Breaking News
Home / Amharic / በመላው አማራ ክልል ለአብይ ድጋፍ እንዲወጣ ማድረግ?

በመላው አማራ ክልል ለአብይ ድጋፍ እንዲወጣ ማድረግ?

ይድረስ ለክቡር አቶ አገኜሁ ተሻገር ❗
በመላው አማራ ክልል ለጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ድጋፍ እንዲወጣ ለማድረግ የአማራ ብልፅግና እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተሰምቷል ❗
ይህ እጅግ አደገኛ የሆነ ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀና በየትኛውም መመዘኛ ትክክል ያልሆነ የድጋፍ ሰልፍ ነው❗
የአማራ ብልፅግና አሁን ሙሉ ለሙሉ በአማራ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አለው ! ይህን ተቀባይነት በዜሮ የሚያባዛ የአማራ ብልፅግናን ከህዝብ የሚነጥል እንደ ቀድሞው በጠላትነት እንድንተያይ የሚያደርግ ውሳኔ ነው የሚሆነው ❗
የአማራ ህዝብ በግፍ በታረደበት ወቅት ሀዘን ለመግለፅ የተጠራን ሰልፍ የከለከለን መንግስት ❗
የአማራ ክልል የተመለሱ መሬቶችን በህግ ያላፀደቀ ! ጭራሽ የአማራን መሬቶች ለሱዳን አሳልፎ የሰጠ መንግስት ❗
በወለጋ የታገቱ ሴት ህህቶቻችን ላይ ድራማ ለሰራ መንግስት
የአማራ ክልል ህጋዊ ተወካይ የሆነን ፓርቲ አሸባሪ የሚል መንግስት ❗
በመተከል የአማራ ህዝብ በየግዜው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ ያስፈፀሙ አመራሮችን አቅፎ እሽሩሩ የሚል መንግስት ❗
አይደለም ሞታችንን ማስቆም ሀዘናችን እንዳንገልፅ ያደረገንን መንግስት ❗
ምን ስላደረገ ነው ! የሰልፍ ድጋፍ አማራ ክልል ላይ የሚወጣው ❗
አሁን አዴፓ ብቻውን አይደለም ! ድፍን የአማራ ህዝብ ከጎኑ ነው !
ራሱን ችሎ በራሱ መቆም አለበት ከተላላኪነት መውጣቱን ማስመስከር አለበት ❗
ይህን የምንለው የአማራ ብልፅግና የብልፅግና አጋር መሆኑን ዘንግተን አይደለም ! ከተላላኪነት ከአድርባይነት ተላቋል ብለን ስላሰብን እንጂ ❗
ክቡር ፕሬዘዳንት የአማራ ህዝብ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ በላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዳር እስከዳር በመውጣት ድጋፍ በመስጠት ለስልጣን ያበቃው የአማራ ህዝብ ነው !
ነገር ግን ጠ/ ሚሩ ለአማራ ያተረፏለት ነገር በዘር መጨፍጨፍን ብቻ ነው ❗
አመራሮቻችንን ያጣው ! ኢንጅነር ስመኜውን ያጣነው ከግማሽ ሚሊዎን በላይ የአማራ ህዝብ የተጨፈጨፈው በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የአገዛዝ ዘመን ነው
ይህ ሁሉ ግፋ ሞልቶ በፈሰሰበት ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ ድጋፍ እንዲወጣ ህዝቡን መግፋት የአማራ ብልፅግና በግልፅ ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች ድጋፍ እንደሰጠ ይቆጠራል ❗
ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ የአዴፓ የፓለቲካ ሞት ይፋ ይሆናል
በአሁኑ ሰአት የአማራ ህዝብ ድጋፍ የሚወጣበት ወቅት ሳይሆን ጥያቄዎቹን የሚያስመልስበት በአንድነት ተጠናክሮ በግራም በቀኝም ከአንዣበበት አደጋ ራሱን የሚከላከልበት ወቅት ነው ❗
ይህ ሰልፍ በፍፁም መደረግ የለበትም ❗
አዴፓ ይህን ሰልፍ ካደረገ ከድፍን የአማራ ህዝብ ጋር በግልፅ ጦርነት ውስጥ ይገባል ❗በአማራ ህዝብ ደም እንደቀለደ ይቆጠራል
ብንወጣ እንኳ የኦሮሞ ብልፅግናን ለማውገዝ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ድምፅ የምናሰማበት ሀዘናችን ቁጣችን የምንገልፅበት እንጂ በፍፁም ለጠ/ ሚሩ ድጋፍ ለመስጠት አይሆንም❗
ጠ/ ሚሩ እንዳኮረፍን በእጅጉ ሊገነዘቡ ይገባል ❗
ሼር በማድረግ አድርሱ❗❗
Gonder tube/ጎንደር

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.