የአገሪቷ ፖሊቲካ ከሚዘወርበት አዲስ አበባ እጅጉን የራቀ በመሆኑ ለፖለቲካው ርቆ ባይተዋርነት ይታይበታል:: በተቃራኒው ለአዲስ አበባ ቅርብ የሆኑት ፖለቲካውን በራሳቸው መንገድ እየዘወሩ የአማራ ሕዝብ አሁንም ከተጠቃሚነት ጎድሎ እንዲያውም ጥቃት እየደረሰበት ይገኛል:: ስለዚህ ክልሉ የስልጣን ማዕከሉን ከባህርዳር ወደ ደብረብርሃን ማዛወር ወይም ሁለተኛውን የመንግስት መቀመጫ ሊያደርግ ግድ ሊለው ይችላል:: በተጨማሪም የተለያዩ የአማራ ቡድኖች በክልሉ ስልጣን ውስጥ ቦታ አልተሰጠንም የሚል ቅሬታ ሊኖራቸው ስለሚችል ይህንን ውስጣዊ ጥንካሬውን ለማምጣት በአግባቡ ውክልናቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ሁሉንም ወደ አንድ አቅጣጫ ማሰባሰብ ያስፈልጋል::
• የክልሉን የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ በዘመናዊ መልክ በማደራጀት እንዲሁም በየመንደሩ እና ጎጡ አደረጃጀቶችን በመፍጠር የመረጃ አሰባሰብ ብቃቱን እና ፍጥነቱን ማሽሻል ይኖርበታል:: የየአካባቢው ሕብረተሰብ የሚሳተፍበት የአካባቢ የቅድመ ሰው ሰራሽ አደጋ መረጃ አሰባሰብ የጥበቃ እና የአደጋ ጊዜ ፈጥኖ የመድረስ እና እርምጃ አወሳሰድ መመሪያዎችን ስልጠናዎችን እና ቁጥጥሮችን መተግበር ይኖርበታል::
• ህብረተሰቡ በሰው ሰራሽ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ ሊከለልበት በተለይ ሴቶች ሕፃናት እና አረጋውያን ከግድያ ከ ጠለፋ ካስገድዶ መደፈር ከአካል መጉደል ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለበት ወዴት መጠለል እና እርዳታ ማግኘት እንዳለባቸው እቅድ ወጥቶ ስፍራዎች መዘጋጀት ስልጠናዎች መሰጠት እና ለዚህ ጊዜ የሚሆኑ ኃላፊነት የሚወስዱ ሰዎች መመደብ ይኖርባቸዋል::
• በክልሉ የሰው ሰራሽ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ የምግብ እና ሌሎች እራስን የማቆያ ግብአቶች እጥረት እንዳይኖር በቀላል ቴክኖሎጊዎች በመታገዝ በፍጥነት ምግብ የሚመረጥበት እና የሚከማችበት ዘዴዎችን ከህብረተሰቡ ጋር ማስተዋወቅ ማላመድ ያስፈልጋል:: በተጨማሪም ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቀጣይነት ያለው የገንዘብ ማሰሰባሰቢያ እና ማተራክሚያ ግልፀኝነት በተሟላ መልኩ ሊተገበር ይገባል::
• በክልልሉ ያለው ወጣት ስራውን አየሰራ አየተማረ ምርታማነት እንዲጨምር እና ሰው ሰራሽ አደጋ በምንርበት ጊዜ እጥረት እንዳይፈጠር ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በመስራት አለኛት መሆን ይኖርበታል:: ለዚህም አደረጃጀቶቹ መረጃን በመሰብሰብ በመለዋወጥ አመራር መስጠት እና ማስተባበር ማንቃት እና ማሰማራት እንዲሁም ለውጦችን መከታተል ይኖርባቸዋል:: በተቸማርውም ሰው ሰራሽ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ እራሱን እና ሕዝቡን ለመከላከል የሚያስችል የትጥቅ ትግል ስልጠና እና የክህሎት ብቃት እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል::
• ሌላው በክልሉ እና ከክልሉ ውጪ ከሚንቀሳቀሱ በአማራ ስም እንዲሁም በኢትዮጵያ ወይም በሌላ ስም ከተደራጁት ኃይሎች እና ኢትዮጵያዊነታቸውን ከሚያስበልጡ እና እንደገና በጋራ ሊገነቧት ከሚፈልጉ ሃይሎች ጋር የሚሰራበትን ስልት በመንደፍ መሪነቱን በመውሰድ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ይኖርበታል:: በተመሳሳይ ሁኔታ የተለያዩ ኢትዮጵያዊነታቸውን ከሚያስበልጡ ክልሎች እና ኃይሎች ጋርም መስራት ይኖርበታል::
• አማራው ክልል አካሄዱን በማስተካከል አቁአሙን ግልፅ በማድረግ ውጭ ሐገር ከሚኖሩት የክልሉ ተወላጆች እና ደጋፊዎቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት የሚፈጥርበት ስልት ነድፎ በመንቀሳቀስ የዲፕሎማሲ እና የገንዘብ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የመዋዕለ ንዋይ አቅሙን ማጠናከር ይኖርበታል:: ይህ ለህልውናው ወሳኝ ነው:: የአማራ ሚዲያዎች እና አከቴቪስቶች እንደ አንድ አንድ እንደገባቸው ሌላው ላይ በማተኮር ጊዜያቸውን እና አቅማቸውን ከሚያባክኑ መጀመሪያ ህዝባቸውን በማደራጀት እና አቅም በማሰባሰብ ላይ ቢሰሩ ሌላው የትም አይሄድባቸውም ስለዚህ ሌገብሩት ይገባል::