Breaking News
Home / Amharic / በአሜሪካን አገር ተሰሚነት ያለው የአማራ የመብት ታጋይ ስለ HR6600 ረቂቅ ሕግ ይህን ብሏል!

በአሜሪካን አገር ተሰሚነት ያለው የአማራ የመብት ታጋይ ስለ HR6600 ረቂቅ ሕግ ይህን ብሏል!

በአሜሪካን አገር ተሰሚነት ያለው የአማራ የመብት ታጋይ ይህን ብሏል::
 
“በ HR6600 ረቂቅ መሰረት በአማራ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀሙ አካላት በሙሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል።” ይህን ያሉት የአማራ ማህበራት በሰሜን አሜሪካ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ትርፌ ናቸው። በጉዳዩ ዙሪያ ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመው ንግግራቸው ቀጥሎ ቀርቧል።
~~
1. “ረቂቁን ተቃወሙ” የሚሉ ባለስልጣናት ጭንቀታቸው ኢትዮጵታያ እንዳትጎዳ ሳይሆን በሰሩት ወንጀል ልክ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ነው፤ የኢትዮጵያ መጎዳት ቢያሳስባቸው ኖሮ ከ HR6600 ይልቅ ሀገሪቱ ውስጥ የሚፈሰው ደም ያስጨንቃቸው ነበር።
2. የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሉዓላዊነት ትዝ የሚላቸው ስለ ማዕቀብና ቅጣት ሲሰሙ ነው ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈፀሙ ግድያዎች ተጠያቂ ላለመሆን በሀገር ሉዓላዊነት ስም ለመደበቅ ይሞክራሉ።
3. የዘር ማጥፋትን የሚፈፅም መንግስት የሚቀጣው አካል ሊኖር ይገባል፤ እንደ HR6600 አይነት ረቂቆች የማይኖሩ ከሆነ ያለ ጠያቂ የሚፈፀመው የአማራ ህዝብ መፈናቀልና ጅምላ ግድያ ይቀጥላል ማለት ነዉ። ስለዚህ የግድ አሳሪ ረቂቅ ተግባራዊ መደረግ አለበት።
4. የኢትዮጵያ መንግስት የ HR6600 ን መፅደቅ በድጋፍ መቋረጥ ስም ማስፈራሪያ አድርጎ ለመጠቀም ይሞክራል፤ እውነታው ግን ከውጪ የሚላኩ ድጋፎች የካድሬ ምሳና ራት ከመሆን አልዘለሉም። ዛሬ ድረስ የተፈናቀሉ ወገኖች በከፍተኛ ርሃብ ውስጥ ናቸውና። ስለዚህ ድጋፎች ባይቋረጡም ለአማራ ህዝብ አይደርሱም፤ ቢቋረጡም የተለዬ ነገር አይኖርም፤ የተለዬ ነገር ካለም ለካድሬው፣ ለጆሮ ጠቢውና ለገዳዩ የሚከፈል ገንዘብ እጥረት ነው።
5. HR6600 ረቂቅ ጉዳቱን ብቻ የማጉላት አዝማሚያ ይታያል። ከአማራ ህዝብ አንፃር ካየነው ከHR6600 ረቂቅ ይልቅ የአብይ አስተዳደር የሚፈፅመው ግፍ አውዳሚ ነው።
6. እኛ HR6600 የአማራን ህዝብ በማይጎዳ እና በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀሙ አካላትን ተጠያቂ በሚያደርግ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰራን ነው።
7. የHR6600 ረቂቅ የኢትዮጵያ መንግስትን ያዳክመዋል፤ ብሄር ለይቶ የሚጨፈጭፍ መንግስት መዳከሙ እንጂ መጠናከሩ ምን ይጠቅማል? መሳሪያ ያጣል? ይጣ፤ መሳሪያ ኖሮት የትኛውን ህዝብ ከየትኛው ግድያ አዳነ?
8. ሌላው የባለስልጣናቱ ጭንቀት መንስኤ የHR6600 በዘር ፍጅት ወንጀል የሚከሰሱ ባለስልጣናት ክስ የሚመሰርት መሆኑ ነው፤ ይሄንን ነው “አሜሪካ ሉዓላዊነታችንን ተዳፈረች፣ እጅ ጠመዘዘች” እያሉ የሌለ ምስል ለመፍጠር የሚሞክሩት።
9. ያም ሆነ ይህ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረግ ግድያ፣ መፈናቀልና መገፋት በማንኛውም መንገድ መቆም አለበት፤ ይህንን የአብይ አስተዳደር ሊያደርገው ስላልቻለ የሚገደድበትን መንገድ ማዘጋጀት ግድ ነው፤ ከዛ መንገድ ውስጥ አንዱ HR6600 ነው።
 

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.