Breaking News
Home / Amharic / በቦታው ያላችሁ አማሮች ሰብሰብ ብላችሁ መመከት ይኖርባችኋል!

በቦታው ያላችሁ አማሮች ሰብሰብ ብላችሁ መመከት ይኖርባችኋል!

መተከል ላይ እየተጨፈጨፉ ስላሉ አማሮች…

(ገብርዬ)
*****
1) በቦታው ያላችሁ አማሮች ሰብሰብ ብላችሁ መመከት ይኖርባችኋል። መመከት ተፈጥሯዊ መብት ነው። ይህን መብታችሁን ተጠቀሙ። ራስን ከጥቃት መከላከል ወንጀል አይደለም።

2) የአማራ ልዩ ኃይል አማራውን የመታደግ ግዴታውን መወጣት አለበት። የአማራ ብሔራዊ መንግሥት አመራሮችም ለዚህ ተልዕኮ አመራር በአስቸኳይ ልትሰጡ ይገባል። ልዩ ኃይሉ ከጭፍጨፋው ጀርባ ያሉ የአካባቢው አመራሮችንም ማንቁርታቸውን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ አለበት።

3) ለአካለ መጠን የደረሰ፤ ራስን ለመከላከል የአካልና የአዕምሮ ሁኔታው የሚፈቅድለት አማራ ሁሉ (ወንድም ሴትም) እንደሕዝብ የተደቀነብንን እልቂት ለመከላከል የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ አለበት። ፍትኅን ከገዳይ እንደመለመን ዓይነት መዋረድ የለም።

4) ወንድማችን የሺሀሳብ አበራ እንደሚለው«ፍትኅ የጉልበት ሎሌ ናት»። አንድ ወቅት አይሁዶች እንዲህ እንደእኛ የማንም ወበከንቱ ማላገጫ ነበሩ። ተደራጅተው ጉልበታቸውን ማፈርጠም ስለቻሉ ግን ዛሬ ላይ እንኳን እስራኤላዊ ዜጋን የእስራኤል ኤምባሲን አጥር እንኳን በሁለት ዓይኑ ደፍሮ የሚያይ የለም። ይህም የሆነው በትግላቸው ባስመዘገቡት ድል እንጂ በዕድል አይደለም። ዓለም ለደካሞች ቦታ የላትምና አማራ ሆይ መጠንከር ምርጫህ ሳይሆን ግዴታህ ነው።

5) ሙሾ ይሰለቻል። «እኒያ ነፍራቆች ለቅሶ ጀምሩ» የሚሉን በዝተዋል። ለቅሶ መናቅን እንጂ መከበርን አይሸምትም። ቆምጨጭ ማለት ብቻ ነው ያለን ምርጫ። ሞት እንደሆነ ለምደነዋል። የአማራ መሞት እኮ ዜና አይደለም። ሞት አዲሳችን አይደለም። እናም ቆምጨጭ እንበል! ሊገለን የሚመጣ ትርፍ ነፍስ የለውም። ገዳያችን ነፍሱ ብረት ለበስ አይደለችም። በቃ ቆምጨጭ ብለን እንመክት! መመከት ራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው። እኛ ገፍተን ሄደን ጡር እንሥራ እንጂ ደጃችን ድረስ ሊገለን የመጣን መመከት በሰውም በእግዜርም ኩነኔ የለውም! እናም ይህን ያህል ሰው ተገደለ ብለህ አትንገረኝ። አማራ ነኝ የሚል፤ የአማራ ጉዳይ ይገደኛል የሚል በየትኛውም ቅርፅና አድማስ ያለ አደረጃጀትም እየተጨፈጨፈ ያለው ወገናችን የሚፈልገው ድጋፍ ከንፈር መጠጣ አለመሆኑን መረዳት አለበት! ወገኔ የሚፈልገው ጨፍጫፊዎችን ልክ የሚያስገባለት ነው። ሕዝቤ የሚፈልገው ለጨፍጫፊዎቹ አመራር የሚሰጡትን የፊጥኝ አስሮ ለፍርድ የሚያቀርብለት ነው።

እጣፈንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!

Check Also

የዘውድ ስርአት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስተባበር ይችላል! (ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር))

የዘውድ ስርአት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስተባበር ይችላል!   ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር) ከአንድ አመት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የእርስበርስ ጦርነት፤ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ …

ያለቅጥ ዝምታ ለበግም አልበጃት ! 12 ሁና አንድ ጅብ ፈጃት !

3 comments

 1. የአማራን ጀግንነት ፣ አባቴ የነገረኝ
  ለካስ የምናብ ነው ፣ እኔን ሲፎግረኝ
  የቁጩ ነው ለካ ፣ የአማራው ጀብዱ
  እንደከብት ሲነዱ ፣ አየን ሲታረዱ
  ይሄው ያለቅሳሉ ፣ በነጋ በጠባ
  ጀግንነቱ ካለ ፣ ታዲያ ወዴት ገባ?
  በተግባር እንየው ፣ ለቅሶው ይቁምና
  መሞጥ ካልቀረ ፣ እንይ ግደልና ።

  • እንደዚህ ተብሎ የሚሰነዘር አስተያየት ወይ በስሜታዊነት የሚደረግ ከህፃናት አይምሮ የሚፈልቅ ነው አሊያም ከአማራው ጠላቶች የሚሰነዘር በአማራ ቃጠሎ ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ ነው።
   አማራው ለ በርካታ አመታት በተሰራበት ግፍ እና በደል ከወደቀበት ገና አልተነሳም። ግን እየተነሳ ነው። ይህም ይመስለኛል ታዛቢውን እና መሰል የአማራ ህዝብ ጥላቶች ፋታ ያሳጣችሁ።
   በዚህም በየአቅጣጫው እሳት ትለኩሳላችሁ። ይሁን እንጂ ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል ነው። አማራ ምንም ሆነ ምንም እራሱን በአስተማማኝ እና ዘላቂነት ባለው መንገድ ማደራጀት የቅድሚያ ስራው ነው እንጂ በተለኮሰለት እሳት ውስጥ በመግባት ከ ጠላቶቹ ቀድሞ እራስን የማጥፋት የጅልነት ተግባር ሊፈፅም አይገባም።
   አለበለዚያማ ባለፈው ሰሞን በሰሜን ሸዋ ተደራጅቶ የመጣ የህወሀት እና የኦነግ መንጋ በተራው የመንዝ ገበሬ የደረሰበትን ምት ታዛቢው እርሶ ቢክዱ ኦነጎቹ እና ህወሀቶቹ እንኳን አይክዱትም ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ… ነው ነገሩ። ለእርሶ እና መሰሎችዎ ደግሞ ምናልባት ጀሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ ነው ነገሩ።
   የሆነው ሆኖ እድሜ ይስጦት እና አማራ እራሱን ብቻ ሳይሆን ድፍን ኢትዮጵያን ነፃ ሲያወጣ በቅርቡ ያዩታል። የዛኔ ግን እርሶ እና ድፍን የአማራ እና የእምዬ ኢትዮጵያ ጠላቶች መግቢያችሁ የት ይሆን?

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.