Breaking News
Home / Amharic / ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ::

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14 ቀን 2015 ዓም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት በሶዶ ዳጬ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ የቤተክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 26 ኤጲስቆጶሳትን በመሾማቸውና ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በመገናኛ ዘዴዎች በማስነገራቸውና ክህደት በመፈጸማቸው፣ አባ ሳዊሮስ፣ አባ አዎስጣጤዎስና አባ ዜናማርቆስ ከድቁና ጀምሮ ያለው ክህነተ ስልጣናቸውን አንስቶ አወገዘ።
ቅዱስ ሲኖዶስ እንዳስታወቀው፣ የወሊሶውን ሕገ ወጥ የኤጴስ ቆጶሳት ሹመት ያስፈጸሙት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ግለሰቦችና ሕገ ወጥ ሹመቱን ለመቀበል ወሊሶ የሄዱ 26 መነኮሳት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ጉባኤ ተለይተው እንዲወገዙ ወስኗል።
ፓትርያርክ ባለበት ሉዋላዊ ስልጣንን በመግፋትና መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረጋቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘዋል። ቅዱስ ፓትርያርክ በሌለበት የሚሰጥን ሹመትን ሲኖዶስ እንደሚያወግዝና ሲመቱም ሕገ ቤተ ክርስቲያን “የተወገዘ ይሁን” ስለሚል አውግዟል:: መጠርያቸውም ሊቀ ጳጳስና ቆሞስ ተብሎ ይጠራ የነበረው አቶ ተብሎ እንዲተካ በሙሉ ድምጽ ተወስኗል። ሕገ ወጥነት ሲመቱ እንዲፈጸም ያስተባበሩና ሥልጣነ ክህነት ያላቸው አካላት በሙሉ ተወግዘው ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ በተጨማሪ ወስኗል።
በጸጸት የተመለሱት አባ ጸጋ ዘአብ ብቻ በውግዘት ሳይለዩ በልዩነት ተይዘው በቅኖና ቤተ ክርስቲያን ጉዳያቸው እንዲታይና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መንገድ በይቅርታ ከተመለሱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.